ክርስቲያናዊ ሕይወት
አቅኚ በመሆን ይሖዋን አወድሱት
እስራኤላውያን ይሖዋን ለማወደስ የሚያነሳሱ ግሩም ምክንያቶች ነበራቸው። ከግብፅ ነፃ ያወጣቸው ከመሆኑም ሌላ ከፈርዖን ሠራዊት ታድጓቸዋል! (ዘፀ 15:1, 2) ይሖዋ አሁንም ለሕዝቡ መልካም ነገሮችን ያደርግላቸዋል። ታዲያ አመስጋኝነታችንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?—መዝ 116:12
አንዱ መንገድ በረዳት ወይም በዘወትር አቅኚነት መካፈል ነው። በአቅኚነት ለማገልገል ፍላጎት እንዲያድርባችሁም ሆነ ኃይል እንዲሰጣችሁ ይሖዋን በጸሎት ጠይቁት። (ፊልጵ 2:13) ብዙዎች መጀመሪያ ላይ ረዳት አቅኚ መሆንን ይመርጣሉ። በመጋቢትና በሚያዝያ እንዲሁም የወረዳ የበላይ ተመልካቹ በሚጎበኝበት ወር 30 ሰዓት ወይም 50 ሰዓት ለማገልገል መምረጥ ትችላላችሁ። ረዳት አቅኚነት የሚያስገኘውን ደስታ ካጣጣማችሁ በኋላ የዘወትር አቅኚ ሆናችሁ ለማገልገል ራሳችሁን ማቅረብ ትችሉ ይሆናል። ሙሉ ቀን የሚሠሩ ወይም የጤና እክል ያለባቸው ወንድሞችና እህቶች እንኳ የዘወትር አቅኚ ሆነው ማገልገል ችለዋል። (mwb16.07 8) በእርግጥም ይሖዋ ሊወደስ ይገባዋል፤ በመሆኑም እሱን ለማወደስ የቻልነውን ያህል ጥረት ማድረግ ይኖርብናል!—1ዜና 16:25
በሞንጎሊያ የሚገኙ ሦስት እህትማማቾች የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ሦስቱ እህትማማቾች የዘወትር አቅኚ ለመሆን የትኞቹን ተፈታታኝ ሁኔታዎች መወጣት አስፈልጓቸዋል?
ምን በረከቶችን አግኝተዋል?
በዘወትር አቅኚነት መካፈል ሲጀምሩ የትኞቹ የአገልግሎት መስኮች ተከፍተውላቸዋል?
የእነሱ ምሳሌ በሌሎች ላይ ምን ተጽዕኖ አሳድሯል?