ከኅዳር 17-23
መኃልየ መኃልይ 6–8
መዝሙር 34 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. በር ሳይሆን ቅጥር ሁኑ
(10 ደቂቃ)
የሱላማዊቷ ልጃገረድ ወንድሞች ሥነ ምግባራዊ ንጽሕናዋን እንድትጠብቅ ይፈልጉ ነበር (መኃ 8:8, 9፤ w15 1/15 32 አን. 15-16)
የሥነ ምግባር ፈተናዎችን በተሳካ ሁኔታ በመቋቋሟ ሰላም አግኝታለች (መኃ 8:10፤ yp 188 አን. 2)
በዚህ ረገድ ለወጣቶች አርዓያ ትሆናለች (yp2 33)
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘በጉባኤያችን ውስጥ ያሉት ያላገቡ ክርስቲያኖች በር ሳይሆን ቅጥር እንዲሆኑ ልረዳቸው የምችለው እንዴት ነው?’
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
መኃ 8:6—እውነተኛ ፍቅር ‘የያህ ነበልባል’ ተብሎ የተጠራው ለምንድን ነው? (w15 1/15 29 አን. 3)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
4. ውይይት መጀመር
(2 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። የjw.org የአድራሻ ካርድ ተጠቅመህ ውይይት ጀምር። (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 4)
5. ውይይት መጀመር
(2 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። በንግድ ክልል ውስጥ ትራክት ተጠቅመህ ውይይት ጀምር። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 4)
6. ውይይት መጀመር
(2 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ወዳጃዊ የሆነ ጭውውት ጀምር፤ መመሥክር ከመቻልህ በፊት ጭውውቱ ይጠናቀቃል። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 4)
7. እምነታችንን ማብራራት
(5 ደቂቃ) ሠርቶ ማሳያ። ijwfq ርዕስ 43—ጭብጥ፦ የይሖዋ ምሥክሮች ከፍቅር ጓደኝነት ጋር በተያያዘ የሚከተሉት መመሪያ አላቸው? (th ጥናት 7)
መዝሙር 121
8. ከፆታ ብልግና ሽሹ
(15 ደቂቃ) ውይይት።
በመኃልየ መኃልይ መጽሐፍ ላይ እረኛው ሱላማዊቷን ልጃገረድ ፍቅር በሚቀሰቅስ አካባቢ ላይ አብራው እንድትንሸራሸር ጋብዟት ነበር። (መኃ 2:10-14) ይህን ያላት በቅን ልቦና ተነሳስቶ ሊሆን ቢችልም የልጃገረዷ ጥበበኛ ወንድሞች ግብዣውን እንዳትቀበል ለማድረግ ሲሉ ሥራ ሰጧት። (መኃ 2:15) ፍቅር በሚቀሰቅስ አካባቢ ውስጥ ከምትወደው ሰው ጋር ብቻዋን መሆኗ ለፈተና ሊዳርጋት እንደሚችል ተገንዝበው ነበር።
መጽሐፍ ቅዱስ ለክርስቲያኖች “ከፆታ ብልግና ሽሹ” የሚል ማሳሰቢያ ይሰጣል። (1ቆሮ 6:18) ወደ ኃጢአት ሊመራ ከሚችል ከማንኛውም ድርጊት መራቅ ይኖርብናል። በመንፈስ ተመርቶ የመኃልየ መኃልይ መጽሐፍን የጻፈው ሰለሞን እንዲህ ሲልም ጽፏል፦ “ብልህ ሰው አደጋ ሲያይ ይሸሸጋል፤ ተሞክሮ የሌለው ግን ዝም ብሎ ይሄዳል፤ መዘዙንም ይቀበላል።”—ምሳሌ 22:3
አምላክ “በልብ ውስጥ ያለውን ሚስጥር ያውቃል” የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
ከዚህ አጭር ድራማ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) lfb ትምህርት 36-37