ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 48–50
ከአረጋውያን ብዙ ነገር መማር ይቻላል
አረጋውያን ይሖዋ በእነዚህ የመጨረሻዎቹ ቀናት ላከናወናቸው “ድንቅ ሥራዎች” የዓይን ምሥክር ናቸው፤ እነሱ የሚነግሩን ተሞክሮ በይሖዋና እሱ በገባው ቃል ላይ ያለንን እምነት ያጠናክርልናል። (መዝ 71:17, 18) በጉባኤያችሁ ውስጥ አረጋውያን ካሉ ስለሚከተሉት ጉዳዮች ጠይቋቸው፦
ይሖዋ ተፈታታኝ ሁኔታዎችን ተቋቁመው እሱን ማገልገላቸውን እንዲቀጥሉ የረዳቸው እንዴት እንደሆነ
በሕይወት ዘመናቸው የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ቁጥር ምን ያህል እንዳደገ
ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ያለን ግንዛቤ እየጠራ በመምጣቱ የተሰማቸውን ደስታ
በይሖዋ ድርጅት ውስጥ ያዩትን መሻሻል