የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 13:18-23
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 “እንግዲህ እናንተ ዘር የዘራውን ሰው ምሳሌ ስሙ።+ 19 አንድ ሰው የመንግሥቱን ቃል ሰምቶ የማያስተውል ከሆነ ክፉው+ መጥቶ በልቡ ውስጥ የተዘራውን ዘር ይነጥቀዋል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ዘር ይህ ነው።+ 20 በድንጋያማ መሬት ላይ የተዘራው ደግሞ ቃሉን ሲሰማ ወዲያውኑ በደስታ የሚቀበል ሰው ነው።+ 21 ሆኖም ቃሉ በውስጡ ሥር ስለማይሰድ የሚቆየው ለጥቂት ጊዜ ነው፤ በቃሉ የተነሳም መከራ ወይም ስደት ሲደርስበት ወዲያው ይሰናከላል። 22 በእሾህ መካከል የተዘራው ደግሞ ቃሉን የሚሰማ ነው፤ ይሁንና የዚህ ሥርዓት* ጭንቀት+ እንዲሁም ሀብት ያለው የማታለል ኃይል ቃሉን ያንቀዋል፤ የማያፈራም ይሆናል።+ 23 በጥሩ አፈር ላይ የተዘራው ደግሞ ቃሉን የሚሰማና የሚያስተውል ነው፤ ፍሬም ያፈራል፤ አንዱ 100፣ አንዱም 60፣ ሌላውም 30 እጥፍ ይሰጣል።”+

  • ማርቆስ 4:14-20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 “ዘሪው ቃሉን ይዘራል።+ 15 ቃሉ ሲዘራ መንገድ ዳር እንደወደቁት ዘሮች የሆኑት እነዚህ ናቸው፤ ቃሉን እንደሰሙ ግን ሰይጣን መጥቶ+ በውስጣቸው የተዘራውን ቃል ይወስደዋል።+ 16 በተመሳሳይም በድንጋያማ መሬት እንደተዘሩት ዘሮች የሆኑት እነዚህ ናቸው፤ ቃሉን እንደሰሙ በደስታ ይቀበሉታል።+ 17 ሆኖም ቃሉ በውስጣቸው ሥር ስለማይሰድ የሚቆዩት ለጥቂት ጊዜ ነው፤ ከዚያም በቃሉ የተነሳ መከራ ወይም ስደት ሲደርስባቸው ወዲያውኑ ይሰናከላሉ። 18 በእሾህ መካከል እንደተዘሩት ዘሮች የሆኑ ሌሎች ደግሞ አሉ። እነዚህ ቃሉን የሰሙ ናቸው፤+ 19 ይሁንና የዚህ ሥርዓት* ጭንቀትና+ ሀብት ያለው የማታለል ኃይል+ እንዲሁም የሌሎች ነገሮች ሁሉ ምኞት+ ወደ ልባቸው ሰርጎ በመግባት ቃሉን ያንቀዋል፤ የማያፈራም ይሆናል። 20 በመጨረሻም፣ ጥሩ አፈር ላይ እንደተዘሩት ዘሮች የሆኑት ቃሉን የሚሰሙና በደስታ የሚቀበሉ እንዲሁም 30፣ 60 እና 100 እጥፍ የሚያፈሩ ናቸው።”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ