የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 104
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መዝሙር የመጽሐፉ ይዘት

      • ድንቅ ለሆኑት የፍጥረት ሥራዎች አምላክን ማወደስ

        • ምድር ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች (5)

        • የወይን ጠጅና ምግብ ሰውን ያስደስታል (15)

        • “ሥራህ ምንኛ ብዙ ነው!” (24)

        • ‘መንፈሳቸውን ስትወስድ ይሞታሉ’ (29)

መዝሙር 104:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴ ይሖዋን ታወድስ።”

  • *

    ወይም “ክብርንና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 103:1
  • +መዝ 86:10
  • +1ዜና 16:27፤ ሕዝ 1:27, 28፤ ዳን 7:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2008፣ ገጽ 13

መዝሙር 104:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ያዕ 1:17፤ 1ዮሐ 1:5
  • +ኢሳ 40:22

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2008፣ ገጽ 13

መዝሙር 104:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በውኃዎቹ ውስጥ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 18:11፤ አሞጽ 9:6
  • +ዘዳ 33:26፤ ኢሳ 19:1
  • +2ሳሙ 22:11፤ ኢዮብ 38:1

መዝሙር 104:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 1:13፤ ዕብ 1:7, 14

መዝሙር 104:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 38:4, 6፤ መዝ 24:1, 2
  • +መክ 1:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንቁ!፣

    ቁጥር 5 2016፣ ገጽ 15

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/2008፣ ገጽ 31

    የአምላክ ቃል፣ ገጽ 103-104

መዝሙር 104:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 1:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የአምላክ ቃል፣ ገጽ 100

መዝሙር 104:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 1:9

መዝሙር 104:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 8:25

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የአምላክ ቃል፣ ገጽ 100

መዝሙር 104:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 38:8-10፤ መዝ 33:7፤ ምሳሌ 8:29፤ ኤር 5:22

መዝሙር 104:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ደረቅ ወንዞች።”

መዝሙር 104:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 38:37፤ መዝ 147:8፤ ኤር 10:13፤ አሞጽ 9:6፤ ማቴ 5:45
  • +መዝ 65:9፤ ሥራ 14:17

መዝሙር 104:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 1:29, 30፤ 9:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 46

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2011፣ ገጽ 8

መዝሙር 104:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መክ 9:7
  • +መክ 10:19

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 43

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2011፣ ገጽ 8

መዝሙር 104:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ባለ ረጃጅም እግር ትልቅ አሞራ።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 8:7

መዝሙር 104:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 39:1
  • +ምሳሌ 30:26

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2004፣ ገጽ 9

    7/15/1997፣ ገጽ 24

መዝሙር 104:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 1:16፤ መዝ 19:6፤ ኤር 31:35

መዝሙር 104:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 1:5፤ መዝ 74:16፤ ኢሳ 45:7

መዝሙር 104:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +አሞጽ 3:4
  • +መዝ 147:9

መዝሙር 104:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 9:6
  • +ምሳሌ 3:19፤ ኤር 10:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ ገጽ 55, 173-175

መዝሙር 104:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 1:21

መዝሙር 104:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 41:1

መዝሙር 104:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 136:25፤ 145:15፤ 147:9፤ ማቴ 6:26

መዝሙር 104:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 12:24
  • +መዝ 107:9፤ 145:16

መዝሙር 104:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 3:19፤ ኢዮብ 34:14, 15፤ መዝ 146:3, 4፤ መክ 3:19, 20፤ 12:7

መዝሙር 104:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 33:4፤ ሥራ 17:28

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/15/2002፣ ገጽ 5

መዝሙር 104:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 1:31

መዝሙር 104:32

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 19:18

መዝሙር 104:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 13:6
  • +መዝ 146:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 14

መዝሙር 104:34

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ስለ እሱ የማሰላስለው ነገር ደስ የሚያሰኝ ይሁን” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 40

መዝሙር 104:35

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴ ይሖዋን ታወድስ።”

  • *

    ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 37:10, 38፤ ምሳሌ 2:22

ተዛማጅ ሐሳብ

መዝ. 104:1መዝ 103:1
መዝ. 104:1መዝ 86:10
መዝ. 104:11ዜና 16:27፤ ሕዝ 1:27, 28፤ ዳን 7:9
መዝ. 104:2ያዕ 1:17፤ 1ዮሐ 1:5
መዝ. 104:2ኢሳ 40:22
መዝ. 104:3መዝ 18:11፤ አሞጽ 9:6
መዝ. 104:3ዘዳ 33:26፤ ኢሳ 19:1
መዝ. 104:32ሳሙ 22:11፤ ኢዮብ 38:1
መዝ. 104:4ሕዝ 1:13፤ ዕብ 1:7, 14
መዝ. 104:5ኢዮብ 38:4, 6፤ መዝ 24:1, 2
መዝ. 104:5መክ 1:4
መዝ. 104:6ዘፍ 1:2
መዝ. 104:7ዘፍ 1:9
መዝ. 104:8ምሳሌ 8:25
መዝ. 104:9ኢዮብ 38:8-10፤ መዝ 33:7፤ ምሳሌ 8:29፤ ኤር 5:22
መዝ. 104:13ኢዮብ 38:37፤ መዝ 147:8፤ ኤር 10:13፤ አሞጽ 9:6፤ ማቴ 5:45
መዝ. 104:13መዝ 65:9፤ ሥራ 14:17
መዝ. 104:14ዘፍ 1:29, 30፤ 9:3
መዝ. 104:15መክ 9:7
መዝ. 104:15መክ 10:19
መዝ. 104:17ኤር 8:7
መዝ. 104:18ኢዮብ 39:1
መዝ. 104:18ምሳሌ 30:26
መዝ. 104:19ዘፍ 1:16፤ መዝ 19:6፤ ኤር 31:35
መዝ. 104:20ዘፍ 1:5፤ መዝ 74:16፤ ኢሳ 45:7
መዝ. 104:21አሞጽ 3:4
መዝ. 104:21መዝ 147:9
መዝ. 104:24ነህ 9:6
መዝ. 104:24ምሳሌ 3:19፤ ኤር 10:12
መዝ. 104:25ዘፍ 1:21
መዝ. 104:26ኢዮብ 41:1
መዝ. 104:27መዝ 136:25፤ 145:15፤ 147:9፤ ማቴ 6:26
መዝ. 104:28ሉቃስ 12:24
መዝ. 104:28መዝ 107:9፤ 145:16
መዝ. 104:29ዘፍ 3:19፤ ኢዮብ 34:14, 15፤ መዝ 146:3, 4፤ መክ 3:19, 20፤ 12:7
መዝ. 104:30ኢዮብ 33:4፤ ሥራ 17:28
መዝ. 104:31ዘፍ 1:31
መዝ. 104:32ዘፀ 19:18
መዝ. 104:33መዝ 13:6
መዝ. 104:33መዝ 146:2
መዝ. 104:35መዝ 37:10, 38፤ ምሳሌ 2:22
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መዝሙር 104:1-35

መዝሙር

104 ይሖዋን ላወድስ።*+

ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ።+

ሞገስንና* ግርማን ለብሰሃል።+

 2 ብርሃንን እንደ ልብስ ተጎናጽፈሃል፤+

ሰማያትን እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘርግተሃል።+

 3 የላይኛዎቹን ክፍሎች ተሸካሚዎች ከላይ ባሉት ውኃዎች ላይ* ያኖራል፤+

ደመናትን ሠረገላው ያደርጋል፤+

በነፋስ ክንፎችም ይሄዳል።+

 4 መላእክቱን መናፍስት፣

አገልጋዮቹን የሚባላ እሳት ያደርጋል።+

 5 ምድርን በመሠረቶቿ ላይ መሠረታት፤+

እሷም ለዘላለም ከቦታዋ አትናወጥም።+

 6 ጥልቅ ውኃን እንደ ልብስ አለበስካት።+

ውኃዎቹ ከተራሮቹ በላይ ቆሙ።

 7 በገሠጽካቸው ጊዜ ሸሹ፤+

የነጎድጓድህን ድምፅ ሲሰሙ በድንጋጤ ፈረጠጡ፤

 8 ተራሮች ወደ ላይ ወጡ፤+ ሸለቆዎችም ወደ ታች ወረዱ፤

ሁሉም ወዳዘጋጀህላቸው ቦታ ሄዱ።

 9 ውኃዎቹ አልፈው እንዳይሄዱ፣

እንደገናም ምድርን እንዳይሸፍኑ ወሰን አበጀህላቸው።+

10 ምንጮችን ወደ ሸለቆዎች* ይልካል፤

በተራሮች መካከል ይፈስሳሉ።

11 የዱር አራዊት ሁሉ ከዚያ ይጠጣሉ፤

የዱር አህዮችም ጥማቸውን ይቆርጣሉ።

12 የሰማይ ወፎች ከእነሱ በላይ ይሰፍራሉ፤

በለመለሙ የዛፍ ቅርንጫፎች መካከል ሆነው ይዘምራሉ።

13 ከላይ ካሉት ክፍሎቹ ሆኖ ተራሮችን ያጠጣል።+

በሥራህ ፍሬ ምድር ረካች።+

14 ሣርን ለከብት፣

አትክልትንም ለሰው ልጆች ጥቅም ያበቅላል፤+

ይህን የሚያደርገው ምድር እህል እንድታስገኝ ነው፤

15 እንዲሁም የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኝ የወይን ጠጅ፣+

ፊትን የሚያበራ ዘይትና

የሰውን ልብ የሚያበረታ እህል እንዲገኝ ነው።+

16 የይሖዋ ዛፎች፣ እሱ የተከላቸው አርዘ ሊባኖሶች፣

ውኃ ጠጥተው ይረካሉ፤

17 በዚያ ወፎች ጎጇቸውን ይሠራሉ።

ራዛ*+ በጥድ ዛፎች ላይ ትኖራለች።

18 ረጃጅሞቹ ተራሮች፣ የተራራ ፍየሎች+ መኖሪያ ናቸው፤

ቋጥኞቹ የሽኮኮዎች+ መሸሸጊያ ናቸው።

19 ጊዜያትን ለመለየት ጨረቃን ሠራ፤

ፀሐይ የምትጠልቅበትን ጊዜ በሚገባ ታውቃለች።+

20 ጨለማን ታመጣለህ፤ ሌሊትም ይሆናል፤+

በዚህ ጊዜ በጫካ የሚኖሩ አራዊት ሁሉ ወጥተው ይንቀሳቀሳሉ።

21 ደቦል አንበሶች አደን ለማግኘት ያገሳሉ፤+

ምግባቸውንም ከአምላክ ይሻሉ።+

22 ፀሐይ ስትወጣ፣

ተመልሰው በየጎሬአቸው ይተኛሉ።

23 ሰውም ወደ ሥራው ተሰማርቶ

እስኪመሽ ድረስ ሲሠራ ይውላል።

24 ይሖዋ ሆይ፣ ሥራህ ምንኛ ብዙ ነው!+

ሁሉንም በጥበብ ሠራህ።+

ምድር በፈጠርካቸው ነገሮች ተሞልታለች።

25 ባሕሩ እጅግ ትልቅና ሰፊ ነው፤

በዚያ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ትናንሽም ሆኑ ትላልቅ ሕያዋን ነገሮች ይርመሰመሳሉ።+

26 በዚያም መርከቦች ይጓዛሉ፤

በዚያ እንዲጫወት የፈጠርከው ሌዋታንም*+ በውስጡ ይሄዳል።

27 በወቅቱ ምግባቸውን እንድትሰጣቸው፣

ሁሉም አንተን ይጠባበቃሉ።+

28 አንተ የምትሰጣቸውን ይሰበስባሉ።+

እጅህን ስትከፍት መልካም ነገሮችን ይጠግባሉ።+

29 ፊትህን ስትሰውር ይታወካሉ።

መንፈሳቸውን ከወሰድክ ይሞታሉ፤ ወደ አፈርም ይመለሳሉ።+

30 መንፈስህን ከላክ ይፈጠራሉ፤+

የምድርንም ገጽ ታድሳለህ።

31 የይሖዋ ክብር ለዘላለም ይኖራል።

ይሖዋ በሥራው ሐሴት ያደርጋል።+

32 ምድርን ሲመለከት ትንቀጠቀጣለች፤

ተራሮችን ሲነካ ይጨሳሉ።+

33 በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ለይሖዋ እዘምራለሁ፤+

በሕይወት እስካለሁ ድረስ ለአምላኬ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+

34 ሐሳቤ እሱን የሚያስደስት ይሁን።*

እኔም በይሖዋ ሐሴት አደርጋለሁ።

35 ኃጢአተኞች ከምድር ይጠፋሉ፤

ክፉዎችም ከእንግዲህ አይገኙም።+

ይሖዋን ላወድስ።* ያህን አወድሱ!*

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ