የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ነገሥት 16
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ነገሥት የመጽሐፉ ይዘት

      • በባኦስ ላይ የተነገረው የይሖዋ ቃል (1-7)

      • ኤላህ በእስራኤል ላይ ነገሠ (8-14)

      • ዚምሪ በእስራኤል ላይ ነገሠ (15-20)

      • ኦምሪ በእስራኤል ላይ ነገሠ (21-28)

      • አክዓብ በእስራኤል ላይ ነገሠ (29-33)

      • ሂኤል ኢያሪኮን መልሶ ገነባ (34)

1 ነገሥት 16:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 16:7
  • +2ዜና 19:2፤ 20:34

1 ነገሥት 16:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 2:8
  • +1ነገ 13:33

1 ነገሥት 16:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 14:10, 11፤ 15:29

1 ነገሥት 16:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 15:21, 33

1 ነገሥት 16:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የኢዮርብዓምን ልጅ ናዳብን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 15:25-29

1 ነገሥት 16:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 9:31

1 ነገሥት 16:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ደም ከሚበቀሉለትም።”

  • *

    ቃል በቃል “ግንብ ላይ የሚሸና።” ወንዶችን የሚያናንቅ የዕብራይስጥ አገላለጽ ነው።

1 ነገሥት 16:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 16:1-3

1 ነገሥት 16:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 32:21፤ 1ሳሙ 12:21፤ 2ነገ 17:15፤ ኢሳ 41:29

1 ነገሥት 16:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 19:44, 48፤ 21:20, 23፤ 1ነገ 15:27

1 ነገሥት 16:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 8:26፤ ሚክ 6:16

1 ነገሥት 16:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 9:53, 54፤ 1ሳሙ 31:4፤ 2ሳሙ 17:23

1 ነገሥት 16:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 12:28-30፤ 14:7, 9

1 ነገሥት 16:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አንድ ታላንት 34.2 ኪሎ ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

  • *

    “የሼሜር ጎሳ ንብረት” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 20:1፤ 2ነገ 17:24፤ አሞጽ 6:1፤ ሥራ 8:5

1 ነገሥት 16:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚክ 6:16

1 ነገሥት 16:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 12:28-30፤ 13:33

1 ነገሥት 16:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 16:33፤ 21:4, 20-22፤ 2ነገ 10:1

1 ነገሥት 16:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 16:23, 24፤ ኢሳ 7:9

1 ነገሥት 16:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 16:25፤ 21:25፤ 2ነገ 3:1, 2

1 ነገሥት 16:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 12:28-30
  • +ዘፍ 10:15
  • +1ነገ 18:4, 19፤ 21:7፤ 2ነገ 9:30፤ ራእይ 2:20
  • +መሳ 2:11፤ 10:6፤ 2ነገ 10:19፤ 17:16

1 ነገሥት 16:32

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መቅደስ ውስጥ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 10:21, 27

1 ነገሥት 16:33

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 34:13፤ 2ነገ 10:26, 28፤ 13:6

1 ነገሥት 16:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 6:26

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/15/1998፣ ገጽ 21-22

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 7፣ ገጽ 6

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ነገ. 16:12ዜና 16:7
1 ነገ. 16:12ዜና 19:2፤ 20:34
1 ነገ. 16:21ሳሙ 2:8
1 ነገ. 16:21ነገ 13:33
1 ነገ. 16:31ነገ 14:10, 11፤ 15:29
1 ነገ. 16:61ነገ 15:21, 33
1 ነገ. 16:71ነገ 15:25-29
1 ነገ. 16:102ነገ 9:31
1 ነገ. 16:121ነገ 16:1-3
1 ነገ. 16:13ዘዳ 32:21፤ 1ሳሙ 12:21፤ 2ነገ 17:15፤ ኢሳ 41:29
1 ነገ. 16:15ኢያሱ 19:44, 48፤ 21:20, 23፤ 1ነገ 15:27
1 ነገ. 16:162ነገ 8:26፤ ሚክ 6:16
1 ነገ. 16:18መሳ 9:53, 54፤ 1ሳሙ 31:4፤ 2ሳሙ 17:23
1 ነገ. 16:191ነገ 12:28-30፤ 14:7, 9
1 ነገ. 16:241ነገ 20:1፤ 2ነገ 17:24፤ አሞጽ 6:1፤ ሥራ 8:5
1 ነገ. 16:25ሚክ 6:16
1 ነገ. 16:261ነገ 12:28-30፤ 13:33
1 ነገ. 16:281ነገ 16:33፤ 21:4, 20-22፤ 2ነገ 10:1
1 ነገ. 16:291ነገ 16:23, 24፤ ኢሳ 7:9
1 ነገ. 16:301ነገ 16:25፤ 21:25፤ 2ነገ 3:1, 2
1 ነገ. 16:311ነገ 12:28-30
1 ነገ. 16:31ዘፍ 10:15
1 ነገ. 16:311ነገ 18:4, 19፤ 21:7፤ 2ነገ 9:30፤ ራእይ 2:20
1 ነገ. 16:31መሳ 2:11፤ 10:6፤ 2ነገ 10:19፤ 17:16
1 ነገ. 16:322ነገ 10:21, 27
1 ነገ. 16:33ዘፀ 34:13፤ 2ነገ 10:26, 28፤ 13:6
1 ነገ. 16:34ኢያሱ 6:26
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ነገሥት 16:1-34

አንደኛ ነገሥት

16 ከዚያም በባኦስ ላይ የተነገረው የይሖዋ ቃል የሃናኒ+ ልጅ ወደሆነው ወደ ኢዩ+ እንዲህ ሲል መጣ፦ 2 “ከአቧራ ላይ አንስቼ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ አደረግኩህ፤+ አንተ ግን የኢዮርብዓምን መንገድ ተከተልክ፤ ሕዝቤ እስራኤልም ኃጢአት እንዲሠራ አደረግክ፤ እነሱም በኃጢአታቸው አስቆጡኝ።+ 3 ስለሆነም ባኦስንና ቤቱን ሙልጭ አድርጌ እጠርጋለሁ፤ ቤቱንም እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮርብዓም+ ቤት አደርገዋለሁ። 4 ከባኦስ ወገን የሆነውን በከተማ ውስጥ የሚሞተውን ሁሉ ውሾች ይበሉታል፤ ከእሱ ወገን የሆነውን በሜዳ ላይ የሚሞተውን ሁሉ ደግሞ የሰማይ አሞሮች ይበሉታል።”

5 የቀረው የባኦስ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮችና ኃያልነቱ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? 6 በመጨረሻም ባኦስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በቲርጻም+ ተቀበረ፤ በእሱም ምትክ ልጁ ኤላህ ነገሠ። 7 በተጨማሪም ባኦስ ልክ እንደ ኢዮርብዓም ቤት በእጁ በሠራቸው ነገሮች ይሖዋን በማስቆጣት በፊቱ መጥፎ የሆነውን ነገር ሁሉ ስለፈጸመ እንዲሁም እሱን* ስለገደለ የይሖዋ ቃል የሃናኒ ልጅ በሆነው በነቢዩ ኢዩ አማካኝነት በባኦስና በቤቱ ላይ መጣ።+

8 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ26ኛው ዓመት የባኦስ ልጅ ኤላህ በቲርጻ ሆኖ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ለሁለት ዓመትም ገዛ። 9 የግማሹ የሠረገላ ሠራዊት አለቃ የሆነው አገልጋዩ ዚምሪ በእሱ ላይ አሴረ፤ በዚህ ጊዜ ኤላህ በቲርጻ የሚገኘው የንጉሡ ቤት ኃላፊ በነበረው በአርጻ ቤት ጠጥቶ ሰክሮ ነበር። 10 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ27ኛው ዓመት ዚምሪ ገብቶ ኤላህን መትቶ ገደለው፤+ በእሱም ምትክ ነገሠ። 11 እሱም ነግሦ ገና በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጠ የባኦስን ቤት ሁሉ መታ። ከዘመዶቹም* ሆነ ከወዳጆቹ መካከል አንድም ወንድ* አላስተረፈም። 12 በዚህ መንገድ ይሖዋ በነቢዩ ኢዩ+ አማካኝነት በባኦስ ላይ በተናገረው ቃል መሠረት ዚምሪ መላውን የባኦስን ቤት አጠፋ። 13 ይህም የሆነው ባኦስ እና ልጁ ኤላህ በፈጸሙት ኃጢአት እንዲሁም ከንቱ በሆኑት ጣዖቶቻቸው አማካኝነት የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን በማስቆጣት እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ባደረጉት ኃጢአት የተነሳ ነው።+ 14 የቀረው የኤላህ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?

15 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ27ኛው ዓመት፣ ሠራዊቱ የፍልስጤማውያን የሆነችውን ጊበቶንን+ ከቦ በነበረበት ወቅት ዚምሪ በቲርጻ ለሰባት ቀን ነገሠ። 16 በኋላም ከተማዋን ከቦ የነበረው ሠራዊት “ዚምሪ ሴራ በመጠንሰስ ንጉሡን ገድሎታል” የሚል ወሬ ሰማ። በመሆኑም መላው እስራኤል የሠራዊቱ አለቃ የሆነውን ኦምሪን+ በዚያን ቀን በሰፈሩ ውስጥ በእስራኤል ላይ አነገሡት። 17 ኦምሪና ከእሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከጊበቶን ወጥተው ቲርጻን ከበቡ። 18 ዚምሪም ከተማዋ መያዟን ሲያይ በንጉሡ ቤት* ወዳለው የማይደፈር ማማ ገብቶ በውስጡ እንዳለ ቤቱን በእሳት አቃጠለው፤ በዚህም የተነሳ ሞተ።+ 19 ይህም የሆነው የኢዮርብዓምን መንገድ በመከተል በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር በመፈጸም በሠራው በገዛ ኃጢአቱና እስራኤላውያን እንዲሠሩ ባደረገው ኃጢአት የተነሳ ነው።+ 20 የቀረው የዚምሪ ታሪክና የጠነሰሰው ሴራ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ ይገኝ የለም?

21 የእስራኤል ሕዝብ በሁለት አንጃ የተከፈለው በዚህ ጊዜ ነበር። አንደኛው ወገን የጊናትን ልጅ ቲብኒን ለማንገሥ ስለፈለገ የእሱ ተከታይ ሆነ፤ ሌላኛው ወገን ደግሞ ኦምሪን ተከተለ። 22 ሆኖም ኦምሪን የተከተለው ሕዝብ የጊናትን ልጅ ቲብኒን በተከተለው ሕዝብ ላይ አየለ። በመሆኑም ቲብኒ ሞተ፤ ኦምሪም ነገሠ።

23 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ31ኛው ዓመት ኦምሪ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ለ12 ዓመትም ገዛ። በቲርጻም ሆኖ ለስድስት ዓመት ገዛ። 24 እሱም የሰማርያን ተራራ ከሼሜር ላይ በሁለት ታላንት* ብር ገዛ፤ በተራራውም ላይ ከተማ ገነባ። የገነባትንም ከተማ የተራራው ጌታ በሆነው በሼሜር ስም ሰማርያ*+ ብሎ ሰየማት። 25 ኦምሪም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ማድረጉን ቀጠለ፤ ከእሱ በፊት ከነበሩት ሁሉ የከፋ ድርጊት ፈጸመ።+ 26 የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በሄደበት መንገድ ሁሉ ሄደ፤ እንዲሁም ኢዮርብዓም እስራኤላውያን በከንቱ ጣዖቶቻቸው አማካኝነት የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን እንዲያስቆጡት በማድረግ በተከተለው የኃጢአት ጎዳና ተመላለሰ።+ 27 የቀረው የኦምሪ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮችና በኃያልነቱ የፈጸማቸው ጀብዱዎች በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? 28 በመጨረሻም ኦምሪ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ በእሱም ምትክ ልጁ አክዓብ+ ነገሠ።

29 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ38ኛው ዓመት የኦምሪ ልጅ አክዓብ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ የኦምሪ ልጅ አክዓብ በሰማርያ+ ሆኖ በእስራኤል ላይ ለ22 ዓመት ገዛ። 30 የኦምሪ ልጅ አክዓብ ከእሱ በፊት የነበሩት ሁሉ ከፈጸሙት የከፋ ድርጊት በይሖዋ ፊት ፈጸመ።+ 31 አክዓብ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም+ በተከተለው የኃጢአት ጎዳና መመላለሱ ሳያንሰው የሲዶናውያን+ ንጉሥ የኤትባዓል ልጅ የሆነችውን ኤልዛቤልን+ አገባ፤ እንዲሁም ባአልን ማገልገልና+ ለእሱ መስገድ ጀመረ። 32 እንዲሁም በሰማርያ ለባአል በሠራው ቤት+ ውስጥ* ለባአል መሠዊያ አቆመ። 33 በተጨማሪም አክዓብ የማምለኪያ ግንድ* ሠራ።+ እንዲሁም ከእሱ በፊት ከነበሩት የእስራኤል ነገሥታት ሁሉ ይበልጥ የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን የሚያስቆጣ ድርጊት ፈጸመ።

34 በአክዓብ ዘመን የቤቴል ሰው የሆነው ሂኤል ኢያሪኮን መልሶ ገነባ። ይሖዋ በነዌ ልጅ በኢያሱ አማካኝነት በተናገረው ቃል መሠረት የከተማዋን መሠረት ሲጥል የበኩር ልጁ አቤሮን ሞተ፤ በሮቿን ሲያቆም ደግሞ የመጨረሻ ልጁ ሰጉብ ሞተ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ