የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 9/01 ገጽ 3
  • የጥያቄ ሣጥን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥያቄ ሣጥን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ውጤታማ የሆነ የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
  • ከመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች የተሟላ ጥቅም ማግኘት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
  • ከአሁን በኋላ የመስክ ስምሪት ስብሰባዎችን ለመምራት በዕለት ጥቅስ አንጠቀምም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
km 9/01 ገጽ 3

የጥያቄ ሣጥን

◼ በመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች ላይ መቅረብ ያለበት ምንድን ነው?

የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ ዓላማ ቀጥሎ በሚከናወነው የአገልግሎት እንቅስቃሴ ላይ እንድናተኩር መርዳት ነው። ስለሆነም የስብሰባው መሪ አበረታች፣ ተጨባጭና ተግባራዊ የሚሆን ሐሳብ ማስተላለፍ እንዲችል በደንብ ተዘጋጅቶ መምጣት ይኖርበታል። የዕለቱ ጥቅስ ከስብከቱ እንቅስቃሴ ጋር በቀጥታ የሚያያዝ ከሆነ ሊነበብና አጭር ውይይት ሊደረግበት ይችላል። ይሁን እንጂ ስብሰባው በይበልጥ በአገልግሎቱ ላይ በማተኮር በዕለቱ በመመስከሩ ሥራ የሚሰማሩት ሁሉ አገልግሎታቸውን ለመፈጸም በተሻለ ሁኔታ የተዘጋጁ እንዲሆኑ የሚረዳ መሆን አለበት።​—⁠2 ጢ⁠ሞ. 4:​5

ከመንግሥት አገልግሎታችን የተወሰዱ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ነጥቦችን አንስቶ በመወያየት ሁሉም በወቅቱ የትኛው ጽሑፍ እንደሚበረከትና እንዴትስ ማበርከት እንደሚችሉ ማስገንዘብ ይቻላል። በመጽሔት ቀን “መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?” ከሚለው ርዕስ አንድ አቀራረብ በሠርቶ ማሳያ ማቅረብ ይቻላል። ለሌሎች ዘመቻዎች ደግሞ ከማመራመር መጽሐፍ ለጉባኤው የአገልግሎት ክልል ተስማሚ በሆኑ አንድ ወይም ሁለት መግቢያዎች ላይ መወያየት ይቻላል። ለምሳሌ ያህል ሰዎችን ስናነጋግር መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል፣ ውይይት የሚያስቆሙ ሐሳቦች ሲሰነዘሩ እንዴት እንደምንመልስ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ለማስጠናት እንዴት እንደምንጋብዝ ወይም ፍላጎት ያሳዩትን እንዴት ተከታትለን መርዳት እንደምንችል ከመሳሰሉት የአገልግሎቱ ዘርፎች መካከል በአንዱ መወያየት ወይም ሠርቶ ማሳያ ማቅረብ ይቻላል።

መመደብን፣ የአገልግሎት ክልል መስጠትንና ጸሎትን ጨምሮ የአገልግሎት ስምሪት ስብሰባው ከ10 እስከ 15 ደቂቃ መብለጥ የለበትም። ስብሰባው ሲያበቃ የተገኙት ሁሉ ከማን ጋር እንደተመደቡና የት እንደሚያገለግሉ ማወቅ የሚኖርባቸው ሲሆን ወዲያው ወደክልላቸው መሄድ አለባቸው። ከስብሰባው አጭርነት አኳያ ሁሉም በሰዓቱ መገኘታቸው አስፈላጊ ነው። ስብሰባውን የሚመራው ወንድም ክልል ላልወሰዱ አስፋፊዎች የሚሰጠው ከቤት ወደ ቤት የሚሸፈን በቂ የአገልግሎት ክልል ሊኖረው ይገባል። የአገልግሎት ስምሪት ስብሰባው እንደ መጠበቂያ ግንብ ጥናት ያለ የጉባኤ ስብሰባ ተከትሎ የሚደረግ ከሆነ የሚሸፍነው ጊዜ አጠር ማለት አለበት። ቀደም ሲል ጥሩ ቅዱስ ጽሑፋዊ ውይይት ስለተደረገ የዕለቱን ጥቅስ መወያየት አስፈላጊ አይደለም።

የአገልግሎት ስምሪት ስብሰባውን እንዲመሩ ብቃት ያላቸው የተጠመቁ ወንድሞች አስቀድመው ሊመደቡ ይገባል። ስብሰባውን የሚመሩ ብቃት ያላቸው ወንድሞች የማይኖሩበት አጋጣሚ በሚፈጠርበት ጊዜ ከተጠመቁ እህቶች መካከል የትኛዋ እህት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ልትመራ እንደምትችል ሽማግሌዎች አስቀድመው ይወስናሉ። እህት እንደተቀመጠች ሆና አጠር ያለ ሐሳብ በመስጠት በዕለቱ ጥቅስ ወይም ከመስክ አገልግሎት ጋር በሚያያዙ ነጥቦች ላይ ውይይት ልትከፍት ትችላለች። በዚህ ጊዜ ራስዋን መከናነብ ይኖርባታል።

የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች እንድንበረታታና በአገልግሎቱ ለመካፈል የታጠቅን እንድንሆን የሚረዱን ግሩም አጋጣሚዎች ናቸው። መሪው በደንብ ከተዘጋጀ ሁሉም ከስብሰባው በይበልጥ ይጠቀማሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ