ወዲያውኑ መሄድ ያለብን ለምንድን ነው?
በስምሪት ስብሰባ ላይ ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን ጋር ስንገናኝ ከእነሱ ጋር ጨዋታ መጀመራችን ያለ ነገር ነው። ይሁን እንጂ ስብሰባው እንዳለቀ ወዲያውኑ ወደ ክልላችን መሄድ ይኖርብናል። የስብከቱ ሥራችን አጣዳፊ ነው። (2 ጢሞ. 4:2) እዚያ ብዙ ከቆየን ለአገልግሎት የምናውለው ጊዜ ያጥራል። ከእምነት ባልንጀሮቻችን ጋር አገልግሎት ላይ ስንሆን ከእነሱ ጋር የሚያንጽ ጭውውት የምናደርግበት ሰፊ አጋጣሚ እናገኛለን። ስምሪቱ ቦታ ከመቆየት ይልቅ ወዲያውኑ ወደ አገልግሎት መሄዳችን ትጉዎች እንዲሁም የይሖዋና የልጁ አገልጋዮች መሆናችንን ያረጋግጣል።—ሮም 12:11