ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘሌዋውያን 6–7
የአመስጋኝነት መግለጫ
በእስራኤል ይቀርቡ የነበሩት የኅብረት መሥዋዕቶች በጸሎታችንና በምግባራችን ለይሖዋ ያለንን አመስጋኝነት መግለጻችን ያለውን አስፈላጊነት ያስታውሱናል።—ፊልጵ 4:6, 7፤ ቆላ 3:15
በምንጸልይበት ጊዜ የትኞቹን ነገሮች ለይተን በመጥቀስ ይሖዋን ልናመሰግነው እንችላለን?—1ተሰ 5:17, 18
አመስጋኝነት ማሳየታችን ምን ጥቅም ያስገኝልናል?
አንድ ሰው “ከአጋንንት ማዕድ” ሊካፈል የሚችለው እንዴት ነው? ይህስ ለይሖዋ አድናቆት እንደሌለው የሚያሳየው እንዴት ነው?—1ቆሮ 10:20, 21