የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 2 ገጽ 10-ገጽ 11 አን. 1
  • አምላክ የመጀመሪያዎቹን ወንድና ሴት ፈጠረ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ የመጀመሪያዎቹን ወንድና ሴት ፈጠረ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጀመሪያዎቹ ወንድና ሴት
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • የምናረጀውና የምንሞተው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
  • የመጨረሻው ጠላት የሆነው ሞት ይደመሰሳል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • የኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ለአንተ ምን ትርጉም አለው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 2 ገጽ 10-ገጽ 11 አን. 1
አዳምና ሔዋን በኤደን የአትክልት ስፍራ

ትምህርት 2

አምላክ የመጀመሪያዎቹን ወንድና ሴት ፈጠረ

ይሖዋ ኤደን በሚባል ቦታ የአትክልት ስፍራ አዘጋጀ። በአትክልት ስፍራው ውስጥ ብዙ አበቦች፣ ዛፎችና እንስሳት ነበሩ። ከዚያም አምላክ የመጀመሪያውን ሰው አዳምን ከአፈር ሠራውና በአፍንጫው እፍ አለበት። በዚህ ጊዜ ሕይወት ያለው ሰው ሆነ! ይሖዋ አዳምን የአትክልት ስፍራውን እንዲንከባከብና ለእንስሳቱ በሙሉ ስም እንዲያወጣ ነገረው።

ይሖዋ ለአዳም አንድ አስፈላጊ መመሪያ ሰጠው። እንዲህ አለው፦ ‘በአትክልቱ ስፍራ ያሉት ዛፎች የሚያፈሩትን ፍሬ ሁሉ መብላት ትችላለህ፤ ከአንዱ ዛፍ ግን አትብላ። ከዚያ ዛፍ ከበላህ ትሞታለህ።’

ቀጥሎ ይሖዋ ‘ለአዳም ረዳት እሠራለታለሁ’ አለ። ከዚያም አዳም ከባድ እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገ፤ በኋላም ከአዳም የጎድን አጥንቶች አንዱን በመጠቀም ለአዳም ሚስት ሠራለት። የሚስቱ ስም ሔዋን ነበር። ይሖዋ የመጀመሪያውን ቤተሰብ የመሠረተው በዚህ መንገድ ነው። ይሖዋ ሔዋንን ሲፈጥርለት አዳም ምን ተሰማው? አዳም በጣም ተደስቶ እንዲህ አለ፦ ‘ይሖዋ የጎድን አጥንቴን ወስዶ ሚስት ሠራልኝ! አሁን እንደ እኔ ያለች ሰው አገኘሁ!’

ይሖዋ ለአዳምና ለሔዋን ልጆች እንዲወልዱና ምድርን እንዲሞሉ ነገራቸው። በተጨማሪም መላዋን ምድር በመንከባከብ ገነት ወይም ልክ እንደ ኤደን የአትክልት ስፍራ ውብ መናፈሻ እንዲያደርጓት ፈልጎ ነበር። ግን እንደዚያ አልሆነም። ለምን? በሚቀጥለው ምዕራፍ ላይ ለዚህ ጥያቄ መልስ እናገኛለን።

“ፈጣሪ ከመጀመሪያውም ወንድና ሴት አድርጎ [ፈጠራቸው]።”—ማቴዎስ 19:4

ጥያቄ፦ ይሖዋ ለአዳም ምን ሥራ ሰጠው? አዳምና ሔዋን አምላክ እንዳይበሉ ካዘዛቸው ዛፍ ፍሬ ቢበሉ ምን ይሆናሉ?

ዘፍጥረት 1:27-31፤ 2:7-9, 15-23፤ መዝሙር 115:16፤ ማቴዎስ 19:4-6

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ