የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኢሳይያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • የይሖዋ ተራራ ከፍ ከፍ ይላል (1-5)

        • ሰይፋቸውን ማረሻ ያደርጋሉ (4)

      • በይሖዋ ቀን ትዕቢተኞች ይዋረዳሉ (6-22)

ኢሳይያስ 2:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 1:1

ኢሳይያስ 2:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በመጨረሻዎቹ ቀኖች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘካ 8:3
  • +መዝ 72:1, 8፤ 86:9፤ ሚክ 4:1-3፤ ሐጌ 2:7፤ ሥራ 10:34, 35

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 142, 154

    የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ፣

    12/2016፣ ገጽ 3

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/1/2007፣ ገጽ 24-25

    12/1/1994፣ ገጽ 11

    4/1/1994፣ ገጽ 15-17

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 38-44

    ንቁ!፣

    4/8/1996፣ ገጽ 11

    መንግሥት፣ ገጽ 24

ኢሳይያስ 2:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መመሪያ፤ ትምህርት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘካ 8:23
  • +ኢሳ 54:13
  • +ኢሳ 51:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    3/2016፣ ገጽ 17

    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)፣

    ቁጥር 2 2016፣ ገጽ 13

    የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ፣

    12/2016፣ ገጽ 3

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 44-45

    መንግሥት፣ ገጽ 25

    “እነሆ” ብሮሸር፣ ገጽ 28

ኢሳይያስ 2:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ያስተካክላል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 46:9
  • +መዝ 72:7፤ ኢሳ 60:18፤ ማቴ 26:52

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ፣

    12/2016፣ ገጽ 3

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/2000፣ ገጽ 26-27

    4/15/1997፣ ገጽ 13-15, 22

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 37-38, 45-48

    ንቁ!፣

    4/8/1996፣ ገጽ 4, 8-10

    ማመራመር፣ ገጽ 270-271

ኢሳይያስ 2:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 60:19, 20

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 48

ኢሳይያስ 2:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 31:16, 17
  • +ዘዳ 18:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 49-50

ኢሳይያስ 2:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 17:15, 16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 50-51

ኢሳይያስ 2:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 28:1, 2፤ 33:1, 7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 50-51

ኢሳይያስ 2:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 50-51

ኢሳይያስ 2:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 51

ኢሳይያስ 2:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ኀፍረት ይከናነባሉ።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 51

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/1/1994፣ ገጽ 11

ኢሳይያስ 2:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሶፎ 1:4, 7
  • +ኢሳ 66:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 51-53, 56

ኢሳይያስ 2:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 51-52

ኢሳይያስ 2:14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 51-52

ኢሳይያስ 2:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 51-52

ኢሳይያስ 2:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 10:22፤ ሕዝ 27:25

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 51-52

ኢሳይያስ 2:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ኀፍረት ይከናነባሉ።”

ኢሳይያስ 2:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 27:9

ኢሳይያስ 2:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በመሬት ጉድጓዶች ውስጥ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 2:10፤ 2ተሰ 1:9
  • +ራእይ 6:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 53-54

ኢሳይያስ 2:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    በልተው የማይጠግቡ ትናንሽ አጥቢ እንስሳት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 30:22፤ 31:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 53-54

ኢሳይያስ 2:21

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 53-54

ኢሳይያስ 2:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እስትንፋሱ በአፍንጫው ላይ ባለች ሰው።”

ተዛማጅ ሐሳብ

ኢሳ. 2:1ኢሳ 1:1
ኢሳ. 2:2ዘካ 8:3
ኢሳ. 2:2መዝ 72:1, 8፤ 86:9፤ ሚክ 4:1-3፤ ሐጌ 2:7፤ ሥራ 10:34, 35
ኢሳ. 2:3ዘካ 8:23
ኢሳ. 2:3ኢሳ 54:13
ኢሳ. 2:3ኢሳ 51:4
ኢሳ. 2:4መዝ 46:9
ኢሳ. 2:4መዝ 72:7፤ ኢሳ 60:18፤ ማቴ 26:52
ኢሳ. 2:5ኢሳ 60:19, 20
ኢሳ. 2:6ዘዳ 31:16, 17
ኢሳ. 2:6ዘዳ 18:10
ኢሳ. 2:7ዘዳ 17:15, 16
ኢሳ. 2:82ዜና 28:1, 2፤ 33:1, 7
ኢሳ. 2:10ዘፀ 20:18
ኢሳ. 2:12ሶፎ 1:4, 7
ኢሳ. 2:12ኢሳ 66:16
ኢሳ. 2:161ነገ 10:22፤ ሕዝ 27:25
ኢሳ. 2:18ኢሳ 27:9
ኢሳ. 2:19ኢሳ 2:10፤ 2ተሰ 1:9
ኢሳ. 2:19ራእይ 6:15
ኢሳ. 2:20ኢሳ 30:22፤ 31:7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኢሳይያስ 2:1-22

ኢሳይያስ

2 የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ይህ ነው፦+

 2 በዘመኑ መጨረሻ*

የይሖዋ ቤት ተራራ

ከተራሮች አናት በላይ ጸንቶ ይቆማል፤+

ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤

ብሔራትም ሁሉ ወደዚያ ይጎርፋሉ።+

 3 ብዙ ሕዝቦችም ሄደው እንዲህ ይላሉ፦

“ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራ፣

ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ።+

እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤

በጎዳናዎቹም እንሄዳለን።”+

ሕግ* ከጽዮን፣

የይሖዋም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።+

 4 እሱ በብሔራት መካከል ይፈርዳል፤

ከብዙ ሕዝቦች ጋር በተያያዘም ሁሉንም ነገር ያቀናል።*

እነሱ ሰይፋቸውን ማረሻ፣

ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ።+

አንዱ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ ሰይፍ አያነሳም፤

ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይማሩም።+

 5 እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ ኑ፤

በይሖዋ ብርሃን እንሂድ።+

 6 አንተ ሕዝብህን ይኸውም የያዕቆብን ቤት ትተሃል፤+

ምክንያቱም እነሱ ከምሥራቅ በመጡ ነገሮች ተሞልተዋል፤

እንደ ፍልስጤማውያን የአስማት ድርጊቶችን ይፈጽማሉ፤+

በባዕድ አገር ሰዎች ልጆችም ተጥለቅልቀዋል።

 7 ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፤

ሀብታቸውም ገደብ የለውም።

ምድራቸው በፈረሶች ተሞልታለች፤

ሠረገሎቻቸውም ስፍር ቁጥር የላቸውም።+

 8 ምድራቸውም ከንቱ በሆኑ አማልክት ተጥለቅልቃለች።+

የገዛ እጃቸው ለሠራው፣

የገዛ ጣታቸውም ላበጀው ነገር ይሰግዳሉ።

 9 በመሆኑም ሰው አንገቱን ይደፋል፤ ኀፍረትም ይከናነባል፤

አንተም ይቅር ልትላቸው አትችልም።

10 ይሖዋ አስፈሪ ከመሆኑ የተነሳና

ከታላቅ ግርማው የተነሳ

በዓለት ውስጥ ተደበቅ፤ በመሬትም ውስጥ ተሸሸግ።+

11 ትዕቢተኛ ዓይኖች ይዋረዳሉ፤

እብሪተኛ ሰዎችም አንገታቸውን ይደፋሉ።*

በዚያም ቀን ይሖዋ ብቻ ከፍ ከፍ ይደረጋል።

12 ይህ ቀን የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ነውና።+

ቀኑ ትዕቢተኛና ኩሩ በሆነው ሁሉ ላይ፣

ከፍ ባለውም ሆነ ዝቅ ባለው ሁሉ ላይ ይመጣል፤+

13 ታላላቅ በሆኑትና ከፍ ከፍ ባሉት አርዘ ሊባኖሶች ሁሉ ላይ

እንዲሁም በባሳን የባሉጥ ዛፎች ሁሉ ላይ፣

14 ታላላቅ በሆኑት ተራሮች ሁሉና

በረጃጅም ኮረብቶች ሁሉ ላይ፣

15 ረጅም በሆነ ማማ ሁሉና ጠንካራ በሆነ ግንብ ሁሉ ላይ፣

16 በተርሴስ መርከቦች+ ሁሉና

በሚያማምሩ ጀልባዎች ሁሉ ላይ ይደርሳል።

17 ትዕቢተኛ ሰው ይዋረዳል፤

እብሪተኞችም አንገታቸውን ይደፋሉ።*

በዚያም ቀን ይሖዋ ብቻ ከፍ ከፍ ይደረጋል።

18 ከንቱ የሆኑት አማልክት ሙሉ በሙሉ ይወገዳሉ።+

19 ይሖዋ ምድርን በሽብር ለማንቀጥቀጥ በሚነሳበት ጊዜ፣

አስፈሪ ከመሆኑ የተነሳና

ከታላቅ ግርማው የተነሳ+

ሰዎች በዓለት ዋሻዎችና

በጉድጓዶች ውስጥ* ይደበቃሉ።+

20 በዚያ ቀን፣ ሰዎች በፊታቸው ይሰግዱ ዘንድ

ለራሳቸው የሠሯቸውን ከንቱ የሆኑ የብርና የወርቅ አማልክት

ለአይጦችና* ለሌሊት ወፎች ይወረውራሉ፤+

21 ይሖዋ ምድርን በሽብር ለማንቀጥቀጥ በሚነሳበት ጊዜ፣

አስፈሪ ከመሆኑ የተነሳና

ከታላቅ ግርማው የተነሳ

በዓለት ዋሻዎችና

በቋጥኝ ስንጥቆች ውስጥ ይደበቃሉ።

22 ለራሳችሁ ስትሉ፣

ከአፍንጫው እንደሚወጣ እስትንፋስ በሆነ ሰው* አትታመኑ።

ለመሆኑ እሱ ያን ያህል ቦታ እንዲሰጠው የሚያደርግ ምን ነገር አለ?

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ