የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 11
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘፍጥረት የመጽሐፉ ይዘት

      • የባቤል ግንብ (1-4)

      • ይሖዋ ቋንቋቸውን ዘበራረቀ (5-9)

      • ከሴም እስከ አብራም (10-32)

        • የታራ ቤተሰብ (27)

        • አብራም ዑርን ለቆ ወጣ (31)

ዘፍጥረት 11:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:9, 10፤ ዳን 1:2

ዘፍጥረት 11:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/1/2013፣ ገጽ 11

    7/1/2012፣ ገጽ 11

    ንቁ!፣

    2/8/1999፣ ገጽ 22

ዘፍጥረት 11:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 9:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/1998፣ ገጽ 24-25

    12/1/1991፣ ገጽ 10

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 5፣ ገጽ 1

ዘፍጥረት 11:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 3/2020፣ ገጽ 2

ዘፍጥረት 11:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የወጠኑትን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 11:1

ዘፍጥረት 11:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የዕብራይስጡ ቃል ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ አካላትን ሊያመለክት ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 1:26

ዘፍጥረት 11:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 32:8

ዘፍጥረት 11:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ዝብርቅ” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 50:1

ዘፍጥረት 11:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 6:10፤ ሉቃስ 3:23, 36
  • +ዘፍ 10:22፤ 1ዜና 1:17

ዘፍጥረት 11:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:21

ዘፍጥረት 11:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:24፤ 1ዜና 1:18፤ ሉቃስ 3:23, 35

ዘፍጥረት 11:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:21፤ 1ዜና 1:18

ዘፍጥረት 11:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:25፤ 1ዜና 1:19

ዘፍጥረት 11:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 3:23, 35

ዘፍጥረት 11:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 11:32፤ ሉቃስ 3:23, 34

ዘፍጥረት 11:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 12:7፤ 15:1, 6፤ 17:5፤ ያዕ 2:23
  • +ኢያሱ 24:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/1994፣ ገጽ 30

ዘፍጥረት 11:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 12:4፤ 19:1፤ 2ጴጥ 2:7

ዘፍጥረት 11:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 7:4
  • +ዘፍ 15:7፤ ነህ 9:7

ዘፍጥረት 11:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 12:11፤ 17:15፤ 20:12, 13፤ 1ጴጥ 3:6
  • +ዘፍ 22:20፤ 24:15

ዘፍጥረት 11:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 16:1, 2፤ ሮም 4:19፤ ዕብ 11:11

ዘፍጥረት 11:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 11:27, 28
  • +ዘፍ 10:19
  • +ዘፍ 12:4፤ 27:42, 43፤ ሥራ 7:2, 4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)፣

    ቁጥር 3 2017፣ ገጽ 14

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 28

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2006፣ ገጽ 15

    8/15/2001፣ ገጽ 14-15, 16-17

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘፍ. 11:2ዘፍ 10:9, 10፤ ዳን 1:2
ዘፍ. 11:4ዘፍ 9:1
ዘፍ. 11:6ዘፍ 11:1
ዘፍ. 11:7ዘፍ 1:26
ዘፍ. 11:8ዘዳ 32:8
ዘፍ. 11:9ኤር 50:1
ዘፍ. 11:10ዘፍ 6:10፤ ሉቃስ 3:23, 36
ዘፍ. 11:10ዘፍ 10:22፤ 1ዜና 1:17
ዘፍ. 11:11ዘፍ 10:21
ዘፍ. 11:12ዘፍ 10:24፤ 1ዜና 1:18፤ ሉቃስ 3:23, 35
ዘፍ. 11:14ዘፍ 10:21፤ 1ዜና 1:18
ዘፍ. 11:16ዘፍ 10:25፤ 1ዜና 1:19
ዘፍ. 11:18ሉቃስ 3:23, 35
ዘፍ. 11:24ዘፍ 11:32፤ ሉቃስ 3:23, 34
ዘፍ. 11:26ዘፍ 12:7፤ 15:1, 6፤ 17:5፤ ያዕ 2:23
ዘፍ. 11:26ኢያሱ 24:2
ዘፍ. 11:27ዘፍ 12:4፤ 19:1፤ 2ጴጥ 2:7
ዘፍ. 11:28ሥራ 7:4
ዘፍ. 11:28ዘፍ 15:7፤ ነህ 9:7
ዘፍ. 11:29ዘፍ 12:11፤ 17:15፤ 20:12, 13፤ 1ጴጥ 3:6
ዘፍ. 11:29ዘፍ 22:20፤ 24:15
ዘፍ. 11:30ዘፍ 16:1, 2፤ ሮም 4:19፤ ዕብ 11:11
ዘፍ. 11:31ዘፍ 11:27, 28
ዘፍ. 11:31ዘፍ 10:19
ዘፍ. 11:31ዘፍ 12:4፤ 27:42, 43፤ ሥራ 7:2, 4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘፍጥረት 11:1-32

ዘፍጥረት

11 በዚህ ጊዜ፣ ምድር ሁሉ አንድ ቋንቋና ተመሳሳይ ቃላት ትጠቀም ነበር። 2 ወደ ምሥራቅ ሲጓዙም በሰናኦር+ ምድር ወደሚገኝ አንድ ሸለቋማ ሜዳ ደረሱ፤ በዚያም መኖር ጀመሩ። 3 እርስ በርሳቸውም “ኑ! ጡብ እንሥራ፤ በእሳትም እንተኩሰው” ይባባሉ ጀመር። በመሆኑም በድንጋይ ፋንታ ጡብ፣ ለማያያዣም ቅጥራን ተጠቀሙ። 4 ከዚያም “ኑ! በመላው ምድር ላይ እንዳንበተን+ ከተማና ጫፉ ሰማይ የሚደርስ ግንብ ለራሳችን እንገንባ፤ ስማችንንም እናስጠራ” ተባባሉ።

5 ከዚያም ይሖዋ ሰዎች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። 6 ይሖዋም እንዲህ አለ፦ “እነዚህ ሰዎች አንድ ቋንቋ የሚናገሩ አንድ ሕዝብ ናቸው፤+ ይኸው አሁን ደግሞ ይህን መሥራት ጀምረዋል። በዚህ ከቀጠሉ ያሰቡትን* ሁሉ ከማከናወን የሚያግዳቸው ምንም ነገር አይኖርም። 7 ና! እንውረድና*+ በቋንቋ እርስ በርስ እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እናዘበራርቅ።” 8 በመሆኑም ይሖዋ ከዚያ ቦታ ተነስተው በመላው ምድር ላይ እንዲበተኑ አደረገ፤+ እነሱም ቀስ በቀስ ከተማዋን መገንባታቸውን አቆሙ። 9 የከተማዋ ስም ባቤል*+ የተባለውም በዚህ የተነሳ ነው፤ ምክንያቱም ይሖዋ በዚያ የምድርን ሁሉ ቋንቋ አዘበራርቋል፤ እንዲሁም ይሖዋ ሰዎቹ ከዚያ ቦታ ተነስተው በመላው ምድር ላይ እንዲበተኑ አድርጓል።

10 የሴም+ ታሪክ ይህ ነው።

ሴም የጥፋት ውኃ ከተከሰተ ከሁለት ዓመት በኋላ አርፋክስድን+ ሲወልድ የ100 ዓመት ሰው ነበር። 11 ሴም አርፋክስድን ከወለደ በኋላ 500 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።+

12 አርፋክስድ 35 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሴሎምን+ ወለደ። 13 አርፋክስድ ሴሎምን ከወለደ በኋላ 403 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

14 ሴሎም 30 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ኤቤርን+ ወለደ። 15 ሴሎም ኤቤርን ከወለደ በኋላ 403 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

16 ኤቤር 34 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ፋሌቅን+ ወለደ። 17 ኤቤርም ፋሌቅን ከወለደ በኋላ 430 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

18 ፋሌቅ 30 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ረኡን+ ወለደ። 19 ፋሌቅ ረኡን ከወለደ በኋላ 209 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

20 ረኡ 32 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሴሮህን ወለደ። 21 ረኡ ሴሮህን ከወለደ በኋላ 207 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

22 ሴሮህ 30 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ናኮርን ወለደ። 23 ሴሮህ ናኮርን ከወለደ በኋላ 200 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

24 ናኮር 29 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ታራን+ ወለደ። 25 ናኮር ታራን ከወለደ በኋላ 119 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

26 ታራ 70 ዓመት ከኖረ በኋላ አብራምን፣+ ናኮርን+ እና ካራንን ወለደ።

27 የታራ ታሪክ ይህ ነው።

ታራ አብራምን፣ ናኮርን እና ካራንን ወለደ፤ ካራን ደግሞ ሎጥን+ ወለደ። 28 ካራንም አባቱ ታራ ገና በሕይወት እያለ፣ በተወለደበት አገር በከለዳውያን+ ዑር+ ሞተ። 29 አብራምና ናኮር ሚስት አገቡ። የአብራም ሚስት ስሟ ሦራ+ ሲሆን የናኮር ሚስት ደግሞ ስሟ ሚልካ+ ነበር፤ እሷም የሚልካ እና የዪስካ አባት የሆነው የካራን ልጅ ናት። 30 በዚህ ጊዜ ሦራ መሃን ነበረች፤+ ልጅም አልነበራትም።

31 ከዚያም ታራ ልጁን አብራምንና የልጁ ልጅ የሆነውን የካራንን ልጅ ሎጥን+ እንዲሁም የልጁ የአብራም ሚስት የሆነችውን ምራቱን ሦራን ይዞ ወደ ከነአን ምድር+ ለመሄድ ከከለዳውያን ዑር ተነሳ። ከጊዜ በኋላም ወደ ካራን+ መጡ፤ በዚያም መኖር ጀመሩ። 32 ታራም 205 ዓመት ኖረ። ከዚያም በካራን ሞተ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ