ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
ሕጉ፣ ይሖዋ ለድሆች ያለውን አሳቢነት የሚያሳየው እንዴት ነው?
ድሆችና ርስት የሌላቸው ሰዎች ከሌሎች እስራኤላውያን እርዳታ የሚያገኙበት ዝግጅት ተደርጎ ነበር (ዘዳ 14:28, 29፤ it-2 1110 አን. 3)
ዕዳ ያለባቸው እስራኤላውያን፣ በሰንበት ዓመት ዕዳቸው ‘ይሰረዝላቸው’ ነበር (ዘዳ 15:1-3፤ it-2 833)
ራሱን ለባርነት የሸጠ አንድ እስራኤላዊ በሰባተኛ ዓመቱ ነፃ ይወጣል፤ ጌታው የሚያሰናብተው ስጦታ ሰጥቶ ነው (ዘዳ 15:12-14፤ it-2 978 አን. 6)
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ችግር ላይ ለወደቁ ክርስቲያኖች አሳቢነት ለማሳየት ምን ማድረግ እችላለሁ?’