8 “ይሖዋን አመስግኑ፤+ ስሙን ጥሩ፤
ሥራውን በሕዝቦች መካከል አስታውቁ!+
9 ለእሱ ዘምሩ፤ የውዳሴም መዝሙር ዘምሩለት፤+
አስደናቂ በሆኑት ሥራዎቹ ሁሉ ላይ አሰላስሉ።+
10 በቅዱስ ስሙ ተኩራሩ።+
ይሖዋን የሚፈልጉ ሰዎች፣ ልባቸው ሐሴት ያድርግ።+
11 ይሖዋንና ብርታቱን ፈልጉ።+
ፊቱን ሁልጊዜ እሹ።+
12 ያከናወናቸውን አስደናቂ ሥራዎች፣
ተአምራቱንና የተናገረውን ፍርድ አስታውሱ፤+
13 እናንተ የአገልጋዩ የእስራኤል ዘሮች፣+
እሱ የመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች፣+ ይህን አስታውሱ።