ከነሐሴ 11-17
ምሳሌ 26
መዝሙር 88 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. ‘ከሞኝ ሰው’ ራቁ
(10 ደቂቃ)
“ሞኝ ሰው” ክብር አይገባውም (ምሳሌ 26:1፤ it-2 729 አን. 6)
“ሞኞች” ብዙውን ጊዜ ጠንከር ያለ ተግሣጽ ያስፈልጋቸዋል (ምሳሌ 26:3፤ w87 10/1 19 አን. 12)
“ሞኝ” ሰው እምነት አይጣልበትም (ምሳሌ 26:6፤ it-2 191 አን. 4)
ፍቺ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ሞኝ ሰው” የሚለው አገላለጽ ምክንያታዊ ያልሆነንና ሥነ ምግባር የጎደለው አካሄድ የሚከተልን ሰው ያመለክታል።
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
ምሳሌ 26:4—ይህን ጥቅስ በሥራ ላይ ማዋል የምንችለው እንዴት ነው? (w23.09 19 አን. 18)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) ምሳሌ 26:1-20 (th ጥናት 5)
4. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። አንድ ትራክት ተጠቅመህ ውይይት ጀምር። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 5)
5. ተመላልሶ መጠየቅ
(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ባለፈው ባበረከትከው ትራክት ላይ ተመሥርተህ ውይይቱን ቀጥል። (lmd ምዕራፍ 7 ነጥብ 4)
6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ
(5 ደቂቃ) ጥናትህ ለዘመዱ ለመስበክ እንዲዘጋጅ እርዳው። (lmd ምዕራፍ 11 ነጥብ 5)
መዝሙር 94
7. በግል ጥናት አማካኝነት “ለመዳን የሚያበቃ ጥበብ” አግኙ
(15 ደቂቃ) ውይይት።
ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ጢሞቴዎስ ከጨቅላነቱ ጀምሮ የተማራቸው ቅዱሳን መጻሕፍት ያላቸውን ዋጋ አስታውሶታል። እነዚህ መጻሕፍት ጢሞቴዎስን “ለመዳን የሚያበቃ ጥበብ” እንዲያገኝ አስችለውታል። (2ጢሞ 3:15) የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች በጣም ውድ ከመሆናቸው አንጻር እያንዳንዱ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብና ለማጥናት ጊዜ መመደቡ አስፈላጊ ነው። ይሁንና ማጥናት የማያስደስተን ቢሆንስ?
አንደኛ ጴጥሮስ 2:2ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትን እየወደድነው ልንሄድ እንችላለን?
ለአምላክ ቃል ‘ጉጉት ማዳበር’ የምንችለው እንዴት ነው?—w18.03 29 አን. 6
ድርጅቱ ያዘጋጃቸው አፕሊኬሽኖችና ድረ ገጾች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን አስደሳች እንዲሆንልን የሚረዱን እንዴት ነው?
ድርጅቱ ያከናወናቸው ነገሮች—የJW ላይብረሪ አጠቃቀም የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
ከJW ላይብረሪ ምን ጥቅም አግኝታችኋል®?
በጣም የምትወዱት የትኛውን ገጽታ ነው?
የትኞቹን ገጽታዎች መማርና መጠቀም መጀመር ትፈልጋላችሁ?
8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) lfb ትምህርት 8-9