ክርስቲያናዊ ሕይወት
በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር በክልላችን ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በሙሉ ማነጋገር
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? የዘካርያስ ትንቢት ከብሔራት ቋንቋዎች ሁሉ የተውጣጡ ሰዎች ለምሥራቹ ጥሩ ምላሽ እንደሚሰጡ ይናገራል። (ዘካ 8:23) ሆኖም ለእነዚህ ሰዎች ምሥራቹን የሚነግራቸው ማን ነው? (ሮም 10:13-15) በክልላችን ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች በሙሉ ምሥራቹን የመናገር መብትና ኃላፊነት ተሰጥቶናል።—od 84 አን. 10-11
ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
ተዘጋጁ። ክልላችሁ ውስጥ የሌላ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ሰዎች ያጋጥሟችኋል? JW Language የተባለውን አፕሊኬሽን በመጠቀም ቀለል ያለ መግቢያ መዘጋጀት ትችላላችሁ። ወይም ደግሞ በተንቀሳቃሽ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያችሁ በመጠቀም ግለሰቡ ከjw.org ላይ በራሱ ቋንቋ መረጃ ማግኘት የሚችለው እንዴት እንደሆነ ማሳየት ትችላላችሁ
አስተዋይ ሁኑ። ከቤት ወደ ቤት ስታገለግሉ በአካባቢው ለሚያልፉ ወይም መኪና ውስጥ ቁጭ ብለው ለሚጠብቁ ሰዎች ለመመሥከር የሚያስችል አጋጣሚ እንዳያልፋችሁ ጥረት አድርጉ። በአደባባይ ምሥክርነት ስትካፈሉ ደግሞ በስብከት ሥራችሁ ላይ ትኩረት አድርጉ
ትጉ ሁኑ። ቤት ያልተገኙ ሰዎችን በድጋሚ ተመልሳችሁ ለማግኘት ጥረት አድርጉ። የምታገለግሉበትን ሰዓት ወይም ቀን በመቀያየር ከእያንዳንዱ ቤት ቢያንስ አንድ ሰው ለማግኘት ሞክሩ። አንዳንድ የቤት ባለቤቶችን ማግኘት የሚቻለው በደብዳቤ፣ በስልክ ወይም ከመንገድ ወደ መንገድ በሚሰጥ ምሥክርነት ሊሆን ይችላል
ተከታትላችሁ እርዱ። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን በሙሉ ሳትዘገዩ ተመልሳችሁ አነጋግሩ። ግለሰቡ የሚናገረው ቋንቋ ሌላ ከሆነ፣ በራሱ ቋንቋ ሊያነጋግረው የሚችል ሰው ለማግኘት ሞክሩ። ሆኖም የእሱን ቋንቋ ከሚናገር አስፋፊ ጋር እስኪገናኝ ድረስ ለግለሰቡ ተመላልሶ መጠየቅ ማድረጋችሁን መቀጠል ይኖርባችኋል።—od 94 አን. 39-40
“እስከ ምድር ዳር ድረስ” መስበክ የተባለውን ቪዲዮ ተመልከቱ፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሩ፦
ወንድሞችና እህቶች በገለልተኛ ክልል ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ለማነጋገር ምን ዝግጅት አድርገዋል? (1ቆሮ 9:22, 23)
የትኞቹን ተፈታታኝ ሁኔታዎች መቋቋም አስፈልጓቸዋል?
ምን በረከቶችን አግኝተዋል?
በክልላችሁ ውስጥ በተቻለ መጠን ብዙ ሰዎችን ለማግኘት ምን ጥረት ማድረግ ትችላላችሁ?