ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘካርያስ 1-8
‘የአንድን አይሁዳዊ ልብስ አጥብቆ መያዝ’
ከብሔራት ቋንቋዎች ሁሉ የተውጣጡ አሥር ሰዎች የአንድን አይሁዳዊ ልብስ አጥብቀው በመያዝ “ከእናንተ ጋር እንሄዳለን” እንደሚሉ በትንቢት ተነግሯል። በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት፣ ከሁሉም ብሔራት የተውጣጡ ብዙ ሰዎች ከቅቡዓን ክርስቲያኖች ጋር አብረው ይሖዋን ለማምለክ ወደ ንጹሕ አምልኮ እየጎረፉ ነው
በዛሬው ጊዜ፣ ሌሎች በጎች ቅቡዓን ክርስቲያኖችን የሚደግፉባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?
በስብከቱ ሥራ የተሟላ ተሳትፎ ያደርጋሉ
ለሥራው በፈቃደኝነት የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋሉ