የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘሌዋውያን 20:22
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 “‘ትኖሩባት ዘንድ እናንተን የማስገባባት ምድር እንዳትተፋችሁ+ ደንቦቼንና ድንጋጌዎቼን ሁሉ ጠብቁ፤+ እንዲሁም ፈጽሟቸው።+

  • ዘዳግም 28:63, 64
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 63 “ይሖዋ እናንተን በማበልጸግና በማብዛት እጅግ ይደሰት እንደነበረው ሁሉ ይሖዋ እናንተን በማጥፋትና በመደምሰስም እጅግ ይደሰታል፤ ገብታችሁ ከምትወርሷት ምድር ላይ ተጠራርጋችሁ ትጠፋላችሁ።

      64 “ይሖዋ ከአንዱ የምድር ጫፍ እስከ ሌላኛው የምድር ጫፍ በብሔራት ሁሉ መካከል ይበትንሃል፤+ እዚያም አንተም ሆንክ አባቶችህ የማታውቋቸውን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ አማልክት ታገለግላለህ።+

  • ኢያሱ 23:15, 16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ሆኖም አምላካችሁ ይሖዋ የገባላችሁ መልካም ቃል በሙሉ እንደተፈጸመላችሁ ሁሉ ይሖዋ አመጣባችኋለሁ ብሎ+ የተናገረውን ጥፋት ሁሉ* ያመጣባችኋል፤ አምላካችሁ ይሖዋ ከሰጣችሁ ከዚህች መልካም ምድርም ያጠፋችኋል።+ 16 አምላካችሁ ይሖዋ እንድትጠብቁት ያዘዛችሁን ቃል ኪዳን ካፈረሳችሁ እንዲሁም ሄዳችሁ ሌሎች አማልክትን ካገለገላችሁና ለእነሱ ከሰገዳችሁ የይሖዋ ቁጣ በእናንተ ላይ ይነድዳል፤+ ከሰጣችሁም መልካም ምድር ላይ በፍጥነት ትጠፋላችሁ።”+

  • 1 ነገሥት 9:6, 7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 ሆኖም እናንተም ሆናችሁ ልጆቻችሁ እኔን ከመከተል ዞር ብትሉ እንዲሁም በፊታችሁ ያስቀመጥኳቸውን ትእዛዛቴንና ደንቦቼን ባትጠብቁ፣ ሄዳችሁም ሌሎች አማልክትን ብታገለግሉና ለእነሱ ብትሰግዱ+ 7 እስራኤላውያንን ከሰጠኋቸው ምድር ላይ አጠፋቸዋለሁ፤+ ለስሜ የቀደስኩትንም ቤት ከፊቴ አስወግደዋለሁ፤+ እስራኤላውያንም በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ መቀለጃና* መሳለቂያ ይሆናሉ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ