ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኢሳይያስ 29-33
“ንጉሥ ለጽድቅ ይነግሣል”
ንጉሡ ኢየሱስ መንጋውን የሚንከባከቡ “ገዢዎች” ወይም ሽማግሌዎች ሰጥቶናል
ሽማግሌዎች “ከውሽንፍር እንደ መሸሸጊያ” በመሆን መንጋውን ከሚያጋጥመው ስደትና ተስፋ መቁረጥ ለመጠበቅ ጥረት ያደርጋሉ
ሽማግሌዎች ‘ውኃ በሌለበት ምድር እንዳለ ጅረት’ በመሆን በመንፈሳዊ ለተጠሙ ሰዎች ያልተበረዘውንና የጠራውን የእውነት ውኃ በመስጠት እንዲረኩ ያደርጋሉ
ሽማግሌዎች ‘በደረቅ ምድር እንዳለ ትልቅ ቋጥኝ ጥላ’ በመሆን መንጋው እረፍት እንዲያገኝ ያደርጋሉ፤ ይህንንም የሚያደርጉት መንፈሳዊ መመሪያና ማበረታቻ በመስጠት ነው