የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘፍጥረት የመጽሐፉ ይዘት

      • ወደ መርከቡ ገቡ (1-10)

      • ምድር አቀፍ የጥፋት ውኃ (11-24)

ዘፍጥረት 7:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 6:9፤ ዕብ 10:38፤ 11:7፤ 1ጴጥ 3:12፤ 2ጴጥ 2:5, 9

ዘፍጥረት 7:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ንጹሕ ከሆነው ከእያንዳንዱ እንስሳ ሰባት ጥንድ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 8:20

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2007፣ ገጽ 31

    1/1/2004፣ ገጽ 29-30

ዘፍጥረት 7:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “በሰማይ ላይ ከሚበርሩ ፍጥረታት ሰባት ጥንድ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 7:23፤ 8:19

ዘፍጥረት 7:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 7:11, 12
  • +ዘፍ 2:5
  • +ዘፍ 6:7, 17

ዘፍጥረት 7:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 8:13

ዘፍጥረት 7:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 17:27፤ ዕብ 11:7

ዘፍጥረት 7:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 6:19, 20

ዘፍጥረት 7:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/1/2013፣ ገጽ 14-15

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 22-23

ዘፍጥረት 7:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 1:7፤ 8:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/2004፣ ገጽ 30

    የአምላክ ቃል፣ ገጽ 110

ዘፍጥረት 7:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/2013፣ ገጽ 12

ዘፍጥረት 7:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 9:18፤ 1ዜና 1:4
  • +ዘፍ 6:18፤ 1ጴጥ 3:20፤ 2ጴጥ 2:5

ዘፍጥረት 7:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሕይወት መንፈስ።”

ዘፍጥረት 7:17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/2013፣ ገጽ 13-14

ዘፍጥረት 7:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ጴጥ 3:5, 6

ዘፍጥረት 7:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አንድ ክንድ 44.5 ሴንቲ ሜትር ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

ዘፍጥረት 7:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “(የሚንቀሳቀስ) ሥጋ ሁሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 17:27
  • +ዘፍ 6:7, 17

ዘፍጥረት 7:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሕይወት መንፈስ እስትንፋስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 2:7፤ 7:15፤ መክ 3:19፤ ኢሳ 42:5

ዘፍጥረት 7:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 6:7፤ 2ጴጥ 3:5, 6
  • +ማቴ 24:37-39፤ 1ጴጥ 3:20፤ 2ጴጥ 2:5, 9

ዘፍጥረት 7:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 8:3

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘፍ. 7:1ዘፍ 6:9፤ ዕብ 10:38፤ 11:7፤ 1ጴጥ 3:12፤ 2ጴጥ 2:5, 9
ዘፍ. 7:2ዘፍ 8:20
ዘፍ. 7:3ዘፍ 7:23፤ 8:19
ዘፍ. 7:4ዘፍ 7:11, 12
ዘፍ. 7:4ዘፍ 2:5
ዘፍ. 7:4ዘፍ 6:7, 17
ዘፍ. 7:6ዘፍ 8:13
ዘፍ. 7:7ሉቃስ 17:27፤ ዕብ 11:7
ዘፍ. 7:8ዘፍ 6:19, 20
ዘፍ. 7:11ዘፍ 1:7፤ 8:2
ዘፍ. 7:13ዘፍ 9:18፤ 1ዜና 1:4
ዘፍ. 7:13ዘፍ 6:18፤ 1ጴጥ 3:20፤ 2ጴጥ 2:5
ዘፍ. 7:192ጴጥ 3:5, 6
ዘፍ. 7:21ሉቃስ 17:27
ዘፍ. 7:21ዘፍ 6:7, 17
ዘፍ. 7:22ዘፍ 2:7፤ 7:15፤ መክ 3:19፤ ኢሳ 42:5
ዘፍ. 7:23ዘፍ 6:7፤ 2ጴጥ 3:5, 6
ዘፍ. 7:23ማቴ 24:37-39፤ 1ጴጥ 3:20፤ 2ጴጥ 2:5, 9
ዘፍ. 7:24ዘፍ 8:3
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘፍጥረት 7:1-24

ዘፍጥረት

7 ከዚህ በኋላ ይሖዋ ኖኅን እንዲህ አለው፦ “በዚህ ትውልድ መካከል በፊቴ ጻድቅ ሆነህ ያገኘሁህ አንተን ስለሆነ+ አንተም ሆንክ መላው ቤተሰብህ ወደ መርከቡ ግቡ። 2 ከአንተም ጋር ንጹሕ ከሆነው ከእያንዳንዱ እንስሳ ሰባት ሰባት* ትወስዳለህ፤+ ተባዕትና እንስት ይሁኑ፤ ንጹሕ ካልሆነው ከእያንዳንዱ እንስሳ ደግሞ ሁለት ሁለት ውሰድ፤ ተባዕትና እንስት ይሁኑ፤ 3 በተጨማሪም በመላው ምድር ላይ ዘራቸው እንዲተርፍ+ በሰማይ ላይ ከሚበርሩ ፍጥረታት ሰባት ሰባት* አስገባ፤ ተባዕትና እንስት ይሁኑ። 4 ከሰባት ቀን በኋላ በምድር ላይ 40 ቀንና 40 ሌሊት+ ዝናብ አዘንባለሁ፤+ የሠራሁትንም ሕይወት ያለው ነገር ሁሉ ከምድር ገጽ ጠራርጌ አጠፋለሁ።”+ 5 ኖኅም ይሖዋ ያዘዘውን ሁሉ አደረገ።

6 የጥፋት ውኃው በምድር ላይ በወረደበት ወቅት ኖኅ 600 ዓመቱ ነበር።+ 7 ኖኅም የጥፋት ውኃው ከመጀመሩ በፊት ከወንዶች ልጆቹ፣ ከሚስቱና ከልጆቹ ሚስቶች ጋር በመሆን ወደ መርከቡ ገባ።+ 8 እያንዳንዱ ንጹሕ እንስሳ፣ እያንዳንዱ ንጹሕ ያልሆነ እንስሳ እንዲሁም የሚበርሩ ፍጥረታትና በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ነገሮች ሁሉ+ 9 አምላክ ኖኅን ባዘዘው መሠረት ተባዕትና እንስት በመሆን ጥንድ ጥንድ እየሆኑ ኖኅ ወዳለበት ወደ መርከቡ ገቡ። 10 ከሰባት ቀን በኋላም የጥፋት ውኃው በምድር ላይ ወረደ።

11 ኖኅ በተወለደ በ600ኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር ከወሩም በ17ኛው ቀን፣ በዚያ ቀን፣ ተንጣሎ የሚገኘው ጥልቅ ውኃ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፤ የሰማያት የውኃ በሮችም ተከፈቱ።+ 12 ዝናቡም ለ40 ቀንና ለ40 ሌሊት በምድር ላይ ወረደ። 13 በዚያው ቀን ኖኅ ከወንዶች ልጆቹ ከሴም፣ ከካምና ከያፌት+ እንዲሁም ከሚስቱና ከሦስቱ የልጆቹ ሚስቶች ጋር ወደ መርከቡ ገባ።+ 14 ከእነሱም ጋር እያንዳንዱ የዱር እንስሳ እንደየወገኑ፣ እያንዳንዱ የቤት እንስሳ እንደየወገኑ፣ በምድር ላይ ያለ መሬት ለመሬት የሚሄድ እያንዳንዱ እንስሳ እንደየወገኑ፣ እያንዳንዱ የሚበር ፍጥረት እንደየወገኑ እንዲሁም እያንዳንዱ ወፍና እያንዳንዱ ክንፍ ያለው ፍጡር ወደ መርከቡ ገባ። 15 የሕይወት እስትንፋስ* ያለው ሁሉም ዓይነት ሕያው ፍጡር ሁለት ሁለት ሆኖ ወደ ኖኅ በመምጣት መርከቡ ውስጥ ይገባ ጀመር። 16 በመሆኑም አምላክ ኖኅን ባዘዘው መሠረት ሁሉም ዓይነት ሕያው ፍጡር ተባዕትና እንስት እየሆነ ወደ መርከቡ ገባ። ከዚያም ይሖዋ ከኋላው በሩን ዘጋበት።

17 የጥፋት ውኃው ለ40 ቀን በምድር ላይ ያለማቋረጥ ወረደ። ውኃው እየጨመረ ሲሄድ መርከቡን ወደ ላይ አነሳው፤ መርከቡም መሬቱን ለቆ መንሳፈፍ ጀመረ። 18 ውኃው በምድር ላይ እያየለና በእጅጉ እየጨመረ ሄደ፤ መርከቡ ግን በውኃው ላይ መንሳፈፉን ቀጠለ። 19 ውኃው በምድር ላይ በጣም እያየለ ከመሄዱ የተነሳ ከሰማይ በታች ያሉ ረጃጅም ተራሮች በሙሉ ተሸፈኑ።+ 20 ውኃው ከተራሮቹ በላይ 15 ክንድ* ያህል ከፍ አለ።

21 በመሆኑም በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረታት በሙሉ* ይኸውም የሚበርሩ ፍጥረታት፣ የቤት እንስሳት፣ የዱር እንስሳት፣ የሚርመሰመሱ ፍጥረታትና ሰዎች በሙሉ+ ጠፉ።+ 22 በአፍንጫው የሕይወት እስትንፋስ*+ የነበረው በየብስ ላይ የሚኖር ፍጡር ሁሉ ሞተ። 23 እሱም ሰውን፣ እንስሳትን፣ መሬት ለመሬት የሚሄዱ እንስሳትንና በሰማይ ላይ የሚበርሩ ፍጥረታትን ጨምሮ ሕይወት ያለውን ነገር ሁሉ ከምድር ገጽ ጠራርጎ አጠፋ። ሁሉም ከምድር ላይ ተጠራርገው ጠፉ፤+ ከጥፋቱ የተረፉት ኖኅና ከእሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩት ብቻ ናቸው።+ 24 ውኃውም በምድር ላይ እንዳየለ ለ150 ቀናት ቆየ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ