የይሖዋ ምሥክሮች ያሳዩት በተግባር የተደገፈ እምነት፣ ክፍል 2፦ ብርሃኑ ይብራ
በ1919፣ ወንድም ራዘርፎርድና የሥራ ባልደረቦቹ ከእስር ከተፈቱ በኋላ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች መጠነ ሰፊ ሥራ ይጠብቃቸው ነበር። የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ብዙ ተቃዋሚዎች እንደሚያጋጥሟቸው፣ ስለ ቅዱሳን ጽሑፎች ያላቸው እውቀት እየጨመረ እንደሚሄድ እንዲሁም እምነታቸው በፈተና እንደሚጣራ የይሖዋ ምሥክሮች ያሳዩት በተግባር የተደገፈ እምነት፣ ክፍል 2፦ ብርሃኑ ይብራ በተባለው ቪዲዮ ላይ መመልከት ይቻላል። (ምሳሌ 4:18፤ ሚል. 3:1-3፤ ዮሐ. 15:20) ይህን ቪዲዮ ከተመለከትክ በኋላ ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ሞክር።
(1) የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቹ ምሥራቹን ለማስፋፋት ምን ዘዴዎችን ተጠቅመዋል? (2) በ1931 እና በ1935 በተደረጉ ጉልህ ስፍራ የሚሰጣቸው የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ ምን ማስታወቂያ ተነግሮ ነበር? (3) በኅዳር 1, 1939 መጠበቂያ ግንብ እትም ላይ ምን ወቅታዊ ሐሳብ ወጥቶ ነበር? (4) ወንድም ራዘርፎርድ በማዲሰን ስኩዌር “መንግሥት እና ሰላም” የተባለውን ንግግር እያቀረበ እያለ ምን እንደተከሰተ ግለጽ። (5) ወንድም ኖር ያቀረበው “ሰላም—ዘላቂ ሊሆን ይችላል?” የተሰኘው ንግግር ትኩረት የሚስብ የነበረው ለምንድን ነው? (6) የይሖዋ ምሥክሮች በ1942 የስብከቱ ሥራቸውን ለማስፋት ምን እቅዶች አወጡ? (7) በዩናይትድ ስቴትስ፣ በካናዳ እና በግሪክ ስለተደረጉ የፍርድ ቤት ሙግቶች አብራራ። (8) ጊልያድ የስብከቱ ሥራ እንዲስፋፋ ምን አስተዋጽኦ አድርጓል? (9) በ1946 የተጀመረው ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሥራ ምንድን ነው? ሥራው የተጀመረውስ ለምንድን ነው? (10) የይሖዋ ምሥክሮች፣ ምግባራቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉት የአቋም ደረጃዎች ጋር እንዲስማማ ለማድረግ ምን እርምጃዎች ወስደዋል? (11) በ1970ዎቹ ዓመታት፣ ድርጅቱ በአደረጃጀት ረገድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰውን ምሳሌ ይበልጥ እንዲከተል ለማድረግ ሲባል የተደረጉትን አንዳንድ ማስተካከያዎች ግለጽ። (12) ይህን ቪዲዮ መመልከትህ ይሖዋ ድርጅቱን እየመራው እንዳለና በእርግጥ የእሱ ድርጅት እንደሆነ ያለህን ግንዛቤ የጨመረልህ እንዴት ነው? (13) ይህ ቪዲዮ እንቅፋቶች ቢኖሩም በቅንዓት መስበክህን ለመቀጠል ያደረግከውን ቁርጥ ውሳኔ ያጠናከረልህ እንዴት ነው? (14) ይህን ቪዲዮ በመጠቀም ዘመዶቻችንን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችንንና ሌሎች ሰዎችን መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?
የይሖዋ ምሥክሮች በእያንዳንዱ ቀን፣ በታሪካቸው ላይ አሻራ ትቶ የሚያልፍ ሥራ ያከናውናሉ። በግለሰብ ደረጃ ስላደረግነው የአገልግሎት እንቅስቃሴ ታሪክ ወደፊት ምን ይል ይሆን? ወንድሞቻችን ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት ሁሉ እኛም በቅንዓት ‘ብርሃን ማብራታችንን’ እንቀጥል!—2 ቆሮ. 4:6