የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 18
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ነገሥት የመጽሐፉ ይዘት

      • ሕዝቅያስ በይሁዳ ላይ ነገሠ (1-8)

      • የእስራኤል አወዳደቅ (9-12)

      • ሰናክሬም ይሁዳን ወረረ (13-18)

      • ራብሻቁ ይሖዋን ተገዳደረ (19-37)

2 ነገሥት 18:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 15:30፤ 17:1
  • +2ነገ 16:2, 20
  • +2ዜና 28:27፤ ማቴ 1:9

2 ነገሥት 18:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አቢያህ የሚለው ስም አጭር መጠሪያ ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 29:1, 2

2 ነገሥት 18:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 15:5፤ 2ነገ 20:3፤ 2ዜና 31:20, 21፤ መዝ 119:128

2 ነገሥት 18:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

  • *

    ወይም “ነሑሽታን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 33:52፤ 1ነገ 3:2፤ 2ነገ 14:1, 4
  • +ዘዳ 7:5፤ 12:3፤ 2ዜና 31:1
  • +ዘኁ 21:8, 9

2 ነገሥት 18:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 19:15፤ 2ዜና 32:7, 8

2 ነገሥት 18:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 10:20፤ ኢያሱ 23:8

2 ነገሥት 18:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 16:7

2 ነገሥት 18:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ጥቂት ሰዎች የሚኖሩባቸውን ቦታዎችም ሆነ ሰው የሚበዛባቸውን ቦታዎች ሁሉ ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 28:18, 19፤ ኢሳ 14:28, 29

2 ነገሥት 18:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 17:1
  • +2ነገ 17:3-6

2 ነገሥት 18:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሆሴዕ 13:16፤ አሞጽ 3:11፤ ሚክ 1:6

2 ነገሥት 18:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 8:4፤ አሞጽ 6:1, 7
  • +2ነገ 17:6፤ 1ዜና 5:26

2 ነገሥት 18:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 8:20፤ 1ነገ 14:15

2 ነገሥት 18:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 10:5
  • +2ዜና 32:1፤ ኢሳ 36:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለሰው ሁሉ፣ ገጽ 14-15

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/1993፣ ገጽ 5-6

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 15፣ ገጽ 20

2 ነገሥት 18:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አንድ ታላንት 34.2 ኪሎ ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 383-385

    ለሰው ሁሉ፣ ገጽ 14-15

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/1993፣ ገጽ 5-6

2 ነገሥት 18:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 12:18፤ 16:8፤ 2ዜና 16:2, 3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/1993፣ ገጽ 6

2 ነገሥት 18:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    በወርቅ የተለበጡ መሆናቸውን ያመለክታል።

  • *

    ቃል በቃል “ቆርጦ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 29:1, 3
  • +1ነገ 6:33-35

2 ነገሥት 18:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አዛዡን።”

  • *

    ወይም “የቤተ መንግሥቱን ዋና ባለሥልጣንና።”

  • *

    ወይም “የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 15:20, 39፤ 2ዜና 11:5, 9
  • +2ዜና 32:9
  • +ኢሳ 36:2, 3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 385-386

2 ነገሥት 18:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የቤተ መንግሥቱ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 19:2፤ ኢሳ 22:20-24
  • +ኢሳ 22:15-19

2 ነገሥት 18:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 32:10፤ ኢሳ 36:4-10

2 ነገሥት 18:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 18:7

2 ነገሥት 18:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 30:1, 2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2010፣ ገጽ 12-13

    8/1/2005፣ ገጽ 11

2 ነገሥት 18:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 32:8
  • +ዘዳ 12:11, 13፤ 2ዜና 32:12
  • +2ዜና 31:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2010፣ ገጽ 13

2 ነገሥት 18:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 10:12, 13

2 ነገሥት 18:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በሶርያ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 18:18
  • +2ነገ 18:17
  • +ዕዝራ 4:7፤ ዳን 2:4
  • +ኢሳ 36:11, 12

2 ነገሥት 18:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 36:13-20

2 ነገሥት 18:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 32:15

2 ነገሥት 18:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 19:32-34

2 ነገሥት 18:31

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ከእኔ ጋር ባርኩ፤ እንዲሁም ወደ እኔ ውጡ።”

2 ነገሥት 18:32

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 17:6

2 ነገሥት 18:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 13:21
  • +2ነገ 17:24
  • +2ነገ 17:6

2 ነገሥት 18:35

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 19:17-19፤ 2ዜና 32:15፤ ኢሳ 37:23

2 ነገሥት 18:36

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 36:21, 22

2 ነገሥት 18:37

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የቤተ መንግሥቱ።”

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ነገ. 18:12ነገ 15:30፤ 17:1
2 ነገ. 18:12ነገ 16:2, 20
2 ነገ. 18:12ዜና 28:27፤ ማቴ 1:9
2 ነገ. 18:22ዜና 29:1, 2
2 ነገ. 18:31ነገ 15:5፤ 2ነገ 20:3፤ 2ዜና 31:20, 21፤ መዝ 119:128
2 ነገ. 18:4ዘኁ 33:52፤ 1ነገ 3:2፤ 2ነገ 14:1, 4
2 ነገ. 18:4ዘዳ 7:5፤ 12:3፤ 2ዜና 31:1
2 ነገ. 18:4ዘኁ 21:8, 9
2 ነገ. 18:52ነገ 19:15፤ 2ዜና 32:7, 8
2 ነገ. 18:6ዘዳ 10:20፤ ኢያሱ 23:8
2 ነገ. 18:72ነገ 16:7
2 ነገ. 18:82ዜና 28:18, 19፤ ኢሳ 14:28, 29
2 ነገ. 18:92ነገ 17:1
2 ነገ. 18:92ነገ 17:3-6
2 ነገ. 18:10ሆሴዕ 13:16፤ አሞጽ 3:11፤ ሚክ 1:6
2 ነገ. 18:11ኢሳ 8:4፤ አሞጽ 6:1, 7
2 ነገ. 18:112ነገ 17:6፤ 1ዜና 5:26
2 ነገ. 18:12ዘዳ 8:20፤ 1ነገ 14:15
2 ነገ. 18:13ኢሳ 10:5
2 ነገ. 18:132ዜና 32:1፤ ኢሳ 36:1
2 ነገ. 18:152ነገ 12:18፤ 16:8፤ 2ዜና 16:2, 3
2 ነገ. 18:162ዜና 29:1, 3
2 ነገ. 18:161ነገ 6:33-35
2 ነገ. 18:17ኢያሱ 15:20, 39፤ 2ዜና 11:5, 9
2 ነገ. 18:172ዜና 32:9
2 ነገ. 18:17ኢሳ 36:2, 3
2 ነገ. 18:182ነገ 19:2፤ ኢሳ 22:20-24
2 ነገ. 18:18ኢሳ 22:15-19
2 ነገ. 18:192ዜና 32:10፤ ኢሳ 36:4-10
2 ነገ. 18:202ነገ 18:7
2 ነገ. 18:21ኢሳ 30:1, 2
2 ነገ. 18:222ዜና 32:8
2 ነገ. 18:22ዘዳ 12:11, 13፤ 2ዜና 32:12
2 ነገ. 18:222ዜና 31:1
2 ነገ. 18:23ኢሳ 10:12, 13
2 ነገ. 18:262ነገ 18:18
2 ነገ. 18:262ነገ 18:17
2 ነገ. 18:26ዕዝራ 4:7፤ ዳን 2:4
2 ነገ. 18:26ኢሳ 36:11, 12
2 ነገ. 18:28ኢሳ 36:13-20
2 ነገ. 18:292ዜና 32:15
2 ነገ. 18:302ነገ 19:32-34
2 ነገ. 18:322ነገ 17:6
2 ነገ. 18:34ዘኁ 13:21
2 ነገ. 18:342ነገ 17:24
2 ነገ. 18:342ነገ 17:6
2 ነገ. 18:352ነገ 19:17-19፤ 2ዜና 32:15፤ ኢሳ 37:23
2 ነገ. 18:36ኢሳ 36:21, 22
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ነገሥት 18:1-37

ሁለተኛ ነገሥት

18 የእስራኤል ንጉሥ የኤላህ ልጅ ሆሺአ+ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የአካዝ+ ልጅ ሕዝቅያስ+ ነገሠ። 2 እሱም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 25 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ29 ዓመት ገዛ። እናቱ አቢ* ትባል ነበር፤ እሷም የዘካርያስ ልጅ ነበረች።+ 3 አባቱ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ እሱም በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ።+ 4 ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎች ያስወገደው፣+ የማምለኪያ ዓምዶቹን ያደቀቀውና+ የማምለኪያ ግንዱን* የቆራረጠው እሱ ነበር። በተጨማሪም ሙሴ ሠርቶት የነበረውን የመዳብ እባብ አደቀቀ፤+ የእስራኤል ሕዝብ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ለእባቡ የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርብ ነበርና፤ ይህም ጣዖት የመዳብ እባብ* ተብሎ ይጠራ ነበር። 5 እሱም በእስራኤል አምላክ በይሖዋ ታመነ፤+ ከእሱ በኋላም ሆነ ከእሱ በፊት ከተነሱት የይሁዳ ነገሥታት መካከል እንደ እሱ ያለ አልተገኘም። 6 ከይሖዋ ጋር ተጣበቀ።+ እሱንም ከመከተል ዞር አላለም፤ ይሖዋ ለሙሴ የሰጠውን ትእዛዝ ጠብቆ ኖረ። 7 ይሖዋም ከእሱ ጋር ነበር። የሚያደርገውንም ነገር ሁሉ በጥበብ ያከናውን ነበር። በኋላም በአሦር ንጉሥ ላይ ዓመፀ፤ እሱንም ለማገልገል ፈቃደኛ አልሆነም።+ 8 በተጨማሪም እስከ ጋዛና እስከ ክልሎቿ ድረስ በመዝለቅ ፍልስጤማውያንን+ ከመጠበቂያ ግንቡ አንስቶ እስከተመሸገው ከተማ* ድረስ ድል አደረገ።

9 ሕዝቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ማለትም የእስራኤል ንጉሥ የኤላህ ልጅ ሆሺአ+ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰልምናሶር በሰማርያ ላይ ዘምቶ ከበባት።+ 10 በሦስተኛው ዓመት ማብቂያ ላይ ከተማዋን ያዟት፤+ ሕዝቅያስ በነገሠ በስድስተኛው ዓመት ይኸውም የእስራኤል ንጉሥ ሆሺአ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ሰማርያ ተያዘች። 11 ከዚያም የአሦር ንጉሥ እስራኤላውያንን ወደ አሦር በግዞት ወስዶ+ በሃላህ፣ በጎዛን ወንዝ አጠገብ በምትገኘው በሃቦርና በሜዶናውያን ከተሞች አሰፈራቸው።+ 12 ይህ የሆነው የአምላካቸውን የይሖዋን ድምፅ ከመስማት ይልቅ ቃል ኪዳኑን ስላፈረሱ ይኸውም የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ የሰጣቸውን ትእዛዝ በሙሉ ስላልጠበቁ ነው።+ አልሰሙም፤ ደግሞም አልታዘዙም።

13 ንጉሥ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም+ በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ ዘምቶ ያዛቸው።+ 14 በመሆኑም የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ በለኪሶ ወደነበረው ወደ አሦር ንጉሥ “በድያለሁ። እባክህ ከእኔ ተመለስ፤ እኔም የምትጠይቀኝን ነገር ሁሉ እሰጣለሁ” የሚል መልእክት ላከ። የአሦርም ንጉሥ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ላይ 300 የብር ታላንትና* 30 የወርቅ ታላንት ቅጣት ጣለበት። 15 በመሆኑም ሕዝቅያስ በይሖዋ ቤትና በንጉሡ ቤት* ግምጃ ቤቶች የተገኘውን ብር ሁሉ ሰጠው።+ 16 በዚህ ጊዜ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ራሱ የለበጣቸውን*+ የይሖዋን ቤተ መቅደስ በሮችና+ መቃኖች ነቃቅሎ* ለአሦር ንጉሥ ሰጠው።

17 ከዚያም የአሦር ንጉሥ ታርታኑን፣* ራብሳሪሱንና* ራብሻቁን* ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ+ በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ላካቸው።+ እነሱም ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተው ወደ ልብስ አጣቢው እርሻ በሚወስደው አውራ ጎዳና ላይ በሚገኘው በላይኛው ኩሬ የውኃ መውረጃ ቦይ አጠገብ ቆሙ።+ 18 ንጉሡ እንዲመጣ በተጣሩ ጊዜ የንጉሡ ቤት* ኃላፊ የሆነው የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፣+ ጸሐፊው ሸብናህ+ እና ታሪክ ጸሐፊው የአሳፍ ልጅ ዮአህ ወደ እነሱ ወጡ።

19 ራብሻቁም እንዲህ አላቸው፦ “እስቲ ሕዝቅያስን እንዲህ በሉት፦ ‘ታላቁ ንጉሥ፣ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ “ለመሆኑ እንዲህ እንድትተማመን ያደረገህ ምንድን ነው?+ 20 ‘የጦር ስልትና ለመዋጋት የሚያስችል ኃይል አለኝ’ ትላለህ፤ ይሁንና ይህ ከንቱ ወሬ ነው። ለመሆኑ በእኔ ላይ ለማመፅ የደፈርከው በማን ተማምነህ ነው?+ 21 እነሆ፣ ሰው ቢመረኮዘው እጁ ላይ ሊሰነቀርና ሊወጋው ከሚችለው ከዚህ የተቀጠቀጠ ሸምበቆ፣ ከግብፅ ድጋፍ አገኛለሁ ብለህ ተማምነሃል።+ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ለሚታመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው። 22 ‘እኛ የምንታመነው በአምላካችን በይሖዋ ነው’+ የምትሉኝ ከሆነ ደግሞ፣ ሕዝቅያስ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ‘መስገድ ያለባችሁ በኢየሩሳሌም በሚገኘው በዚህ መሠዊያ ፊት ነው’+ ብሎ የእሱን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችና መሠዊያዎች አስወግዶ የለም?”’+ 23 በል እስቲ፣ አሁን ከጌታዬ ከአሦር ንጉሥ ጋር ተወራረድ፦ ጋላቢዎች ማግኘት የምትችል ከሆነ 2,000 ፈረሶች እሰጥሃለሁ።+ 24 አንተ የምትታመነው በግብፅ ሠረገሎችና ፈረሰኞች ነው፤ ታዲያ ከጌታዬ አገልጋዮች መካከል ዝቅተኛ ደረጃ ያለውን አንዱን አለቃ እንኳ እንዴት መመከት ትችላለህ? 25 ለመሆኑ ይህን አካባቢ ለማጥፋት የመጣሁት ይሖዋ ሳይፈቅድልኝ ይመስልሃል? ይሖዋ ራሱ ‘በዚህ ምድር ላይ ዘምተህ አጥፋው’ ብሎኛል።”

26 በዚህ ጊዜ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፣ ሸብናህ+ እና ዮአህ ራብሻቁን+ እንዲህ አሉት፦ “እባክህ፣ እኛ አገልጋዮችህ ቋንቋውን ስለምናውቅ በአረማይክ* ቋንቋ+ አናግረን፤ በቅጥሩ ላይ ያለው ሕዝብ በሚሰማው በአይሁዳውያን ቋንቋ አታነጋግረን።”+ 27 ራብሻቁ ግን እንዲህ አላቸው፦ “ጌታዬ ይህን ቃል እንድናገር የላከኝ ለጌታህና ለአንተ ብቻ ነው? ከእናንተ ጋር የገዛ ራሳቸውን እዳሪ ለሚበሉትና የገዛ ራሳቸውን ሽንት ለሚጠጡት በቅጥሩ ላይ ለተቀመጡት ሰዎች ጭምር አይደለም?”

28 ከዚያም ራብሻቁ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ በአይሁዳውያን ቋንቋ እንዲህ አለ፦ “የታላቁን ንጉሥ፣ የአሦርን ንጉሥ ቃል ስሙ።+ 29 ንጉሡ እንዲህ ይላል፦ ‘ሕዝቅያስ አያታላችሁ፤ እሱ ከእጄ ሊታደጋችሁ አይችልምና።+ 30 ደግሞም ሕዝቅያስ “ይሖዋ በእርግጥ ይታደገናል፤ ይህችም ከተማ በአሦር ንጉሥ እጅ አትወድቅም” እያለ በይሖዋ እንድትታመኑ አያድርጋችሁ።+ 31 ሕዝቅያስን አትስሙት፤ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላልና፦ “ከእኔ ጋር ሰላም ፍጠሩ፤ እጃችሁንም ስጡ፤* እያንዳንዳችሁም ከራሳችሁ ወይንና ከራሳችሁ በለስ ትበላላችሁ፤ ከራሳችሁም የውኃ ጉድጓድ ትጠጣላችሁ፤ 32 ይህም የሚሆነው መጥቼ የእናንተን ምድር ወደምትመስለው፣ እህልና አዲስ የወይን ጠጅ፣ ዳቦና የወይን እርሻ፣ የወይራ ዛፍና ማር ወደሚገኝባት ምድር እስክወስዳችሁ ድረስ ነው።+ በዚያን ጊዜ በሕይወት ትኖራላችሁ እንጂ አትሞቱም። ሕዝቅያስን አትስሙት፤ ‘ይሖዋ ይታደገናል’ እያለ ያታልላችኋልና። 33 ከብሔራት አማልክት መካከል ምድሩን ከአሦር ንጉሥ እጅ ያስጣለ አለ? 34 የሃማትና+ የአርጳድ አማልክት የት አሉ? የሰፋርዊም፣+ የሄና እና የኢዋ አማልክትስ የት አሉ? ሰማርያን ከእጄ ማስጣል ችለዋል?+ 35 ከእነዚህ አገሮች አማልክት ሁሉ ምድሩን ከእጄ ማስጣል የቻለ የትኛው ነው? ታዲያ ይሖዋ ኢየሩሳሌምን ከእጄ ሊያስጥላት ይችላል?”’”+

36 ሕዝቡ ግን ንጉሡ “ምንም መልስ አትስጡት” ብሎ አዝዞ ስለነበር ዝም አለ፤ አንድም ቃል አልመለሰለትም።+ 37 ይሁንና የቤቱ* አስተዳዳሪ የሆነው የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፣ ጸሐፊው ሸብናህ እና ታሪክ ጸሐፊው የአሳፍ ልጅ ዮአህ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቅያስ መጡ፤ ራብሻቁ ያለውንም ነገሩት።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ