ዘፍጥረት 32:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 እኔ ባሪያህ ይህን ያህል ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ልታሳየኝ+ የሚገባኝ ሰው አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ስሻገር ከበትር ሌላ ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን ይኸው ሁለት ቡድን ሆኛለሁ።+ 1 ሳሙኤል 2:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ይሖዋ ያደኸያል፤ እንዲሁም ያበለጽጋል፤+እሱ ያዋርዳል፤ ከፍ ከፍም ያደርጋል።+ 2 ዜና መዋዕል 25:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 በዚህ ጊዜ አሜስያስ የእውነተኛውን አምላክ ሰው “ታዲያ ለእስራኤል ወታደሮች የሰጠሁት 100 ታላንት ምን ይሁን?” አለው። የእውነተኛውም አምላክ ሰው “ይሖዋ ከዚህ እጅግ የሚበልጥ ሊሰጥህ ይችላል” ሲል መለሰለት።+ ምሳሌ 22:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ትሕትናና ይሖዋን መፍራትሀብት፣ ክብርና ሕይወት ያስገኛል።+ ኢሳይያስ 61:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 በኀፍረት ፋንታ እጥፍ ድርሻ ይኖራችኋል፤በውርደትም ፋንታ በሚያገኙት ድርሻ በደስታ እልል ይላሉ። አዎ፣ በምድራቸው እጥፍ ድርሻ ይወርሳሉ።+ የዘላለም ሐሴት የእነሱ ይሆናል።+
10 እኔ ባሪያህ ይህን ያህል ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ልታሳየኝ+ የሚገባኝ ሰው አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ስሻገር ከበትር ሌላ ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን ይኸው ሁለት ቡድን ሆኛለሁ።+
9 በዚህ ጊዜ አሜስያስ የእውነተኛውን አምላክ ሰው “ታዲያ ለእስራኤል ወታደሮች የሰጠሁት 100 ታላንት ምን ይሁን?” አለው። የእውነተኛውም አምላክ ሰው “ይሖዋ ከዚህ እጅግ የሚበልጥ ሊሰጥህ ይችላል” ሲል መለሰለት።+
7 በኀፍረት ፋንታ እጥፍ ድርሻ ይኖራችኋል፤በውርደትም ፋንታ በሚያገኙት ድርሻ በደስታ እልል ይላሉ። አዎ፣ በምድራቸው እጥፍ ድርሻ ይወርሳሉ።+ የዘላለም ሐሴት የእነሱ ይሆናል።+