የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w96 12/15 ገጽ 30
  • ታስታውሳለህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታስታውሳለህን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘የመጽናናት ሁሉ አምላክ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • የኢየሱስ መምጣት ወይስ የኢየሱስ መገኘት?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • እውነተኛ መጽናኛ ማግኘት የሚቻለው ከየት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • መጽናናትን ለማግኘት ይሖዋን ተስፋ አድርግ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
w96 12/15 ገጽ 30

ታስታውሳለህን?

በቅርብ ጊዜ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች አንብበሃቸዋልን? ከሆነ የሚከተሉትን ሐሳቦች ይበልጥ የማወቅ ፍላጎት የሚቀሰቅሱ ሆነው ልታገኛቸው ትችላለህ፦

◻ በማቴዎስ 24:3, 27, 37, 39 ላይ የተሠራበት ፓሩስያ የተባለው የግሪክኛ ቃል ትርጉም ምንድን ነው?

የቫይን ኤክስፖዚተሪ ዲክሽነሪ ኦቭ ኒው ቴስታመንት ዎርድስ እንዲህ ይላል፦ “ፓሩስያ . . . መምጣትንም ሆነ ከመጡ በኋላ አብሮ መሆንን ያመለክታል።” ስለዚህ መምጣት ብቻ ሳይሆን ከመጡ በኋላ ያለው የቆይታ ጊዜ ነው።—8/15፣ ገጽ 11

◻ በመጀመሪያው መቶ ዘመን ‘ሥጋ ለባሾች’ እንዲድኑ ‘ቀኖቹ ያጠሩት’ እንዴት ነው? ይህ በከፍተኛ ደረጃ የሚፈጸመውስ እንዴት ነው? (ማቴዎስ 24:22)

በ66 እዘአ ሮማውያን ባልተጠበቀ አኳኋን አፈግፍገው ወደ ኋላ መመለሳቸው ክርስቲያን ‘ሥጋ ለባሾች’ እንዲድኑ አስችሏቸዋል። በተመሳሳይም ወደፊት በታላቂቱ ባቢሎን ላይ የሚደርሰው ጥቃት በሆነ መንገድ እንደሚያጥር እንጠብቃለን። ይህም በመሆኑ ቅቡዓን ክርስቲያኖችና ጓደኞቻቸው ሊመጣ ከሚችለው ጥፋት ይድናሉ።—8/15፣ ገጽ 18-20

◻ አንድ ሰው ከመታሰቢያው ቂጣና ወይን መካፈል ቢጀምር ወይም ቢያቆም የሚሰማን ስሜት ምን መሆን ይኖርበታል?

ሌሎች ክርስቲያኖች ጉዳዩ ሊያሳስባቸው አይገባም። ኢየሱስ “መልካሙ እረኛ እኔ ነኝ። በጎቼንም አውቃቸዋለሁ” ብሏል። በተመሳሳይም ይሖዋ መንፈሳዊ ልጆች አድርጎ የመረጣቸውን ለይቶ እንደሚያውቅ ምንም አያጠራጥርም። (ዮሐንስ 10:14፤ ሮሜ 8:16, 17)—8/15፣ ገጽ 31

◻ የሙሴ ሕግ የተሰጠበት ዋና ዓላማ ምን ነበር?

በመጀመሪያ ደረጃ እስራኤላውያን ከኃጢአተኛ ሁኔታቸው የሚቤዣቸው መሲሕ እንደሚያስፈልጋቸው አስተምሯቸዋል። (ገላትያ 3:24) በተጨማሪም ሕጉ አምላካዊ ፍርሃትንና ታዛዥነትን አስተምሯቸዋል። ከዚህም በላይ በዙሪያቸው የነበሩት አሕዛብ ከሚፈጽሟቸው ወራዳ ልማዶች የተለዩ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። (ዘሌዋውያን 18:24, 25)—9/1፣ ገጽ 9

◻ የአዲሱ ቃል ኪዳን ዓላማ ምንድን ነው? (ኤርምያስ 31:31-34)

ሁሉም የሰው ልጆች የሚባረኩበት የነገሥታትና የካህናት ብሔር ማስገኘት ነው። (ዘጸአት 19:6፤ 1 ጴጥሮስ 2:9፤ ራእይ 5:10)—9/1፣ ገጽ 14, 15

◻ ይቅርታ የመጠየቅን ልማድ ማዳበር ያለብን ለምንድን ነው?

ይቅርታ መጠየቅ ባለፍጽምና ምክንያት የሚፈጠር መቆሳሰል የሚያስከትለው ሥቃይ እንዲቀንስ ያደርጋል፤ መቃቃርንም ለማስወገድ ይረዳል። ይቅርታ በጠየቅን ቁጥር ትሕትናን እንማራለን፤ እንዲሁም ወደፊት ለሌሎች ሰዎች ስሜት ይበልጥ እንድንጠነቀቅ ያደርገናል።—9/15፣ ገጽ 24

◻ በኖኅ ዘመን የደረሰው ዓለም አቀፍ የጥፋት ውኃ በታሪክ የተረጋገጠ ሐቅ ነውን?

አዎን። ከአሜሪካ አንሥቶ እስከ አውስትራሊያ በዓለም ዙሪያ የተለያዩ ሕዝቦች ስለ ጥፋት ውኃ የሚተርኩ አፈ ታሪኮች አሏቸው። ይህ ሐሳብ በሰፊው መሰራጨቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተዘገበው ዓለም አቀፍ የጥፋት ውኃ በትክክል ለመከሰቱ ተጨማሪ ማስረጃ ነው። (ዘፍጥረት 7:11-20)—9/15፣ ገጽ 25

◻ እንግዳ ተቀባይ መሆን ማለት ምን ማለት ነው? (ሮሜ 12:13)

“እንግዳ ተቀባይ” መሆን ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል “ፍቅር” እና “እንግዳ” የሚል ትርጉም ባላቸው ሁለት የግሪክኛ ቃላት ጥምረት የተመሠረተ ቃል ነው። ስለዚህ እንግዳ መቀበል ማለት በመሠረቱ “እንግዶችን መውደድ” ማለት ነው። ይሁን እንጂ እንግዳ ተቀባይ መሆን በግዴታ ስሜት ተነሣስቶ ከሚደረገው በመሠረተ ሥርዓት ላይ ከተመሠረተው ፍቅር አልፎ የሚሄድ ነው። በልባዊ ፍቅር፣ መውደድና ጓደኝነት ላይ የተመሠረተ ባሕርይ ነው።—10/1፣ ገጽ 9

◻ ጳውሎስ በመጀመሪያው የቆሮንቶስ መልእክት ምዕራፍ 7 ላይ ጋብቻንና ነጠላነትን አስመልክቶ ያቀረበው ሐሳብ ዋነኛ ፍሬ ነገር ምንድን ነው?

ማግባት ምንም ስሕተት የሌለበትና በአንዳንድ ሁኔታዎችም ለአንዳንዶች ጥሩ ነው። ሆኖም አሳቡ ብዙም ሳይከፋፈል ይሖዋን ለማገልገል ለሚፈልግ ክርስቲያን ወንድ ወይም ለምትፈልግ ክርስቲያን ሴት ነጠላነት ጠቃሚ እንደሆነ አይካድም።—10/15፣ ገጽ 13

◻ አንድ ሽማግሌ ‘ለእርሱ ለሆኑት የሚያስፈልጋቸውን የሚያቀርበው’ እንዴት ነው? (1 ጢሞቴዎስ 5:8)

አንድ ሽማግሌ ‘የእርሱ የሆኑት’ ሚስቱና ልጆቹ በቁሳዊ፣ በመንፈሳዊና በስሜት ‘የሚያስፈልጋቸውን ማቅረብ’ ይኖርበታል።—10/15፣ ገጽ 22

◻ ይሖዋ ለአገልጋዮቹ መጽናናት የሚሰጣቸው እንዴት ነው?

የአምላክ ቅዱስ መንፈስ እንደ “አጽናኝ” ሆኖ ያገለግላል። (ዮሐንስ 14:16 የአዓት የግርጌ ማስታወሻ) አምላክ ማጽናኛ የሚሰጥበት ሌላው መንገድ በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ነው። (ሮሜ 15:4) አምላክ እያንዳንዳችን የሚያስፈልገንን ነገር ስለሚያውቅ ጳውሎስ ቲቶ በነገረው ነገር እንደተጽናና ሁሉ እኛም አንዳችን ለሌላው የመጽናኛ ምንጭ እንድንሆን ሊጠቀምብን ይችላል። (2 ቆሮንቶስ 7:11-13)—11/1፣ ገጽ 10, 12

◻ ጳውሎስ በ2 ቆሮንቶስ 1:3 ላይ ይሖዋን “የርኅራኄ አባት” ሲል የገለጸው ነገር ምን ያመለክታል?

“የርኅራኄ አባት” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ስም በሌላ ሰው ላይ በደረሰ መከራ ሳቢያ ማዘንን ከሚገልጽ ቃል የመጣ ነው። ስለዚህ ጳውሎስ አምላክ መከራ ለሚደርስባቸው ታማኝ አገልጋዮቹ ሁሉ የሚሰማውን የርኅራኄ ስሜት ገልጿል።—11/1፣ ገጽ 13

◻ እስራኤላውያን በዓመታዊው የስርየት ቀን የሚጾሙት ጾም ምን ያከናውን ነበር? (ዘሌዋውያን 16:29-31፤ 23:27)

የእስራኤል ሕዝብ በስርየት ቀን የሚጾሙት ጾም ኃጢአተኛነታቸውንና ቤዛ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ይበልጥ እንዲገነዘቡ ያደርግ ነበር። በዚህ ጾም አማካኝነት ስለ ኃጢአታቸው የተሰማቸውን ሐዘን ከመግለጻቸውም በላይ በአምላክ ፊት ንስሐ መግባታቸውን ያሳዩ ነበር።—11/15፣ ገጽ 5

◻ ወጣቶች “ፈጣሪህን አስብ” ተብለው የታዘዙት ትእዛዝ ምን ትርጉም አለው? (መክብብ 12:1)

አንድ ምሁር “አስብ” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል ብዙውን ጊዜ “መውደድና ከትውስታ ጋር ተከትሎ የሚመጣውን ድርጊት” ያመለክታል ይላሉ። ስለዚህ ይህ ትእዛዝ ስለ ይሖዋ ማሰብ ማለት ብቻ አይደለም። ድርጊትን ማለትም እሱን የሚያስደስተውን ነገር ማድረግን ይጨምራል።—12/1፣ ገጽ 16

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ