ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 106-109
‘ለይሖዋ ምስጋና አቅርቡለት’
እስራኤላውያን የይሖዋን የማዳን ሥራዎች ወዲያውኑ የረሱት ለምንድን ነው?
ትኩረታቸው ያረፈው በይሖዋ ላይ ሳይሆን በራሳቸው ምቾትና በሚፈልጓቸው ነገሮች ላይ ነበር
ከልብ አመስጋኝ ለመሆንና ይህን ባሕርይ ይዘህ ለመቀጠል ምን ማድረግ ትችላለህ?
አመስጋኝ እንድትሆን በሚያነሳሱህ በርካታ ነገሮች ላይ ትኩረት አድርግ
በወደፊቱ ተስፋህ ላይ አሰላስል
ከይሖዋ ያገኘኸውን በረከት ለይተህ በመጥቀስ የምስጋና ጸሎት አቅርብ