ኢሳይያስ 35:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ሐሴት ያደርጋል፤+በረሃማው ቦታም ደስ ይለዋል፤ እንደ ሳሮን አበባም * ያብባል።+ ኢሳይያስ 41:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 በበረሃ አርዘ ሊባኖስ፣ግራር፣ አደስና ዘይት የሚሰጥ ዛፍ እተክላለሁ።+ በበረሃማ ሜዳ የጥድ ዛፍ፣የአሽ ዛፍና* የፈረንጅ ጥድ በአንድነት እተክላለሁ፤+