ዘሌዋውያን 19:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 “‘ወደ መናፍስት ጠሪዎች አትሂዱ፤+ ጠንቋዮችንም አትጠይቁ፤+ እንዲህ ካደረጋችሁ በእነሱ ትረክሳላችሁ። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። ዘዳግም 18:10, 11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፣+ ሟርተኛ፣+ አስማተኛ፣+ ሞራ ገላጭ፣+ ምትሃተኛ፣+ 11 ድግምተኛ፣ መናፍስት ጠሪ፣+ ጠንቋይ+ ወይም ሙታን አነጋጋሪ+ በመካከልህ አይገኝ። 2 ነገሥት 21:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ምናሴ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 12 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ55 ዓመት ገዛ።+ የእናቱ ስም ሄፍጺባ ነበር። 2 ነገሥት 21:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 የገዛ ልጁን ለእሳት አሳልፎ ሰጠ፤ አስማተኛና መተተኛም ሆነ፤+ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ቀጠረ።+ ይሖዋን ያስቆጣው ዘንድ በእሱ ፊት በጣም ብዙ መጥፎ ነገሮችን ሠራ። ኢሳይያስ 8:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 እነሱም “የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሹኩትን መናፍስት ጠሪዎች ወይም ጠንቋዮች ጠይቁ” ቢሏችሁ፣ አንድ ሕዝብ መጠየቅ ያለበት የራሱን አምላክ አይደለም? ስለ ሕያዋንስ ሙታንን መጠየቁ ተገቢ ነው?+
10 ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፣+ ሟርተኛ፣+ አስማተኛ፣+ ሞራ ገላጭ፣+ ምትሃተኛ፣+ 11 ድግምተኛ፣ መናፍስት ጠሪ፣+ ጠንቋይ+ ወይም ሙታን አነጋጋሪ+ በመካከልህ አይገኝ።
6 የገዛ ልጁን ለእሳት አሳልፎ ሰጠ፤ አስማተኛና መተተኛም ሆነ፤+ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ቀጠረ።+ ይሖዋን ያስቆጣው ዘንድ በእሱ ፊት በጣም ብዙ መጥፎ ነገሮችን ሠራ።
19 እነሱም “የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሹኩትን መናፍስት ጠሪዎች ወይም ጠንቋዮች ጠይቁ” ቢሏችሁ፣ አንድ ሕዝብ መጠየቅ ያለበት የራሱን አምላክ አይደለም? ስለ ሕያዋንስ ሙታንን መጠየቁ ተገቢ ነው?+