የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g98 3/8 ገጽ 3
  • ምንነቱን መረዳት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ምንነቱን መረዳት
  • ንቁ!—1998
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ማረጥ የሚያስከትላቸውን አስቸጋሪ ሁኔታዎች መቋቋም
    ንቁ!—2013
  • በማረጥ ምክንያት የሚመጡትን ችግሮች መቋቋም
    ንቁ!—1998
  • የተሻለ ግንዛቤ ማግኘት
    ንቁ!—1998
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2013
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1998
g98 3/8 ገጽ 3

ምንነቱን መረዳት

ማረጥ ከሴቶች ዕድሜ መግፋት ጋር የሚመጣ ነገር ነው። ይሁን እንጂ ስለ ማረጥ የተሳሳተ ግንዛቤ ሰፍኖ ቆይቷል። ዘ ሳይለንት ፓሴጅ—ሜኖፖዝ የተባለው መጽሐፍ እንደሚለው የ19ኛው መቶ ዘመን የማሕጸን ሐኪሞች ማረጥ “የሴቶችን ሥርዓተ ነርቭ እንዳልነበረ እንደሚያደርግና ውበታቸውንና ለዛቸውን ጨርሶ እንደሚያሟጥጥ” አድርገው ያምኑ ነበር ይላል።

እንዲህ ያለው የተሳሳተ ግንዛቤ በጣም ሥር የሰደደ ነው። በዚህም ምክንያት ማረጥ ብዙ ሴቶችን ገና ከሩቁ ያስፈራቸዋል። ከማረጥ ጋር ተያይዘው የሚመጡትን የሥነ ልቦና ችግሮች መወጣት “በአንዲት ሴት ሕይወት ውስጥ ከሚያጋጥሙት ችግሮች በጣም ከፍተኛው ነው” በማለት ናቹራል ሜኖፖዝ—ዘ ኮምፕሊት ጋይድ ቱ ኤ ውመንስ ሞስት ሚስአንደርሰቱድ ፓሴጅ የተባለው መጽሐፍ ይናረጋል።

ለወጣትነትና ለወጣትነት ቁመና ከፍተኛ ግምት በሚሰጥባቸው ማኅበረሰቦች የማረጥ ምልክቶች መታየት መጀመራቸው የወጣትነት ዕድሜ በድንገት አብቅቶ እርጅና መጀመሩን እንደሚያመለክት ተደርጎ ይወሰዳል። በዚህ ምክንያት አንዳንድ ሴቶች አዲስና ተፈላጊ ያልሆነ የሕይወታቸው ክፍል እንደጀመረ ስለሚሰማቸው ማረጥን በጣም ይፈራሉ። እንዲያውም አንዳንዶች “ከፊል ሞት” አድርገው ይመለከቱታል።

ይሁን እንጂ የዘመናችን ሴቶች እዚህ ዕድሜ ላይ ሲደርሱ በድንቁርና ተሸብበው መሠቃየት አይኖርባቸውም። በማረጥ ዙሪያ ተዘርግቶ የቆየው ምሥጢራዊ ግርዶሽ በመገለጥ ላይ ነው። በዚህ መስክ ብዙ ጥናትና ምርምር በመደረግ ላይ ሲሆን ይህን የሽግግር ወቅት ቀለል የሚያደርጉ በርካታ የሕክምና ዓይነቶች ተገኝተዋል። መጽሔቶች፣ ጋዜጦችና መጻሕፍት በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ትኩረት በማድረግ ከአሁን በፊት አንዳንዶች ለመጠየቅ እንኳን ያሳፍሯቸው ለነበሩት ጥያቄዎች መልስና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው። የሕክምና ባለሞያዎችም ሴቶች ሊያጋጥሟቸው ስለሚችሉ ችግሮች የበለጠ ግንዛቤ አግኝተዋል።

ለዚህ ርዕሰ ጉዳይ ይህን የሚያክል ትኩረት የተሰጠው ለምንድን ነው? ስለማረጥ የተሻለ ግንዛቤ ማግኘት ብዙ ሴቶች የሚያድርባቸውን ፍርሃት፣ አጉል እምነትና ብስጭት ለማስወገድ ስለሚያስችል ነው። በብዙ አገሮች የሴቶች አማካይ ዕድሜ እየጨመረ በመሄዱ በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፍኖ የቆየውን የዝምታ ሴራ ለማፍረስና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚፈልጉ ሴቶች ቁጥር በዝቷል። ለጥያቄዎቻቸው ቀላልና ቀጥተኛ የሆኑ መልሶች ለማግኘት ይፈልጋሉ። አብዛኞቹ ሴቶች የዕድሜያቸውን ሲሶ የሚያሳልፉት ካረጡ በኋላ ስለሆነ በዚህ ጊዜ ስለሚከሰቱት ሁኔታዎች ለማወቅ መፈለጋቸው ተገቢ ነው።

በዩናይትድ ስቴትስ ከሕዝብ ቆጠራ የተገኙ መረጃዎች በሚቀጥለው አሥር ዓመት በማረጥ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ሴቶች ቁጥር 50 በመቶ እንደሚጨምር ይጠቁማሉ። እነዚህ ሴቶች ከማረጥ ጋር ስለሚመጡት የጤንነት ችግሮች፣ ትኩሳትና ላብ፣ የስሜት መለዋወጥ፣ ምቾት ማጣት፣ እንዲሁም ስሜታዊና አካላዊ ለውጦች ማወቅ ይፈልጋሉ። እነዚህ ነገሮች የሚመጡት ለምንድን ነው? አንዲት ሴት ካረጠች በኋላ የሚኖራት ዕድሜ ምንም እርባና የለውም ማለት ነውን? ማረጥ የአንድን ሴት ጠባይ ይለውጣል? የሚቀጥሉት ርዕሶች እነዚህን ጥያቄዎች ይመረምራሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ