የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዕብራውያን 7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዕብራውያን የመጽሐፉ ይዘት

      • መልከጼዴቅ፣ ልዩ የሆነ ንጉሥና ካህን (1-10)

      • የክርስቶስ ክህነት ያለው ብልጫ (11-28)

        • ክርስቶስ ሙሉ በሙሉ ሊያድን ይችላል (25)

ዕብራውያን 7:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 14:17-20

ዕብራውያን 7:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “አካፈለው።”

ዕብራውያን 7:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 110:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/15/1995፣ ገጽ 19

    11/15/1993፣ ገጽ 31

ዕብራውያን 7:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ፓትሪያርክ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 14:20

ዕብራውያን 7:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 40:12, 15
  • +ዘኁ 18:21, 26፤ ዘዳ 14:28

ዕብራውያን 7:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 12:7፤ 14:18-20፤ 17:6፤ 22:17

ዕብራውያን 7:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 7:3

ዕብራውያን 7:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 9/2019፣ ገጽ 2

ዕብራውያን 7:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ወደፊት የሚወለድ የአባቱ የአብርሃም ዘር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 14:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 9/2019፣ ገጽ 2

ዕብራውያን 7:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 3:20፤ ዕብ 7:19፤ 9:9፤ 10:1
  • +መዝ 110:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 9/2019፣ ገጽ 3

ዕብራውያን 7:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 3:27፤ 1ቆሮ 9:21፤ ገላ 6:2፤ ቆላ 2:13, 14

ዕብራውያን 7:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 18:6, 7

ዕብራውያን 7:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 49:10፤ ማቴ 1:1, 3፤ ሉቃስ 3:23, 33

ዕብራውያን 7:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 3:1፤ 7:26
  • +መዝ 110:4

ዕብራውያን 7:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 6:9፤ 1ጢሞ 6:16

ዕብራውያን 7:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 110:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 2/2020፣ ገጽ 2

ዕብራውያን 7:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 8:3፤ ዕብ 9:9፤ 13:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    10/2023፣ ገጽ 25

ዕብራውያን 7:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 13:38, 39፤ ገላ 2:15, 16፤ ዕብ 10:1
  • +1ጴጥ 1:3, 4
  • +ዮሐ 14:6፤ ዕብ 4:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    10/2023፣ ገጽ 25

ዕብራውያን 7:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

  • *

    ወይም “አይጸጸትም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 110:4

ዕብራውያን 7:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እንደ መያዣ የተሰጠ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 31:31፤ ማቴ 26:27, 28፤ 1ቆሮ 11:25፤ ዕብ 8:6፤ 9:15፤ 12:22, 24

ዕብራውያን 7:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 6:4

ዕብራውያን 7:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 1:33፤ ዕብ 7:15, 16

ዕብራውያን 7:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 8:34፤ 1ጢሞ 2:5፤ ዕብ 9:24፤ 1ዮሐ 2:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 140

    ንቁ!፣

    11/2010፣ ገጽ 21

ዕብራውያን 7:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 53:9፤ 1ጴጥ 2:21, 22
  • +ኤፌ 1:20, 21፤ 1ጴጥ 3:22

ዕብራውያን 7:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 9:8, 15
  • +ዘኁ 28:3
  • +ሮም 6:10፤ ዕብ 9:28፤ 10:14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/15/2008፣ ገጽ 14

ዕብራውያን 7:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 16:11
  • +መዝ 2:7፤ 110:4
  • +ዕብ 2:10፤ 5:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/15/2008፣ ገጽ 14

ተዛማጅ ሐሳብ

ዕብ. 7:1ዘፍ 14:17-20
ዕብ. 7:3መዝ 110:4
ዕብ. 7:4ዘፍ 14:20
ዕብ. 7:5ዘፀ 40:12, 15
ዕብ. 7:5ዘኁ 18:21, 26፤ ዘዳ 14:28
ዕብ. 7:6ዘፍ 12:7፤ 14:18-20፤ 17:6፤ 22:17
ዕብ. 7:8ዕብ 7:3
ዕብ. 7:10ዘፍ 14:18
ዕብ. 7:11ሮም 3:20፤ ዕብ 7:19፤ 9:9፤ 10:1
ዕብ. 7:11መዝ 110:4
ዕብ. 7:12ሮም 3:27፤ 1ቆሮ 9:21፤ ገላ 6:2፤ ቆላ 2:13, 14
ዕብ. 7:13ዘኁ 18:6, 7
ዕብ. 7:14ዘፍ 49:10፤ ማቴ 1:1, 3፤ ሉቃስ 3:23, 33
ዕብ. 7:15ዕብ 3:1፤ 7:26
ዕብ. 7:15መዝ 110:4
ዕብ. 7:16ሮም 6:9፤ 1ጢሞ 6:16
ዕብ. 7:17መዝ 110:4
ዕብ. 7:18ሮም 8:3፤ ዕብ 9:9፤ 13:9
ዕብ. 7:19ሥራ 13:38, 39፤ ገላ 2:15, 16፤ ዕብ 10:1
ዕብ. 7:191ጴጥ 1:3, 4
ዕብ. 7:19ዮሐ 14:6፤ ዕብ 4:16
ዕብ. 7:21መዝ 110:4
ዕብ. 7:22ኤር 31:31፤ ማቴ 26:27, 28፤ 1ቆሮ 11:25፤ ዕብ 8:6፤ 9:15፤ 12:22, 24
ዕብ. 7:231ዜና 6:4
ዕብ. 7:24ሉቃስ 1:33፤ ዕብ 7:15, 16
ዕብ. 7:25ሮም 8:34፤ 1ጢሞ 2:5፤ ዕብ 9:24፤ 1ዮሐ 2:1
ዕብ. 7:26ኢሳ 53:9፤ 1ጴጥ 2:21, 22
ዕብ. 7:26ኤፌ 1:20, 21፤ 1ጴጥ 3:22
ዕብ. 7:27ዘሌ 9:8, 15
ዕብ. 7:27ዘኁ 28:3
ዕብ. 7:27ሮም 6:10፤ ዕብ 9:28፤ 10:14
ዕብ. 7:28ዘሌ 16:11
ዕብ. 7:28መዝ 2:7፤ 110:4
ዕብ. 7:28ዕብ 2:10፤ 5:9
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዕብራውያን 7:1-28

ለዕብራውያን የተጻፈ ደብዳቤ

7 አብርሃም ነገሥታትን ድል አድርጎ ሲመለስ የሳሌም ንጉሥና የልዑሉ አምላክ ካህን የሆነው ይህ መልከጼዴቅ አግኝቶት ባረከው፤+ 2 አብርሃም ደግሞ ከሁሉ ነገር አንድ አሥረኛ ሰጠው።* በመጀመሪያ ስሙ “የጽድቅ ንጉሥ” ማለት ነው፤ ደግሞም የሳሌም ንጉሥ ማለትም “የሰላም ንጉሥ” ነው። 3 አባትና እናትም ሆነ የዘር ሐረግ እንዲሁም ለዘመኑ መጀመሪያ፣ ለሕይወቱም መጨረሻ የለውም፤ ከዚህ ይልቅ የአምላክን ልጅ እንዲመስል በመደረጉ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።+

4 እንግዲህ የቤተሰብ ራስ* የሆነው አብርሃም ምርጥ ከሆነው ምርኮ ላይ አንድ አሥረኛውን የሰጠው+ ይህ ሰው ምን ያህል ታላቅ እንደነበረ ተመልከቱ። 5 እርግጥ የክህነት ኃላፊነት የሚቀበሉ ከሌዊ ልጆች ወገን የሆኑት ሰዎች+ ምንም እንኳ ወንድሞቻቸው የአብርሃም ዘሮች ቢሆኑም ከሕዝቡ ማለትም ከገዛ ወንድሞቻቸው አሥራት እንዲሰበስቡ ሕጉ ያዛል።+ 6 ሆኖም ከእነሱ የትውልድ ሐረግ ያልመጣው ይህ ሰው ከአብርሃም አሥራት የተቀበለ ሲሆን የተስፋ ቃል የተሰጠውን ሰው ባርኮታል።+ 7 እንግዲህ አነስተኛ የሆነው ከእሱ በሚበልጠው እንደተባረከ ምንም ጥርጥር የለውም። 8 በአንድ በኩል አሥራት የሚቀበሉት ሟች የሆኑ ሰዎች ሲሆኑ በሌላ በኩል ግን አሥራት የሚቀበለው ሕያው ሆኖ እንደሚኖር የተመሠከረለት ሰው ነው።+ 9 እንግዲህ አሥራት የሚቀበለው ሌዊ እንኳ በአብርሃም በኩል አሥራት ከፍሏል ማለት ይቻላል፤ 10 መልከጼዴቅ አብርሃምን ባገኘው ጊዜ ሌዊ ገና በአባቱ በአብርሃም አብራክ ውስጥ* ነበርና።+

11 እንግዲህ ፍጽምና ሊገኝ የሚችለው በሌዊ ክህነት አማካኝነት ቢሆን ኖሮ+ (ክህነቱ ለሕዝቡ የተሰጠው ሕግ አንዱ ገጽታ ስለሆነ)፣ እንደ አሮን ሥርዓት ሳይሆን እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት+ ያለ ተብሎ የተነገረለት ሌላ ካህን መነሳቱ ምን ያስፈልግ ነበር? 12 ክህነቱ ስለሚለወጥ ሕጉም የግድ መለወጥ ያስፈልገዋልና።+ 13 ይህ ሁሉ ነገር የተነገረለት ሰው ከሌላ ነገድ የመጣ ነውና፤ ከዚህ ነገድ ማንም ወደ መሠዊያው ቀርቦ ያገለገለ የለም።+ 14 ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደወጣ የታወቀ ነውና፤+ ይሁንና ሙሴ ከዚህ ነገድ ካህናት እንደሚገኙ የተናገረው ነገር የለም።

15 ደግሞም እንደ መልከጼዴቅ ያለ ሌላ ካህን+ ሲነሳ ይህ ጉዳይ ይበልጥ ግልጽ ይሆናል፤+ 16 እሱ ካህን የሆነው በሥጋዊ ትውልድ ላይ በተመካውና ሕጉ በያዘው መሥፈርት ሳይሆን የማይጠፋ ሕይወት+ እንዲኖረው ባስቻለው ኃይል ነው። 17 “እንደ መልከጼዴቅ፣ አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ተብሎ ተመሥክሮለታልና።+

18 እንግዲህ የቀድሞው ትእዛዝ ደካማና ፍሬ ቢስ በመሆኑ ተሽሯል።+ 19 ሕጉ የትኛውንም ነገር ወደ ፍጽምና አላደረሰምና፤+ ወደ አምላክ የምንቀርብበት የተሻለ ተስፋ+ መሰጠቱ ግን ይህን ማድረግ ችሏል።+ 20 በተጨማሪም ይህ ያለመሐላ እንዳልሆነ ሁሉ 21 (ያለመሐላ ካህናት የሆኑ ሰዎች አሉና፤ እሱ ግን በመሐላ ካህን ሆኗል፤ ይህም የሆነው “ይሖዋ* ‘አንተ ለዘላለም ካህን ነህ’ ብሎ ምሏል፤ ደግሞም ሐሳቡን አይለውጥም”* በማለት ስለ እሱ የተናገረው አምላክ በማለው መሐላ መሠረት ነው፤)+ 22 እንደዚሁም ኢየሱስ ለተሻለ ቃል ኪዳን ዋስትና* ሆኗል።+ 23 ከዚህም በተጨማሪ ካህናት አገልግሎታቸውን እንዳይቀጥሉ ሞት ስለሚያግዳቸው አንዱ ሌላውን እየተካ እንዲያገለግል ብዙዎች ካህናት መሆን ነበረባቸው፤+ 24 እሱ ግን ለዘላለም+ ሕያው ሆኖ ስለሚኖር ክህነቱ ተተኪ የለውም። 25 ስለሆነም ለእነሱ ለመማለድ ሁልጊዜ ሕያው ሆኖ ስለሚኖር በእሱ አማካኝነት ወደ አምላክ የሚቀርቡትን ፈጽሞ ሊያድናቸውም ይችላል።+

26 እኛ የሚያስፈልገን ታማኝ፣ ቅን የሆነ፣ ያልረከሰ፣+ ከኃጢአተኞች የተለየና ከሰማያት በላይ ከፍ ያለ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ነው።+ 27 እነዚያ ሊቃነ ካህናት ያደርጉ እንደነበረው፣ በመጀመሪያ ለራሱ ኃጢአት ከዚያም ለሕዝቡ ኃጢአት+ በየዕለቱ መሥዋዕት ማቅረብ አያስፈልገውም፤+ ምክንያቱም ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ባቀረበ ጊዜ ይህን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ፈጽሞታል።+ 28 ሕጉ ድክመት ያለባቸውን ሰዎች ሊቃነ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፤+ ከሕጉ በኋላ የመጣው የመሐላ ቃል+ ግን ለዘላለም ፍጹም የተደረገውን ልጅ+ ይሾማል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ