በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለው መጽሐፍ ሰዎችን ለማስተማር የምንጠቀምበት ዋነኛ መሣሪያ ነው። ይሁን እንጂ በዚህ መጽሐፍ ተጠቅመን አንድን ሰው ከማስተማራችን በፊት መጽሐፉን ልንሰጠው ይገባል። በመሆኑም ሁላችንም የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ በማበርከት ረገድ ውጤታማ ለመሆን መጣር አለብን። (ምሳሌ 22:29) መጽሐፉን ማበርከት የሚቻልባቸው የተለያዩ ዘዴዎች አሉ፤ አስፋፊዎች ለእነሱ ውጤታማ ሆነው ያገኟቸውን ዘዴዎች መጠቀም ይኖርባቸዋል።
በዚህ ወር እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ፦
ይህን ማድረግ የምትችሉት እንዴት እንደሆነ በቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራማችሁ ወቅት ተለማመዱ።
አገልግሎት ስትወጡ ምን ለማለት እንዳሰባችሁ ከሌሎች አስፋፊዎች ጋር ተነጋገሩ። (ምሳሌ 27:17) መግቢያችሁ ውጤታማ እንዳልሆነ ካስተዋላችሁ ቀይሩት።