መዝሙር 45:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 አምላክ ለዘላለም ዙፋንህ ነው፤+የመንግሥትህ በትር የቅንነት* በትረ መንግሥት ነው።+ ኢሳይያስ 32:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 እነሆ፣ ንጉሥ+ ለጽድቅ ይነግሣል፤+መኳንንትም ፍትሕ ለማስፈን ይገዛሉ። ኤርምያስ 23:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 “እነሆ፣ ለዳዊት፣ ጻድቅ ቀንበጥ* የማስነሳበት ጊዜ እየደረሰ ነው”+ ይላል ይሖዋ። “ንጉሥም ይገዛል፤+ በማስተዋል ይመላለሳል እንዲሁም በምድሪቱ ላይ ለፍትሕና ለጽድቅ ይቆማል።+ ዕብራውያን 1:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ስለ ልጁ ሲናገር ግን እንዲህ ይላል፦ “አምላክ ለዘላለም ዙፋንህ ነው፤+ የመንግሥትህ በትርም የቅንነት* በትረ መንግሥት ነው።
5 “እነሆ፣ ለዳዊት፣ ጻድቅ ቀንበጥ* የማስነሳበት ጊዜ እየደረሰ ነው”+ ይላል ይሖዋ። “ንጉሥም ይገዛል፤+ በማስተዋል ይመላለሳል እንዲሁም በምድሪቱ ላይ ለፍትሕና ለጽድቅ ይቆማል።+