ማቴዎስ 5:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ።+ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አትችልም። ኤፌሶን 5:8, 9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 እናንተ በአንድ ወቅት ጨለማ ውስጥ ነበራችሁና፤ አሁን ግን የጌታ በመሆናችሁ+ ብርሃን ውስጥ ናችሁ።+ የብርሃን ልጆች ሆናችሁ መመላለሳችሁን ቀጥሉ፤ 9 የብርሃን ፍሬ ሁሉንም ዓይነት ጥሩነት፣ ጽድቅና እውነት የያዘ ነውና።+ 1 ጴጥሮስ 2:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን+ የእሱን “ድንቅ ባሕርያት* በየቦታው እንድታውጁ+ የተመረጠ ዘር፣ ንጉሣዊ ካህናት፣ ቅዱስ ብሔር፣+ ልዩ ንብረት እንዲሆን የተለየ ሕዝብ”+ ናችሁ። 1 ጴጥሮስ 2:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ክፉ አድራጊዎች እንደሆናችሁ አድርገው ሲከሷችሁ መልካም ሥራችሁን በዓይናቸው ማየት እንዲችሉ+ ብሎም አምላክ ለመመርመር በሚመጣበት ቀን እሱን እንዲያከብሩ በዓለም ባሉ ሰዎች መካከል መልካም ምግባር ይኑራችሁ።+
8 እናንተ በአንድ ወቅት ጨለማ ውስጥ ነበራችሁና፤ አሁን ግን የጌታ በመሆናችሁ+ ብርሃን ውስጥ ናችሁ።+ የብርሃን ልጆች ሆናችሁ መመላለሳችሁን ቀጥሉ፤ 9 የብርሃን ፍሬ ሁሉንም ዓይነት ጥሩነት፣ ጽድቅና እውነት የያዘ ነውና።+
9 እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን+ የእሱን “ድንቅ ባሕርያት* በየቦታው እንድታውጁ+ የተመረጠ ዘር፣ ንጉሣዊ ካህናት፣ ቅዱስ ብሔር፣+ ልዩ ንብረት እንዲሆን የተለየ ሕዝብ”+ ናችሁ።
12 ክፉ አድራጊዎች እንደሆናችሁ አድርገው ሲከሷችሁ መልካም ሥራችሁን በዓይናቸው ማየት እንዲችሉ+ ብሎም አምላክ ለመመርመር በሚመጣበት ቀን እሱን እንዲያከብሩ በዓለም ባሉ ሰዎች መካከል መልካም ምግባር ይኑራችሁ።+