የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 38:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 “እባክህ ይሖዋ ሆይ፣ በታማኝነትና በሙሉ ልብ+ በፊትህ እንዴት እንደተመላለስኩ እንዲሁም በዓይኖችህ ፊት መልካም የሆነውን ነገር እንዳደረግኩ እንድታስታውስ አጥብቄ እለምንሃለሁ።”+ ሕዝቅያስም ምርር ብሎ አለቀሰ።

  • ኢሳይያስ 38:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 “ተመልሰህ ሄደህ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፦+ ‘የአባትህ የዳዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ጸሎትህን ሰምቻለሁ።+ እንባህንም አይቻለሁ።+ እነሆ በዕድሜህ* ላይ 15 ዓመት እጨምርልሃለሁ፤+

  • ኢዩኤል 2:13, 14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤+

      ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋም ተመለሱ፤

      እሱ ሩኅሩኅና* መሐሪ፣ ለቁጣ የዘገየና+ ታማኝ ፍቅሩ የበዛ ነውና፤+

      ሊያመጣ ያሰበውንም ጥፋት መለስ ብሎ ያጤናል።*

      14 ደግሞም ተመልሶ ጉዳዩን እንደገና በማጤን፣*+

      ለአምላካችሁ ለይሖዋ የእህል መባና የመጠጥ መባ ማቅረብ ትችሉ ዘንድ

      በረከት ያስቀርላችሁ እንደሆነ ማን ያውቃል?

  • አሞጽ 5:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ክፉ የሆነውን ጥሉ፤ መልካም የሆነውንም ውደዱ፤+

      በከተማዋም በር ላይ ፍትሕ እንዲሰፍን አድርጉ።+

      የሠራዊት አምላክ ይሖዋ

      ከዮሴፍ ለቀሩት ሰዎች ሞገሱን ያሳያቸው ይሆናል።’+

  • ዮናስ 3:8, 9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 ሰውም ሆነ እንስሳ ማቅ ይልበስ፤ ሁሉም አጥብቆ ወደ አምላክ ይጩኽ፤ ክፉ መንገዳቸውንና የሚፈጽሙትን ግፍ ይተዉ። 9 እኛ እንዳንጠፋ፣ እውነተኛው አምላክ ሊያመጣው ያሰበውን ነገር እንደገና በማጤን* ከሚነደው ቁጣው ይመለስ እንደሆነ ማን ያውቃል?”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ