ኅዳር 9 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ኅዳር 9 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 48 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 27 ከአን. 1-9 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዜና መዋዕል 21-25 (8 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 1 ዜና መዋዕል 23:1-11 (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ኤልሳዕ—ጭብጥ፦ ለይሖዋ አገልጋዮች ጥልቅ አክብሮት ይኑራችሁ—w05 8/1 ገጽ 9 አን. 6 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አርማጌዶን ምንድን ነው?—የቃላት መፍቻ፣ nwt ገጽ 1638 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
የወሩ ጭብጥ፦ “እኔ ተከልኩ፤ አጵሎስ አጠጣ፤ ያሳደገው ግን አምላክ ነው።”—1 ቆሮ. 3:6
10 ደቂቃ፦ “እኔ ተከልኩ፤ አጵሎስ አጠጣ፤ ያሳደገው ግን አምላክ ነው።” በወሩ ጭብጥ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። (1 ቆሮ. 3:6) ጊዜ በፈቀደ መጠን፣ መጋቢት 1, 1993 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 20-23 ላይ ያሉ አንዳንድ ነጥቦችን አቅርብ። በዚህ ወር በአገልግሎት ስብሰባ ላይ የሚቀርቡትን አንዳንድ ክፍሎች በአጭሩ ከልስ፤ እንዲሁም ከወሩ ጭብጥ ጋር ያላቸውን ተያያዥነት ግለጽ።
20 ደቂቃ፦ “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት።” በውይይት የሚቀርብ። ሁለት አጫጭር ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ፤ አንደኛው ሠርቶ ማሳያ በዚህ ርዕስ ላይ ከተጠቀሱት አቀራረቦች አንዱን የሚያሳይ ይሁን፤ በሌላኛው ሠርቶ ማሳያ ላይ ደግሞ አስፋፊዎች የሚጠቀሙበት ሌላ ውጤታማ የሆነ መግቢያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 111 እና ጸሎት