የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 38
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መዝሙር የመጽሐፉ ይዘት

      • ንስሐ የገባ ሰው ያቀረበው ጸሎት

        • “በጭንቀት ተዋጥኩ፤ አንገቴንም ደፋሁ” (6)

        • ይሖዋ እሱን የሚጠባበቁ ሰዎችን ይሰማል (15)

        • ‘ኃጢአቴ አስጨንቆኝ ነበር’ (18)

መዝሙር 38:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 10:24

መዝሙር 38:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 32:4

መዝሙር 38:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በሥጋዬ ላይ ጤነኛ ቦታ የለም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 6:2፤ 41:4፤ 51:8

መዝሙር 38:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕዝራ 9:6፤ መዝ 40:12

መዝሙር 38:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “መላ ወገቤ ተቃጠለ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 38:3

መዝሙር 38:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እጮኻለሁ።”

መዝሙር 38:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 6:7

መዝሙር 38:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 16:7፤ መዝ 62:4

መዝሙር 38:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 16:11
  • +መዝ 39:2, 9

መዝሙር 38:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 16:12፤ መዝ 123:2
  • +መዝ 138:3

መዝሙር 38:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 77:2

መዝሙር 38:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 32:5
  • +መዝ 51:3

መዝሙር 38:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ሕያዋንና።”

  • *

    “ይሁንና ከመሬት ተነስተው የሚጠሉኝ ብዙ ናቸው” ማለትም ሊሆን ይችላል።

መዝሙር 38:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 22:11፤ 35:22

መዝሙር 38:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 27:1፤ 62:2፤ ኢሳ 12:2

ተዛማጅ ሐሳብ

መዝ. 38:1ኤር 10:24
መዝ. 38:2መዝ 32:4
መዝ. 38:3መዝ 6:2፤ 41:4፤ 51:8
መዝ. 38:4ዕዝራ 9:6፤ መዝ 40:12
መዝ. 38:7መዝ 38:3
መዝ. 38:10መዝ 6:7
መዝ. 38:122ሳሙ 16:7፤ መዝ 62:4
መዝ. 38:132ሳሙ 16:11
መዝ. 38:13መዝ 39:2, 9
መዝ. 38:152ሳሙ 16:12፤ መዝ 123:2
መዝ. 38:15መዝ 138:3
መዝ. 38:17መዝ 77:2
መዝ. 38:18መዝ 32:5
መዝ. 38:18መዝ 51:3
መዝ. 38:21መዝ 22:11፤ 35:22
መዝ. 38:22መዝ 27:1፤ 62:2፤ ኢሳ 12:2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መዝሙር 38:1-22

መዝሙር

የዳዊት ማህሌት፤ ማስታወሻ ሆኖ የሚያገለግል።

38 ይሖዋ ሆይ፣ በቁጣህ አትውቀሰኝ፤

ተናደህም አታርመኝ።+

 2 ፍላጻዎችህ እስከ ውስጥ ድረስ ወግተውኛልና፤

እጅህም ተጭኖኛል።+

 3 ከቁጣህ የተነሳ መላ ሰውነቴ ታመመ።*

ከኃጢአቴም የተነሳ አጥንቶቼ ሰላም የላቸውም።+

 4 የፈጸምኳቸው ስህተቶች በራሴ ላይ ያንዣብባሉና፤+

እንደ ከባድ ሸክም በጣም ከብደውኛል።

 5 ከሞኝነቴ የተነሳ

ቁስሌ ሸተተ፤ ደግሞም አመረቀዘ።

 6 በጭንቀት ተዋጥኩ፤ አንገቴንም ደፋሁ፤

ቀኑን ሙሉ በሐዘን ተውጬ እመላለሳለሁ።

 7 ውስጤ ተቃጠለ፤*

መላ ሰውነቴ ታመመ።+

 8 ደነዘዝኩ፤ ፈጽሞም ደቀቅኩ፤

በጭንቀት ከተዋጠው ልቤ የተነሳ እጅግ እቃትታለሁ።*

 9 ይሖዋ ሆይ፣ ምኞቴ ሁሉ በፊትህ ነው፤

የማሰማው ሲቃም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።

10 ልቤ በኃይል ይመታል፤ ጉልበቴ ከድቶኛል፤

የዓይኔም ብርሃን ጠፍቷል።+

11 ከቁስሌ የተነሳ ወዳጆቼና ጓደኞቼ ሸሹኝ፤

በቅርብ የሚያውቁኝ ሰዎችም ከእኔ ራቁ።

12 ሕይወቴን* የሚሹ ሰዎች ወጥመድ ዘረጉብኝ፤

እኔን መጉዳት የሚፈልጉም ስለ ጥፋት ያወራሉ፤+

ቀኑን ሙሉ ተንኮል ሲሸርቡ ይውላሉ።

13 እኔ ግን እንደ ደንቆሮ አልሰማቸውም፤+

እንደ ዱዳም አፌን አልከፍትም።+

14 መስማት እንደማይችል፣

በአፉም የመከላከያ መልስ እንደማይሰጥ ሰው ሆንኩ።

15 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን በተስፋ ተጠባብቄአለሁና፤+

ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ አንተም መልስ ሰጥተኸኛል።+

16 “በእኔ ውድቀት አይፈንድቁ፤

ወይም እግሬ ቢንሸራተት በእኔ ላይ አይኩራሩ” ብያለሁና።

17 ልወድቅ ምንም አልቀረኝም ነበርና፤

ሥቃዬም ከእኔ አልተለየም።+

18 በደሌን ተናዘዝኩ፤+

ኃጢአቴም አስጨንቆኝ ነበር።+

19 ይሁንና ጠላቶቼ ብርቱዎችና* ኃያላን ናቸው፤*

ያላንዳች ምክንያት የሚጠሉኝ ተበራከቱ።

20 ላደረግኩት መልካም ነገር ክፉ መለሱልኝ፤

መልካም የሆነውን ነገር በመከተሌ ይቃወሙኝ ነበር።

21 ይሖዋ ሆይ፣ አትተወኝ።

አምላክ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።+

22 አዳኜ ይሖዋ ሆይ፣

እኔን ለመርዳት ፍጠን።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ