የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 18
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • በሸክላ ሠሪው እጅ ውስጥ ያለ ጭቃ (1-12)

      • ይሖዋ ለእስራኤል ጀርባውን ሰጠ (13-17)

      • በኤርምያስ ላይ የተጠነሰሰ ሴራና እሱ ያቀረበው ልመና (18-23)

ኤርምያስ 18:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 19:1

ኤርምያስ 18:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ሸክላ ሠሪው በዓይኑ ፊት ትክክል መስሎ በታየው መንገድ።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 4/2017፣ ገጽ 1

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/1/1999፣ ገጽ 22

ኤርምያስ 18:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 9:20, 21

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 4/2017፣ ገጽ 1

    የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ፣

    4/2017፣ ገጽ 3

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/1/1999፣ ገጽ 22

ኤርምያስ 18:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 1:10፤ 12:14፤ 25:9፤ 45:4

ኤርምያስ 18:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ላመጣው ባሰብኩት ጥፋት እጸጸታለሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 8:33, 34፤ መዝ 106:45፤ ኤር 7:3፤ 26:3፤ ሕዝ 18:21፤ ኢዩ 2:13፤ ዮናስ 3:5, 10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 4/2017፣ ገጽ 1

    የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ፣

    4/2017፣ ገጽ 3

ኤርምያስ 18:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ባሰብኩት መልካም ነገር እጸጸታለሁ።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 4/2017፣ ገጽ 1

ኤርምያስ 18:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እየሠራሁ ነው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 1:16፤ ሕዝ 18:23

ኤርምያስ 18:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 2:25
  • +ዘዳ 29:19, 20፤ ኤር 7:24

ኤርምያስ 18:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 2:13

ኤርምያስ 18:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ባልተሠሩ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 2:19፤ 3:21
  • +ኤር 10:14, 15
  • +ኤር 6:16

ኤርምያስ 18:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:33፤ ሕዝ 6:14
  • +1ነገ 9:8፤ ኤር 19:8፤ ሰቆ 2:15፤ ሚክ 6:16
  • +ዘዳ 28:37

ኤርምያስ 18:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 31:17

ኤርምያስ 18:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መመሪያው፤ ትምህርቱ።”

  • *

    ቃል በቃል “በምላስ እንምታው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 11:19

ኤርምያስ 18:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለነፍሴ ጉድጓድ ቆፍረዋልና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 35:7

ኤርምያስ 18:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 12:3
  • +ሰቆ 5:3
  • +2ዜና 36:17

ኤርምያስ 18:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 38:12

ኤርምያስ 18:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 11:19, 20
  • +ኤር 15:15
  • +መዝ 35:4

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 18:2ኤር 19:1
ኤር. 18:6ሮም 9:20, 21
ኤር. 18:7ኤር 1:10፤ 12:14፤ 25:9፤ 45:4
ኤር. 18:81ነገ 8:33, 34፤ መዝ 106:45፤ ኤር 7:3፤ 26:3፤ ሕዝ 18:21፤ ኢዩ 2:13፤ ዮናስ 3:5, 10
ኤር. 18:11ኢሳ 1:16፤ ሕዝ 18:23
ኤር. 18:12ኤር 2:25
ኤር. 18:12ዘዳ 29:19, 20፤ ኤር 7:24
ኤር. 18:13ኤር 2:13
ኤር. 18:15ኤር 2:19፤ 3:21
ኤር. 18:15ኤር 10:14, 15
ኤር. 18:15ኤር 6:16
ኤር. 18:16ዘሌ 26:33፤ ሕዝ 6:14
ኤር. 18:161ነገ 9:8፤ ኤር 19:8፤ ሰቆ 2:15፤ ሚክ 6:16
ኤር. 18:16ዘዳ 28:37
ኤር. 18:17ዘዳ 31:17
ኤር. 18:18ኤር 11:19
ኤር. 18:20መዝ 35:7
ኤር. 18:21ኤር 12:3
ኤር. 18:21ሰቆ 5:3
ኤር. 18:212ዜና 36:17
ኤር. 18:22መዝ 38:12
ኤር. 18:23ኤር 11:19, 20
ኤር. 18:23ኤር 15:15
ኤር. 18:23መዝ 35:4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 18:1-23

ኤርምያስ

18 ከይሖዋ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦ 2 “ተነሥተህ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ውረድ፤+ እኔም በዚያ ቃሌን አሰማሃለሁ።”

3 ስለዚህ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ወረድኩ፤ እሱም በሸክላ መዘውሮቹ ላይ እየሠራ ነበር። 4 ሆኖም ሸክላ ሠሪው በጭቃ እየሠራ የነበረው ዕቃ እጁ ላይ ተበላሸ። በመሆኑም ሸክላ ሠሪው ተስማሚ ሆኖ ባገኘው መንገድ* መልሶ ሌላ ዕቃ አድርጎ ሠራው።

5 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 6 “‘የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ይህ ሸክላ ሠሪ እንዳደረገው እኔም በእናንተ ላይ ማድረግ አልችልም?’ ይላል ይሖዋ። ‘የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እነሆ፣ በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ ጭቃ፣ እናንተም በእኔ እጅ እንዲሁ ናችሁ።+ 7 አንድን ብሔር ወይም አንድን መንግሥት እንደምነቅል፣ እንደማፈርስና እንደማጠፋ በተናገርኩ ጊዜ፣+ 8 ያ ብሔር እኔ ያወገዝኩትን ክፉ ነገር ቢተው፣ ሐሳቤን ለውጬ በእሱ ላይ ላመጣው ያሰብኩትን ጥፋት እተወዋለሁ።*+ 9 ሆኖም አንድን ብሔር ወይም አንድን መንግሥት እንደምገነባውና እንደምተክለው በተናገርኩ ጊዜ፣ 10 በፊቴ ክፉ የሆነውን ነገር ቢያደርግና ድምፄን ባይሰማ እኔም ሐሳቤን ለውጬ ለእሱ አደርገዋለሁ ብዬ ያሰብኩትን መልካም ነገር እተወዋለሁ።’*

11 “አሁንም ለይሁዳ ሰዎችና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እባክህ እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በእናንተ ላይ ጥፋት ለማምጣት እየተዘጋጀሁ ነው፤* በእናንተም ላይ ክፉ ነገር እየጠነሰስኩ ነው። እባካችሁ፣ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ መንገዳችሁንና ተግባራችሁንም አስተካክሉ።”’”+

12 እነሱ ግን እንዲህ አሉ፦ “ይህ ያበቃለት ጉዳይ ነው!+ እኛ እንደሆነ በራሳችን ሐሳብ እንሄዳለን፤ እያንዳንዳችንም ግትር የሆነውን ክፉ ልባችንን እንከተላለን።”+

13 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“እስቲ ራሳችሁ ብሔራትን ጠይቁ።

እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቷል?

የእስራኤል ድንግል እጅግ የሚሰቀጥጥ ነገር አድርጋለች።+

14 የሊባኖስ ዓለታማ ተረተር በረዶ ተለይቶት ያውቃል?

ወይስ ከሩቅ ስፍራ የሚፈስሱት ቀዝቃዛ ውኃዎች ይደርቃሉ?

15 ሕዝቤ ግን እኔን ረስቶኛል።+

ለማይረባ ነገር መሥዋዕት ያቀርባሉና፤+

ሰዎችም በመንገዳቸው፣ በጥንቶቹ ጎዳናዎች እንዲሰናከሉ+

ደግሞም ባልተስተካከሉና ባልተደለደሉ* ተለዋጭ መንገዶች እንዲሄዱ ያደርጋሉ፤

16 ስለዚህ ምድራቸው አስፈሪ ቦታ፣+

ለዘላለምም ማፏጫ ትሆናለች።+

በዚያ የሚያልፍ ሁሉ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታል፤ ራሱንም ይነቀንቃል።+

17 እንደ ምሥራቅ ነፋስ በጠላት ፊት እበትናቸዋለሁ።

በሚጠፉበት ቀን ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አላሳያቸውም።”+

18 እነሱም እንዲህ አሉ፦ “ኑ፣ በኤርምያስ ላይ እናሲር፤+ ሕጉ* ከካህናት፣ ምክር ከጠቢባን ወይም ቃሉ ከነቢያት አይጠፋምና። ኑና በአንደበታችን እናጥቃው፤* የሚናገረውንም ቃል አንስማ።”

19 ይሖዋ ሆይ፣ ትኩረትህን ወደ እኔ አድርግ፤

ተቃዋሚዎቼ የሚናገሩትንም ስማ።

20 ስለ መልካም ነገር ክፉ መመለስ አግባብ ነው?

እነሱ ጉድጓድ ቆፍረውልኛልና።*+

ቁጣህ ከእነሱ እንዲመለስ፣ ስለ እነሱ መልካም ነገር ለመናገር

ምን ያህል ጊዜ በፊትህ እንደቆምኩ አስብ።

21 ስለዚህ ወንዶች ልጆቻቸውን ለረሃብ ዳርጋቸው፤

ለሰይፍ ኃይል አሳልፈህ ስጣቸው።+

ሚስቶቻቸው የወላድ መሃንና መበለት ይሁኑ።+

ወንዶቻቸው በገዳይ መቅሰፍት ይሙቱ፤

ወጣቶቻቸው በጦር ሜዳ በሰይፍ ተመተው ይውደቁ።+

22 በድንገት ወራሪዎችን ስታመጣባቸው

ከየቤታቸው ጩኸት ይሰማ።

እኔን ለመያዝ ጉድጓድ ቆፍረዋልና፤

ለእግሮቼም ወጥመድ ዘርግተዋል።+

23 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን

እኔን ለመግደል የጠነሰሱትን ሴራ ሁሉ በሚገባ ታውቃለህ።+

በደላቸውን አትሸፍን፤

ኃጢአታቸውንም ከፊትህ አትደምስስ።

በቁጣ ተነሳስተህ እርምጃ ስትወስድባቸው+

በፊትህ ይሰናከሉ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ