የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w94 4/15 ገጽ 30
  • ታስታውሳለህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታስታውሳለህን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዊልያም ዊስተን መናፍቅ ወይስ ሐቀኛ ምሁር?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ዊልያም ዊስተን
    ንቁ!—2014
  • ጥሩና መጥፎ ፍሬዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • የማርያም ፍልሰታ በአምላክ የተገለጠ ቀኖና ነውን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
w94 4/15 ገጽ 30

ታስታውሳለህን?

በቅርብ ጊዜ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች አንብበሃቸዋልን? አንብበሃቸው ከሆነ ቀጥሎ ያሉትን ብታስታውስ ደስ ይልህ ይሆናል፦

▫ እስራኤላውያኑ ሰላዮች በጋለሞታይቱ በረዓብ ቤት ለማረፍ የመረጡት ለምን ነበር?

እስራኤላውያኑ ሰላዮች በአምላክ ሕግ የሚመሩ ሰዎች ስለነበሩ ረዓብ ቤት ለማደር የገቡት የብልግና ድርጊት ለመፈጸም አልነበረም። ጋለሞታ ቤት ማደራችን በከተማው ሰዎች አያስጠረጥረንም ብለው አስበው ሊሆን ይችላል። ቤትዋ በከተማው ግንብ ላይ የሚገኝ መሆኑም በቀላሉ ለማምለጥ ያስችላቸው ነበር። ከዚህም ይበልጥ ደግሞ ለእስራኤላውያን የተደረጉትን መለኮታዊ ክንዋኔዎች በመስማቷ ልቧ ወደ ተነካውና ወደ ተለወጠችው ኃጢአተኛ ቤት እንዲያመሩ ያደረጋቸው ይሖዋ እንደሆነ ግልጽ ነው።—12/15፣ ገጽ 24–25

▫ ቁጣ ጤንነታችንን የሚጎዳው እንዴት ነው?

ቁጣ ሰውነታችን የተጨነቁ ሆርሞኖችን እንዲያመነጭ እንደሚያደርጉት ጥናቶች ያመለክታሉ። ቶሎ ቶሎ በቁጣ መገንፈል ተከላካይ በሆኑት እና ጎጂ በሆኑት ኮሌስትሮሎች መካከል የሚዛን መዛባት ይፈጥርና ለልብ በሽታ ያጋልጠናል።—12/15፣ ገጽ 32

▫ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን በብዛት ለማበርከት የሚረዱ ምን ሐሳቦች ቀርበውልን ነበር?

መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን በንቃት ተከታተል፣ አቀራረብህን ቀላል አድርግ፣ አጠር ያሉ ጥቂት መግቢያዎችን አዘጋጅና አቀራረብህን እንደ ሁኔታው ለዋውጥ፣ የግል ግብ ይኑርህ።—1/1፣ ገጽ 24–25

▫ ሙሴ ልንከተለው የሚገባን ጥሩ ቲኦክራሲያዊ ምሳሌ የሆነው ለምንድን ነው?

ሙሴ የይሖዋን መመሪያ ለማግኘት ይጥር ነበር፤ ይጨነቅ የነበረው ስለ ራሱ ፍላጎት ሳይሆን ስለ ይሖዋ ክብር ነበር፤ ጠንካራ እምነት ነበረው። ሙሴ የእስራኤል ሕዝብ ገዥ ይሖዋ መሆኑን ፈጽሞ አይረሳም ነበር።—1/15፣ ገጽ 11

▫ መለኮታዊ ትምህርት ድል የሚያደርግባቸው አንዳንድ መንገዶች ምንድን ናቸው?

መለኮታዊው ትምህርት የይሖዋ ሕዝቦች እየጨመረ የሚሄድ የቅዱሳን ጽሑፎች እውቀት እንዲያገኙ በማድረግ ድል ያደርጋል። ሰዎችን ወደ መንፈሳዊ ብርሃን ያመጣል፤ እንዲሁም ቅን ሰዎች አምላክን ‘በመንፈስና በእውነት’ የሚያመልኩበትን መንገድ ያሳያቸዋል። (ዮሐንስ 4:24) በተጨማሪም መለኮታዊው ትምህርት መከራንና ይህንን ክፉ ዓለም ድል ያደርጋል።—2/1፣ ገጽ 10–12

▫ ውጤታማ ምክር ለመለገስ ቁልፉ ምንድን ነው?

ቁልፉ ለሌላው ሰው ተገቢ አክብሮት ማሳየትና ግለሰቡ በክብርና በጥንቃቄ መያዝ እንዳለበት መገንዘብ ነው። ስለዚህ ተገቢውን አክብሮት የሚያሳይ አንድ ክርስቲያን መካሪ ደግና ጥብቅ ቢሆንም ለምክር ተቀባዩ ክብር ያለብሰዋል።—2/1፣ ገጽ 28

▫ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የማርያምን ፍልሰታ እንደ መሠረታዊ ትምህርት አድርጋ እንዴት ልትቀበለው ቻለች?

ኢየሱስ ከሞተ በኋላ በነበሩት የመጀመሪያዎቹ መቶ ዘመናት ማርያም ወደ ሰማይ አርጋለች የሚለው አሳብ በክርስቲያኖች ዘንድ ፈጽሞ የማይታወቅ ነበረ። የሥላሴ ትምህርት የቤተ ክርስቲያን ዋነኛ መሠረተ ትምህርት ከሆነ በኋላ ግን ለማርያም ከፍተኛ ቦታ መስጠት ተጀመረ። ፓፓ ፓየስ 12ኛ “የማርያምን ፍልሰታ በአምላክ የተገለጠ ቀኖና ነው ብለን ደንግገናል” ብለው እስካስታወቁበት እስከ ኅዳር 1, 1950 ድረስ ይህ የፍልሰታ ንድፈ ሐሳብ ተቀባይነት ያገኘ ቀኖና አልነበረም።—ሙኒፊከንቲስመስ ዲዮስ—2/15፣ ገጽ 26–27

▫ በኤርምያስ ምዕራፍ 24 ላይ የተገለጹት ሁለቱ የበለስ ቅርጫቶች ማለትም የጥሩው በለስ ቅርጫትና የመጥፎው በለስ ቅርጫት ምንን የሚወክሉ ናቸው?

ጥሩዎቹ በለሶች በመጀመሪያ በግዞት ወደ ባቢሎን ተወስደው የነበሩትንና በኋላም ወደ ይሁዳ የተመለሱትን ቀሪዎች የሚወክሉ ናቸው። መጥፎዎቹ በለሶች ደግሞ ለንጉሥ ናቡከደነፆር በይሖዋ ስም የማለውን መሐላ አፍርሶ ያመፀውን ንጉሥ ሴዴቅያስንና አብረውት ያመፁትን ሰዎች ይወክላሉ። በተመሳሳይም የበሰበሰ ፍሬ ካፈሩት የሕዝበ ክርስትና ቀሳውስት በተቃራኒ በሕይወታቸው ሁሉ ጥሩ ፍሬ ያፈሩ ዘመናዊ የመንፈሳዊ ቀሪዎች እንዳሉ እንመለከታለን።—3/1፣ ገጽ 14–16

▫ ኳርቶዴሲማንስ ተብለው ይጠሩ የነበሩት እነማን ናቸው? በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖችን ትኩረት የሚስቡትስ ለምንድን ነው?

ከሐዋርያት ዘመን በኋላ አንዳንዶች ሐዋርያት ያደርጉት እንደነበረው የጌታ ራትን በየዓመቱ ኒሣን 14 ላይ ያከብሩ ነበር። እነዚህ ሰዎች ከጊዜ በኋላ ኳርቶዴሲማንስ ወይም በእንግሊዝኛ “ፎርቲንዘርስ” (“አሥራ አራተኞች”) በመባል ይታወቁ ጀመር። ይህ ትኩረትን የሚስብ ነው፤ ምክንያቱም ሐዋርያት ከሞቱ በኋላም እንኳን ትክክለኛውን መንገድ ተከትለው በዓመት አንድ ጊዜ በኒሣን 14 ላይ የኢየሱስን ሞት የሚያስቡ አንዳንዶች እንደነበሩ ያሳያል።—3/15፣ ገጽ 4–5

▫ ዊልያም ዊስተን ማን ነበር?

በ18ኛው መቶ ዘመን በእንግሊዝ አገር ይኖር የነበረ በጣም የሚደነቅ ምሑርና የሰር አይዛክ ኒውተን የቅርብ ወዳጅ የነበረ ሰው ነው። ዊስተን የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎችን የተረጎመ፣ የሥላሴን መሠረተ ትምህርት በግልጽ የተቃወመና የከዋክብት ጥናትና የሒሳብ ትምህርት አስተማሪ የነበረ ሰው ነው። ሆኖም ዊስተን በይበልጥ የሚታወቀው የአይሁድ ታሪክ ጸሐፊ የነበረውን የፍላቪየስ ጆሴፈስን ጽሑፍ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ በመተርጎሙ ነው።—3/15፣ ገጽ 26–28

▫ ሰው በአምላክ መልክ ተፈጠረ የሚባለው እንዴት ነው? (ዘፍጥረት 1:27)

ሰው የአምላክን አስደናቂ ባሕርያት ማለትም ፍቅርን፣ ፍትህን፣ ጥበብንና ኃይልን እንዲሁም ሌሎች ባሕርያትን ማሳየት እንዲችል ሆኖ በመፈጠሩ ነው።—4/1፣ ገጽ 25

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ