ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፀአት 39–40
ሙሴ የተሰጠውን መመሪያ በጥንቃቄ ተከትሏል
ሙሴ ከማደሪያ ድንኳኑ አሠራርና አተካከል ጋር በተያያዘ ይሖዋ የሰጠውን ዝርዝር መመሪያ በጥንቃቄ ተከትሏል። እኛም በተመሳሳይ ከይሖዋ ድርጅት የምናገኘውን መመሪያ በሙሉ ማዳመጥ እንዲሁም በፍጥነትና በሙሉ ልብ መታዘዝ ይኖርብናል። መመሪያው ያን ያህል አስፈላጊ ባይመስልም ወይም መመሪያው የተሰጠበት ምክንያት ባይገባንም እንኳ እንዲህ ማድረጋችን አስፈላጊ ነው።—ሉቃስ 16:10
በሚከተሉት ጉዳዮች ረገድ መመሪያዎችን ማዳመጥና በጥንቃቄ መከተል ያለብን ለምንድን ነው?
በመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ ወቅት
ለድንገተኛ ሕክምና ዝግጅት ከማድረግ ጋር በተያያዘ
ለአደጋ ዝግጁ ከመሆን ጋር በተያያዘ