ከታኅሣሥ 22-28
ኢሳይያስ 11–13
መዝሙር 14 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. ስለ መሲሑ የተነገሩ ትንቢቶች
(10 ደቂቃ)
የእሴይ ልጅ በሆነው በዳዊት በኩል የእሴይ ዘር ይሆናል (ኢሳ 11:1፤ ip-1 159 አን. 4-5)
የአምላክ መንፈስና ይሖዋን የመፍራት መንፈስ ይኖረዋል (ኢሳ 11:2, 3ሀ፤ ip-1 159 አን. 6፤ 160 አን. 8)
ጻድቅና መሐሪ ፈራጅ ይሆናል (ኢሳ 11:3ለ-5፤ ip-1 160 አን. 9፤ 161 አን. 11)
ለማሰላሰል የሚረዳ ጥያቄ፦ ኢየሱስን ከየትኛውም ሰብዓዊ ገዢ የላቀ የሚያደርገው ምንድን ነው?
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
ኢሳ 11:10—ይህ ትንቢት የተፈጸመው እንዴት ነው? (ip-1 165-166 አን. 16-18)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) ኢሳ 11:1-12 (th ጥናት 11)
4. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 5)
5. ተመላልሶ መጠየቅ
(4 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። ግለሰቡ ያነሳውን ጥያቄ ለመመለስ jw.orgን ተጠቀም። (lmd ምዕራፍ 8 ነጥብ 3)
6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ
(5 ደቂቃ) ጥናትህ አብሮህ ከቤት ወደ ቤት ለመስበክ እንዲዘጋጅ እርዳው። (lmd ምዕራፍ 11 ነጥብ 4)
መዝሙር 57
7. ‘በጽድቅ ትፈርዳላችሁ?’
(15 ደቂቃ) ውይይት።
በየዕለቱ በሰዎች ላይ እንፈርዳለን፤ አንዳንድ ጊዜም ይህን የምናደርገው በደመ ነፍስ ነው። ብዙውን ጊዜ፣ በምናየው ነገር ላይ ተመሥርተን መደምደሚያ ላይ መድረስ ይቀናን ይሆናል። ይሁንና ምሳሌያችን የሆነው ኢየሱስ የሚፈርደው ከዚህ በተለየ መንገድ ነው። (ኢሳ 11:3, 4) ኢየሱስ የሰዎችን ልብ ማንበብ እንዲሁም አስተሳሰባቸውንና ዝንባሌያቸውን ማስተዋል ይችላል። እኛ ግን እንዲህ ያለ ችሎታ የለንም። ያም ቢሆን ኢየሱስን ለመምሰል አቅማችን የፈቀደውን ያህል ማድረግ እንችላለን። ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦ “የሰውን ውጫዊ ገጽታ በማየት አትፍረዱ፤ ከዚህ ይልቅ በጽድቅ ፍረዱ።”—ዮሐ 7:24
በምናየው ነገር ላይ ተመሥርተን በሰዎች ላይ የምንፈርድ ከሆነ ለአገልግሎት ያለን ቅንዓትና ውጤታማነታችን ሊገደብ ይችላል። ለምሳሌ የአንድ ዘር ወይም ሃይማኖት አባላት በብዛት በሚኖሩበት አካባቢ ለመስበክ እናመነታለን? ሀብታም ወይም ድሃ በሆኑ ሰፈሮች መስበክስ ይከብደናል? የአንድን ሰው ውጫዊ ገጽታ በማየት ብቻ ለመልእክቱ ፍላጎት እንደማይኖረው እናስባለን? የአምላክ “ፈቃድ ሁሉም ዓይነት ሰዎች እንዲድኑና የእውነትን ትክክለኛ እውቀት እንዲያገኙ ነው።”—1ጢሞ 2:4
ከመጠበቂያ ግንብ የምናገኛቸው ትምህርቶች—የሰውን ውጫዊ ገጽታ በማየት አትፍረዱ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
በቪዲዮው ላይ እንደተጠቀሰው አንዳንድ ሰዎች በሌሎች ላይ የሚፈርዱት ምንን መሠረት አድርገው ነው?
መድልዎ ወደ ጉባኤው ሾልኮ እንዲገባ ከፈቀድን ምን መጥፎ ውጤት ሊኖረው ይችላል?
ቃለ መጠየቅ የተደረገላቸው ክርስቲያኖች በውጫዊ ገጽታ ላይ ተመሥርተው እንዳይፈርዱ የረዳቸው ምንድን ነው?
ከዚህ የመጠበቂያ ግንብ ርዕስ አንተ ምን ትምህርት አግኝተሃል?
8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) lfb ትምህርት 46-47