ዮሐንስ 1:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 በማግስቱ ኢየሱስ ወደ እሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ “የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደው+ የአምላክ በግ+ ይኸውላችሁ!+ 1 ቆሮንቶስ 5:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 አዲስ ሊጥ እንድትሆኑ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ፤ ምክንያቱም የፋሲካችን በግ+ የሆነው ክርስቶስ ስለተሠዋ+ ከእርሾ ነፃ ናችሁ። ራእይ 5:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በዙፋኑ መካከል፣ በአራቱ ሕያዋን ፍጥረታት መካከልና በሽማግሌዎቹ+ መካከል የታረደ+ የሚመስል በግ+ ቆሞ አየሁ፤ በጉም ሰባት ቀንዶችና ሰባት ዓይኖች አሉት፤ ዓይኖቹም ወደ መላው ምድር የተላኩትን ሰባቱን የአምላክ መናፍስት+ ያመለክታሉ።
6 በዙፋኑ መካከል፣ በአራቱ ሕያዋን ፍጥረታት መካከልና በሽማግሌዎቹ+ መካከል የታረደ+ የሚመስል በግ+ ቆሞ አየሁ፤ በጉም ሰባት ቀንዶችና ሰባት ዓይኖች አሉት፤ ዓይኖቹም ወደ መላው ምድር የተላኩትን ሰባቱን የአምላክ መናፍስት+ ያመለክታሉ።