ክርስቲያናዊ ሕይወት
“ፈጽሞ አትጨነቁ”
ይሖዋ በጥንቷ እስራኤል የነበሩ ድሆችን ረድቷቸዋል። በዛሬው ጊዜ በአገልጋዮቹ መካከል ያሉ ድሆችን እየረዳ ያለው በየትኞቹ መንገዶች ነው?
ስለ ገንዘብ ሚዛናዊ አመለካከት እንዲኖራቸው ያስተምራቸዋል።—ሉቃስ 12:15፤ 1ጢሞ 6:6-8
ለራሳቸው አክብሮት እንዲኖራቸው ይረዳቸዋል።—ኢዮብ 34:19
ጠንክረው እንዲሠሩና ጎጂ ልማዶችን እንዲያስወግዱ ያስተምራቸዋል።—ምሳሌ 14:23፤ 20:1፤ 2ቆሮ 7:1
አፍቃሪ በሆነ የወንድማማች ማኅበር ውስጥ እንዲታቀፉ አድርጓል።—ዮሐ 13:35፤ 1ዮሐ 3:17, 18
ተስፋ ሰጥቷቸዋል።—መዝ 9:18፤ ኢሳ 65:21-23
ያለንበት ሁኔታ ምንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆን መጨነቅ አይኖርብንም። (ኢሳ 30:15) አስቀድመን የአምላክን መንግሥት መፈለጋችንን እስከቀጠልን ድረስ ይሖዋ የሚያስፈልጉን ቁሳዊ ነገሮች እንዲሟሉልን ያደርጋል።—ማቴ 6:31-33
ፍቅር ለዘላለም ይኖራል—ድህነት ቢኖርም—ኮንጎ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
የክልል ስብሰባ በሚደረግባቸው ቦታዎች አቅራቢያ የሚኖሩ ወንድሞች ረጅም ርቀት ተጉዘው ወደ ስብሰባው ለሚመጡ ወንድሞች የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ ያሳዩት እንዴት ነው?
ይህ ቪዲዮ፣ ይሖዋ ለድሆች ስላለው ፍቅር ምን ያስተምረናል?
በቁሳዊ ረገድ ሀብታምም ሆንን ድሃ ይሖዋን መምሰል የምንችለው እንዴት ነው?