የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም
መስከረም 10 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 39 (86)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
13 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
22 ደቂቃ:- “አገልግሎታችሁን በተሟላ ሁኔታ እየፈጸማችሁ ነውን?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከ1-3 ባሉት አንቀጾች ላይ ከተወያያችሁ በኋላ የመስከረም 15 መጠበቂያ ግንብ እና የመስከረም 2001 ንቁ! መጽሔቶችን በመጠቀም መጽሔት ሲበረከት የሚያሳዩ ሁለት አጫጭር ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በአንቀጽ 4 ላይ ከተወያያችሁ በኋላ የተሰጠውን አቀራረብ በመጠቀም ለዘላለም መኖር መጽሐፍ ሲበረከት የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።
መዝሙር 71 (163) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 17 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 42 (92)
15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። በዚህ ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ እንዴት ማስተዋወቅ እንደሚቻል የሚያሳዩ ከዚህ በፊት የወጡ የመንግሥት አገልግሎታችን እትሞችን ጠቁም።
15 ደቂቃ:- ያለፈው ዓመት እንቅስቃሴያችን ምን ይመስል ነበር? በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ ንግግር። የጉባኤውን የ2001 የአገልግሎት ዓመት ሪፖርት ጎላ ያሉ ገጽታዎች ከልስ። ስለተከናወኑት መልካም ነገሮች ሁሉንም አመስግን። በተሰብሳቢዎች ቁጥር፣ በመስክ አገልግሎት አዘውታሪነት፣ የአገልግሎት ክልሎችን በመሸፈን፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንቅስቃሴ ረገድ ጉባኤው ምን እንዳከናወነ በማተኮር ድክመቶችን ለማሻሻል ምን መደረግ እንዳለበት ተናገር። ለሚቀጥለው ዓመት ሊደረስባቸው የሚችሉ ግቦችን ጠቁም።
15 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን። በንግግር የሚቀርብ። የጉባኤውን ሳምንታዊ የመስክ ስምሪት ስብሰባዎች ፕሮግራም ተናገር። በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ የሚገኙ አስፋፊዎች በሙሉ ውጤታማ ውይይት እንዲደረግ አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ተናገር። ጉባኤው ይህን የአገልግሎት ዝግጅት እንዲደግፍ አበረታታ።
መዝሙር 52 (129) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 24 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 24 (50)
15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?” በሚለው ርዕስ ሥር በተሰጠው ሐሳብ መሠረት ጥቅምት 1 መጠበቂያ ግንብ እና ጥቅምት 2001 ንቁ! መጽሔቶችን በመጠቀም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ።
30 ደቂቃ:- በዓለም ያሉትን ነገሮች ሳይሆን አምላክን ውደዱ። (1 ዮሐ. 2:15-17) ባለፈው የአገልግሎት ዓመት ውስጥ ያደረግነውን የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም በመከለስ የሚቀርብ ንግግርና ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። አስፋፊዎች ስለተማሯቸው ቁልፍ ነጥቦች ሐሳብ እንዲሰጡ እንዲሁም ትምህርቱን በግል ወይም በቤተሰብ ደረጃ እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደቻሉ እንዲናገሩ ጋብዝ። (ሐሳብ የሚሰጡባቸውን ነጥቦች አስቀድሞ ማከፋፈል ይቻላል።) የሚከተሉትን ክፍሎች ሸፍን:- (1) “ለአምላክ ያለን ፍቅር ለአገልግሎት ያነሳሳናል።” ለአምላክ ያለን ፍቅር እንዳንሰብክ እንቅፋት ሊሆኑብን የሚችሉትን እንደ ዓይናፋርነት፣ ብቃት የለኝም የሚል ስሜትና የሰው ፍርሃት ያሉ አሉታዊ ስሜቶች እንድናሸንፍ ይረዳናል። (2) “ይሖዋን የሚወድዱ ክፉውን ይጠላሉ።” (w99 10/1 28-31) ከአምላክ ጋር የሚኖረን ዝምድና እሱ የሚጠላውን በመጥላታችን ላይ የተመካ ነው። ይኸውም ክፉ መሆኑ በግልጽ የሚታወቀውን ብቻ ሳይሆን ስውር ስህተቶችንም መጥላትን ይጨምራል። (3) “ከሁሉ የሚበልጠውን የፍቅር መንገድ ተከተሉ።” (w92 7/15 27-30) አንደኛ ቆሮንቶስ 13:4-8 የሌሎችን አለፍጽምና ችለን ማለፍ ያለብን፣ ራስ ወዳድነትንና የፉክክር መንፈስን ማስወገድ የሚኖርብን ጎጂ ሐሜት መንዛት የሌለብን እንዲሁም ለአምላክ ድርጅት ምንጊዜም ታማኝ ሆነን መኖር ያለብን ለምን እንደሆነ ይገልጻል። (4) “በዓለም ያሉትን ነገሮች እንዴት ልንመለከታቸው ይገባል?” በዓለም ያሉትን ነገሮች መውደድ፣ ለሥጋ ምኞቶች መሸነፍ፣ በዓይን አምሮት መታለል ወይም ያለኝ ይታይልኝ የሚል መንፈስ ማንጸባረቅ አይኖርብንም። (5) “የዓለም ክፍል አለመሆን ጥበቃ ይሆነናል።” ሁለተኛ ቆሮንቶስ 6:14-17 አንዳንድ እምነቶች፣ ልማዶችና ድርጊቶች በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት እንድናጣ ሊያደርጉን እንደሚችሉ ይገልጻል። ዲያብሎስ የሚሸርባቸውን ወጥመዶች ማስተዋልና ከእነርሱ መራቅ ይገባናል። (6) “አምላክን ለሚወዱ ሰዎች የተሰጡ መለኮታዊ ተስፋዎች።” (w86 6/15 5-6) የይሖዋ በረከት ለሕይወታችን ደስታ ይጨምርልናል፣ በመንፈሳዊም ያበለጽገናል።—1 ጢሞ. 6:17-19
መዝሙር 55 (133) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 45 (106)
5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የመስከረም የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው።
20 ደቂቃ:- “መልካም አድርጉ ምስጋናም ይሆንላችኋል!” በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በነሐሴ 2000 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 11 ላይ የሚገኙትን ነጥቦች ጨምረህ ተገቢ የሆኑ የአውራጃ ስብሰባ ማሳሰቢያዎችን ተናገር።
20 ደቂቃ:- “ለስብከቱ ሥራ እንቅፋት ይሆናልን?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ለመንግሥቱ ፍላጎቶች ቅድሚያ እንድንሰጥ የሚያስችሉ ነገሮችን በማስቀደም በዓለማዊ ሥራ ረገድ ሚዛናዊ የመሆንን አስፈላጊነት ጎላ አድርገህ ተናገር። መንፈሳዊ ፍላጎታቸውን መሥዋዕት ሳያደርጉ ለቤተሰባቸው ቁሳዊ ነገሮችን የማቅረቡን ተፈታታኝ ሁኔታ እንዴት እንደተወጡት እንዲናገሩ በጉባኤው ውስጥ ያሉ አንዳንድ የቤተሰብ ራሶችን ጋብዝ።
መዝሙር 38 (85) እና የመደምደሚያ ጸሎት።