-
መስከረም 5 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራምየመንግሥት አገልግሎት—2011 | ነሐሴ
-
-
መስከረም 5 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መስከረም 5 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 28 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 17 አን. 1-7 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 119 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ መዝሙር 119:49-72 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ቅዱሳን መጻሕፍት ይሖዋን እንድንፈራ የሚያበረታቱን ለምንድን ነው?—ዘዳ. 5:29 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ የአምላክ መንግሥት ሙታንን ያስነሳል—rs ገጽ 231 አን. 1-4 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። ሥራ 5:17-42ን አንብብና ተወያዩበት። ይህ ዘገባ በአገልግሎታችን ሊጠቅመን የሚችለው እንዴት እንደሆነ ግለጽ።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ በቤተሰብ ደረጃ ለአገልግሎት ዝግጅት አድርጉ። በቃለ ምልልስና በሠርቶ ማሳያ የሚቀርብ። በቤተሰብ አምልኮ ወቅት ለአገልግሎት ዝግጅት የሚያደርጉት እንዴት እንደሆነ ለአንድ ባልና ሚስት እንዲሁም ልጆች ላሉት አንድ ቤተሰብ ቃለ ምልልስ አድርግ። ከዚያም አንደኛው ቤተሰብ ለአገልግሎት ዝግጅት ሲያደርግ የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ።
መዝሙር 41 እና ጸሎት
-
-
ማስታወቂያዎችየመንግሥት አገልግሎት—2011 | ነሐሴ
-
-
ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ነሐሴ፦ ብሮሹሮች። ቀጥሎ ከተጠቀሱት ብሮሹሮች ውስጥ ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል፦ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ፣ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ነቅተህ ጠብቅ!፣ ሪል ፌይዝ—ዩር ኪ ቱ ኤ ሃፒ ላይፍ (ለሙስሊሞች)፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ዘ ሮድ ቱ ኤቨርላስቲንግ ላይፍ—ሃቭ ዩ ፋውንድ ኢት?፣ ሕይወት የተገኘው በፍጥረት ነው?፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው—እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? እና የምትወዱት ሰው ሲሞት። መስከረም፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ሰዎችን በምታነጋግሩበት በመጀመሪያው ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ጥቅምት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ፍላጎት ያለው ሰው ስታገኙ እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ? የተባለውን ትራክት አበርክቱለት፤ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ኅዳር፦ መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው? ከዚህ ብሮሹር ጋር ወይም ደግሞ በዚህ ብሮሹር ፋንታ በሐምሌና በነሐሴ ወር ያበረከትነውን ማንኛውንም ባለ 32 ገጽ ብሮሹር መጠቀም ይቻላል።
◼ ጂሆቫስ ዊትነስስ—ፌይዝ ኢን አክሽን ፓርት 1፣ አውት ኦቭ ዳርክነስ (የይሖዋ ምሥክሮች ያሳዩት በተግባር የተደገፈ እምነት፣ ክፍል 1፦ ከጨለማ መውጣት) እና ዎንደርስ ኦቭ ክርኤሽን ሪቪል ጎድስ ግሎሪ (አስደናቂ የፍጥረት ሥራዎች የአምላክን ክብር ይገልጣሉ) የተሰኙትን ሁለት ፊልሞች በቅርቡ በምናደርጋቸው የአገልግሎት ስብሰባ ክፍሎች ላይ እንከልሳለን። ፊልሞቹን ማግኘት የምትፈልጉ ከሆነ በተቻለ ፍጥነት በጉባኤው በኩል ማዘዝ ይኖርባችኋል።
-
-
የአቀራረብ ናሙናዎችየመንግሥት አገልግሎት—2011 | ነሐሴ
-
-
የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“የተለያየ እምነትና ዜግነት ያላቸው ሰዎች በየቀኑ ይጸልያሉ። አምላክ ሁሉንም ጸሎቶች የሚሰማና መልስ የሚሰጥ ይመስልዎታል?” ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም የመስከረም 1ን መጠበቂያ ግንብ ስጠውና ገጽ 16 ላይ በሚገኘው የመጀመሪያው ንዑስ ርዕስ ሥር ባለው ሐሳብ ላይ ተወያዩ፤ በተጨማሪም እዚያ ላይ ከተጠቀሱት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ አንዱን አንብቡ። መጽሔቶቹን እንዲወስድ ከጋበዝከው በኋላ በቀጣዩ ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1
የመጽሔቱን የፊት ገጽ አሳየውና እንዲህ በማለት ጠይቀው፦ “እርስዎ ለዚህ ጥያቄ ምን መልስ ይሰጣሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚል ልብ ይበሉ። [1 ዮሐንስ 5:19ን አንብብ።] ይህ ጥቅስ እንደሚናገረው ‘ክፉው’ ወይም ዲያብሎስ ዓለምን እየገዛ ነው። ሆኖም ይህ አንዳንድ ጥያቄዎችን ያስነሳል። ዲያብሎስ የመጣው ከየት ነው? የራሱ ሕልውና ያለው አካል ነው? አምላክ ዓለምን እንዲገዛ የሚፈቅድለትስ እስከ መቼ ነው? ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ምን ሐሳብ እንደሚሰጥ ይናገራል።”
ንቁ! መስከረም
“ዛሬ ብዙ ሰዎች ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ያሉባቸው ችግሮች ያስጨንቋቸዋል። መሠረታዊ ፍላጎቶችን ማሟላት ይህን ያህል ከባድ የሆነው ለምን ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ብዙ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ጠቃሚ ምክሮችን ተግባራዊ በማድረግ ገንዘባቸውን በአግባቡ መጠቀም ችለዋል። [በገጽ 8 እና 9 ላይ ከሚገኙት ጥቅሶች መካከል አንዱን አንብብ።] ይህ መጽሔት ዕዳቸውን ለመክፈል ለተቸገሩ ሰዎች የሚሆኑ ጠቃሚ ሐሳቦችን ይዟል።”
-
-
የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎችየመንግሥት አገልግሎት—2011 | ነሐሴ
-
-
የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በሰማይ ያለውን አፍቃሪ አባታችንን ለማወደስ ከፍተኛ የአገልግሎት እንቅስቃሴ ያደረግንበት የሚያዝያ ወር በጣም አስደሳች ነበር! በዚህ ወር ትልልቅ ስብሰባዎች የተካሄዱ ቢሆንም በአገሪቱ ካሉት አስፋፊዎች መካከል 61 በመቶ የሚሆኑት አቅኚ ሆነው አገልግለዋል። ከእነዚህ መካከል 3,900 የሚሆኑት ረዳት አቅኚዎች የነበሩ ሲሆን ይህም ቀደም ሲል ከተመዘገበው ከፍተኛ ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ከእጥፍ በላይ ነው። ብዙዎች ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ሌሎች ደግሞ ከረጅም ጊዜ በኋላ ረዳት አቅኚዎች ሆነው ማገልገል በመቻላቸው አመስጋኞች ሆነዋል። በዚህ ወር 9,128 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ያገኘን ከመሆኑም በተጨማሪ በአገልግሎት ሰዓት፣ በመጽሔትና በተመላልሶ መጠየቅ ረገድ አዲስ ከፍተኛ ቁጥር ተመዝግቧል። በመሆኑም በሚያዝያ ወር መጠነ ሰፊ ምሥክርነት የተሰጠ ሲሆን ፍላጎት ያሳዩትን በርካታ ሰዎች ተመልሰን ሄደን ‘ማጠጣት’ ይጠበቅብናል።
-