የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/13 ገጽ 1
  • ረዳት አቅኚ ትሆናለህ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ረዳት አቅኚ ትሆናለህ?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አገልግሎታችሁን ለማስፋት አሁኑኑ እቅድ አውጡ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • የመታሰቢያው በዓል የሚከበርበት ወቅት አስደሳች እንዲሆንላችሁ አድርጉ!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • 1,000 ረዳት አቅኚዎች ይፈለጋሉ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • የይሖዋን ግርማ በሰፊው አውጁ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
km 2/13 ገጽ 1

ረዳት አቅኚ ትሆናለህ?

1. የመታሰቢያው በዓል ሰሞን አገልግሎታችንን ለማስፋት ጥሩ አጋጣሚ ይከፍትልናል የምንለው ለምንድን ነው?

1 የመታሰቢያው በዓል በሚከበርበት ወቅት አገልግሎታችንን ለማስፋት ጥሩ አጋጣሚ እናገኛለን። ይህ ወቅት ይሖዋ፣ ልጁን ቤዛዊ መሥዋዕት በማድረግ ያሳየን ታላቅ ፍቅር ላይ የምናሰላስልበት ጊዜ ነው። (ዮሐ. 3:16) ይሖዋ ላደረገልን ነገር በጣም አመስጋኞች ነን፤ ይህ ደግሞ ስለ እሱና ለሰው ልጆች ስላደረገው ነገር ለሌሎች ለመንገር ያለን ፍላጎት እንዲጨምር ያደርጋል። (ኢሳ. 12:4, 5፤ ሉቃስ 6:45) በተጨማሪም በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የምናውቃቸውንና በክልላችን ያሉ ሰዎችን በልዩ ዘመቻ አማካኝነት እንጋብዛለን። ከዚያም በበዓሉ ላይ የተገኙ ሰዎችን ፍላጎት ለማዳበር ጥረት እናደርጋለን። በመጋቢት፣ በሚያዝያ ወይም በግንቦት ወር ረዳት አቅኚ በመሆን አገልግሎትህን ማስፋት ትችላለህ?

2. መጋቢት ወር ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል አመቺ ነው የምንለው ለምንድን ነው?

2 በመጋቢት ልዩ እንቅስቃሴ አድርጉ፦ መጋቢት ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል አመቺ ወር ነው። በዚህ ወር ረዳት አቅኚ የሚሆኑ 30 ወይም 50 ሰዓት ለማገልገል ግብ ሊያወጡ ይችላሉ። የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጉብኝት የሚያደርገው በመጋቢት ወር ከሆነ ረዳት አቅኚዎች ከዘወትርና ከልዩ አቅኚዎች ጋር በሚደረገው ስብሰባ ላይ እስከ መጨረሻው መካፈል ይችላሉ። በዚህ ዓመት ማክሰኞ፣ መጋቢት 26, 2013 (እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር መጋቢት 17, 2005) በሚከበረው የመታሰቢያ በዓል ላይ እንዲገኙ ሰዎችን ለመጋበዝ የሚደረገው ዘመቻ የሚጀምረው ቀደም ብሎ ማለትም ከመጋቢት 1 ጀምሮ ነው። በተጨማሪም የመጋቢት ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች አሉት። በዚህ ልዩ እንቅስቃሴ በሚደረግበት የመጋቢት ወር የበኩልህን ተሳትፎ ለማድረግ አሁኑኑ በጉዳዩ ላይ ለምን በቁም ነገር አታስብም?

3. አገልግሎታችንን ለማስፋት ዕቅድ ማውጣት የምንችለው እንዴት ነው?

3 አሁኑኑ ዕቅድ አውጣ፦ ረዳት አቅኚ ሆነህ ለማገልገል ፕሮግራምህን ማጤንና ማስተካከያ ማድረግ ያለብህ አሁን ነው። በዚህ ረገድ ቤተሰቦች መተባበራቸው በጣም አስፈላጊ ነው፤ በቤተሰቡ ግብ ላይ ለመወያየትና ፕሮግራም ለማውጣት በቤተሰብ አምልኮ ወቅት ጊዜ መድቡ። (ምሳሌ 15:22) ረዳት አቅኚ መሆን ካልቻልክ ተስፋ አትቁረጥ። አገልግሎት ስትወጣ ረጅም ሰዓት ለማገልገል ፕሮግራምህን ማስተካከል ትችል ይሆናል። ወይም በሳምንቱ መሃል ተጨማሪ ቀን አገልግሎት መውጣት ትችል ይሆናል።

4. በመጋቢት፣ በሚያዝያና በግንቦት ወራት የምናደርገውን እንቅስቃሴ ከፍ ማድረጋችን ምን ጥቅሞች ያስገኝልናል?

4 የአገልግሎት እንቅስቃሴያችንን በመጋቢት፣ በሚያዝያ እና በግንቦት ወራት ከፍ ካደረግን ይሖዋን በማገልገል እንዲሁም ለሌሎች በመስጠት የምናገኘው ደስታና እርካታ ይጨምራል። (ዮሐ. 4:34፤ ሥራ 20:35) ከሁሉም በላይ ደግሞ የራሳችንን ጥቅም መሥዋዕት ማድረጋችን ይሖዋን ያስደስተዋል።—ምሳሌ 27:11

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ