-
1 ነገሥት 1:40አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
40 ከዚያም ሕዝቡ በሙሉ ዋሽንት እየነፋና በደስታ እየፈነደቀ ተከትሎት ወጣ፤ ከጩኸታቸውም የተነሳ ምድሪቱ ተሰነጠቀች።+
-
-
ማርቆስ 11:7-11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 ውርንጭላውንም+ ወደ ኢየሱስ አመጡት፤ መደረቢያቸውንም በውርንጭላው ጀርባ ላይ አደረጉ፤ እሱም ተቀመጠበት።+ 8 ብዙዎችም መደረቢያቸውን በመንገዱ ላይ አነጠፉ፤ ሌሎች ደግሞ በመንገድ ዳር ካሉት ዛፎች ቅርንጫፎች እየቆረጡ አነጠፉ።+ 9 ከፊቱ የሚሄዱትና ከኋላው የሚከተሉት እንዲህ እያሉ ይጮኹ ነበር፦ “እንድታድነው እንለምንሃለን!*+ በይሖዋ* ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!+ 10 የሚመጣው የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከ ነው!+ በሰማይ የምትኖረው ሆይ፣ እንድታድነው እንለምንሃለን!” 11 ኢየሱስም ኢየሩሳሌም ደረሰ፤ ከዚያም ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ በዙሪያውም ያለውን ነገር ሁሉ ተመለከተ፤ ሆኖም ሰዓቱ ገፍቶ ስለነበር ከአሥራ ሁለቱ ጋር ወደ ቢታንያ ሄደ።+
-