ኢሳይያስ 11:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ተኩላ ከበግ ጠቦት ጋር የሚቀመጥበት ጊዜ ይኖራል፤+ነብርም ከፍየል ግልገል ጋር ይተኛል፤ጥጃ፣ አንበሳና* የሰባ ከብት አብረው ይሆናሉ፤*+ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል። ኢሳይያስ 35:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ሐሴት ያደርጋል፤+በረሃማው ቦታም ደስ ይለዋል፤ እንደ ሳሮን አበባም * ያብባል።+ ኢሳይያስ 65:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 እነሆ፣ አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር እየፈጠርኩ ነውና፤+የቀድሞዎቹ ነገሮች አይታሰቡም፤*ወደ ልብም አይገቡም።+ የሐዋርያት ሥራ 24:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ደግሞም እነዚህ ሰዎች ራሳቸው ተስፋ እንደሚያደርጉት ጻድቃንም ሆኑ ጻድቃን ያልሆኑ ሰዎች+ ከሞት እንደሚነሱ+ በአምላክ ተስፋ አለኝ። ራእይ 21:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 እኔም አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አየሁ፤+ የቀድሞው ሰማይና የቀድሞው ምድር አልፈዋልና፤+ ባሕሩም+ ከእንግዲህ ወዲህ የለም።
6 ተኩላ ከበግ ጠቦት ጋር የሚቀመጥበት ጊዜ ይኖራል፤+ነብርም ከፍየል ግልገል ጋር ይተኛል፤ጥጃ፣ አንበሳና* የሰባ ከብት አብረው ይሆናሉ፤*+ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል።