ከታኅሣሥ 8-14
ኢሳይያስ 6–8
መዝሙር 75 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. “እነሆኝ! እኔን ላከኝ!”
(10 ደቂቃ)
ኢሳይያስ የአምላክ ቃል አቀባይ ለመሆን ያለምንም ማመንታት ራሱን አቅርቧል (ኢሳ 6:8፤ ip-1 93-94 አን. 13-14)
ኢሳይያስ የተሰጠው ሥራ ከባድ ነበር (ኢሳ 6:9, 10፤ ip-1 95 አን. 15-16)
የኢሳይያስ የነቢይነት ተልእኮ ኢየሱስ ለሚያከናውነው ሥራ ጥላ ሆኗል (ማቴ 13:13-15፤ ip-1 99 አን. 23)
ለማሰላሰል የሚረዳ ጥያቄ፦ የፈቃደኝነት መንፈስ በማሳየት ረገድ ማሻሻያ ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
ኢሳ 7:3, 4—ይሖዋ ክፉውን ንጉሥ አካዝን ያዳነው ለምንድን ነው? (w06 12/1 9 አን. 3)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
4. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ሰዎችን ውደዱ በተባለው ብሮሹር ተጨማሪ መረጃ ሀ ላይ የሚገኝ አንድ እውነት አካፍል። (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 5)
5. ተመላልሶ መጠየቅ
(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠና ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 3)
6. ተመላልሶ መጠየቅ
(5 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እንደምናስጠና አሳየው። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 5)
መዝሙር 83
7. መለያችን የሆነው ከቤት ወደ ቤት አገልግሎት
(15 ደቂቃ) ውይይት።
እንደ ኢየሱስና እንደ መጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች ሁሉ የይሖዋ ምሥክሮችም ከቤት ወደ ቤት በመስበክ ይታወቃሉ።—ሉቃስ 10:5፤ ሥራ 5:42
እርግጥ ነው፣ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ከቤት ወደ ቤት መስበካችንን ለማቆም ተገደን ነበር። በዚህም የተነሳ መደበኛ ባልሆነ ምሥክርነት፣ ደብዳቤ በመጻፍና ስልክ በመደወል ምሥራቹን በማስፋፋት ላይ አተኮርን። እነዚህን ግሩም የስብከት ዘዴዎች መልመድ የምንችልበት አጋጣሚ በማግኘታችን በጣም ደስተኞች ነን! ሆኖም አሁንም ቢሆን ምሥራቹን የምናስፋፋበት ዋነኛው መንገድ ከቤት ወደ ቤት ማገልገል ነው። አዘውትራችሁ ከቤት ወደ ቤት ለማገልገል ሁኔታችሁ ይፈቅድላችኋል?
ከቤት ወደ ቤት ማገልገላችን የሚከተሉትን ነገሮች ለማከናወን የሚረዳን እንዴት ነው?
ክልላችንን አጥርተን ለመሸፈን
የማስተማር ችሎታችንን ለማሻሻል እንዲሁም እንደ ድፍረት፣ ከአድልዎ ነፃ መሆን እና የራስን ጥቅም መሥዋዕት ማድረግ ያሉትን ባሕርያት ለማዳበር
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመር
የአየሩ ጠባይ አስቸጋሪ ቢሆንም መስበክ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦
በፌሮ ደሴቶች ከሚኖሩት የራሳቸውን ጥቅም መሥዋዕት የሚያደርጉ ወንጌላውያን ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) lfb ትምህርት 42-43