መዝሙር 97:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 እናንተ ይሖዋን የምትወዱ፣ ክፉ የሆነውን ነገር ጥሉ።+ እሱ የታማኝ አገልጋዮቹን ሕይወት* ይጠብቃል፤+ከክፉዎች እጅ* ይታደጋቸዋል።+ መዝሙር 101:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 በዓይኖቼ ፊት የማይረባ* ነገር አላኖርም። ከትክክለኛው መንገድ የሚወጡ ሰዎች የሚያደርጓቸውን ነገሮች እጠላለሁ፤+ከእነሱ ጋር የሚያገናኘኝ ምንም ጉዳይ የለም።* ምሳሌ 8:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ይሖዋን መፍራት ማለት ክፉ ነገርን መጥላት ነው።+ ትዕቢትን፣ ኩራትን፣+ ክፉ መንገድንና ጠማማ ንግግርን እጠላለሁ።+ ምሳሌ 13:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ጻድቅ ውሸትን ይጠላል፤+የክፉ ሰው ድርጊት ግን ኀፍረትና ውርደት ያመጣበታል። ሮም 12:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ፍቅራችሁ ግብዝነት የሌለበት ይሁን።+ ክፉ የሆነውን ተጸየፉ፤+ ጥሩ የሆነውን አጥብቃችሁ ያዙ።
3 በዓይኖቼ ፊት የማይረባ* ነገር አላኖርም። ከትክክለኛው መንገድ የሚወጡ ሰዎች የሚያደርጓቸውን ነገሮች እጠላለሁ፤+ከእነሱ ጋር የሚያገናኘኝ ምንም ጉዳይ የለም።*