የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/03 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ግንቦት 12 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 19 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 26 የሚጀምር ሳምንት
  • ሰኔ 2 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 5/03 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ግንቦት 12 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 23 (48)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 12 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የሚያዝያ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሚያዝያ 2003 ንቁ! ሲበረከት የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው አንደኛውን መጽሔት ብቻ ያስተዋውቅና ሌላኛውንም መጽሔት አያይዞ ያበረክታል። በሠርቶ ማሳያው ላይ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚቻልበት ዝግጅት እንዲጠቀስ አድርግ።

20 ደቂቃ:- ወላጆች  ​—⁠ ልጆቻችሁን በመንፈሳዊ እንዲያድጉ እርዷቸው። የአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 9-12 እና 21-38 ላይ ባሉት ዋና ዋና ሐሳቦች ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። ወላጆች ልጆቻቸው በአገልግሎት እድገት እንዲያደርጉ ለማሰልጠን ከላይ በተጠቀሰው ጽሑፍ ላይ የቀረበውን ትምህርት በቤተሰብ ጥናታቸው እንዲጠቀሙበት አበረታታ። ትናንሽ ልጆች ለአገልግሎት የሚያስፈልጓቸውን ችሎታዎች እንዲያዳብሩ ለመርዳት የሚጠቅሙ ነጥቦችን ጥቀስ።

15 ደቂቃ:- “ወንጌሉ በአደራ ተሰጥቶናል።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በስብከቱ ሥራ የሚያደርጉትን ተሳትፎ ለማሳደግ ሁኔታዎቻቸውን እንዴት እንዳመቻቹ የሚናገሩ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች አስቀድመህ አዘጋጅ።

መዝሙር 21 (46) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 19 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 29 (62)

15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። “ዓለም አቀፍ የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ በአንዳንድ የአውሮፓ አገሮች” የሚለውን በንግግር አቅርብ። የገንዘብ አቅማቸው ውስን በሆኑ እንደ ኢትዮጵያ ባሉና በሌሎች አገሮችም ውስጥ የግንባታው ወጪ የሚሸፈነው ለመንግሥት አዳራሽ ግንባታ በሚደረገው መዋጮ መሆኑን ግለጽ።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

15 ደቂቃ:- “በዘመናችን መቶ ዓመት ባስቆጠረው ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት እየተካፈላችሁ ነውን?” በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።

መዝሙር 56 (135) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 26 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 77 (174)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የግንቦት የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። የጉባኤያችሁን የመስክ አገልግሎት ሪፖርት ከልስ። በገጽ 12 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የሚያዝያ 15 መጠበቂያ ግንብ እና የሚያዝያ 22 (እንግሊዝኛ) ንቁ! ሲበረከት የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው አንደኛውን መጽሔት ብቻ ያስተዋውቅና ሌላኛውንም መጽሔት አያይዞ ያበረክታል። በአንደኛው ሠርቶ ማሳያ መጨረሻ ላይ የቤቱ ባለቤት መጽሔት አልወስድም ሲል አስፋፊው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ? የተባለውን ትራክት ያበረክትለታል።

15 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን። በንግግር ይቀርባል። በጉባኤው ክልል ውስጥ የስልክ ምሥክርነት ለመስጠት ውጤታማ ሆነው የተገኙ አንዳንድ አቀራረቦችን በአጭሩ ተናገር።

20 ደቂቃ:- “የአምላክ ቃል እውነት ነው።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ለአንቀጾቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች ተጠቀም። አስፋፊዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅመው ለጥያቄዎቻቸው መልስ በመስጠት እውነትን እንዲማሩ እንዴት እንደረዷቸው አድማጮች እንዲናገሩ ጋብዝ። አንቀጽ 4ን ስትወያዩ አንድ ጥሩ ችሎታ ያለው አስፋፊ በታኅሣሥ 2001 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 1 አን. 3-4 ላይ “የአምላክን ቃል በትክክል ተጠቀምበት” በሚለው ርዕስ ከቀረቡት ሐሳቦች ውስጥ አንዳንዶቹን በመጠቀም አንድን ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያነጋግር እንዴት በመጽሐፍ ቅዱስ መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ።

መዝሙር 20 (45) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሰኔ 2 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 16 (37)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከጥር 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር እና እውቀት መጽሐፍን ለማበርከት የሚያስችሉ አንድ ወይም ሁለት አቀራረቦችን ተናገር።

20 ደቂቃ:- ክብር ያለው ጋብቻ​—⁠መለኮታዊ መሥፈርት ነው። በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በብዙ አገሮች ውስጥ ወንድና ሴት በሕጋዊ ሁኔታ ሳይጋቡ አብረው መኖራቸው የተለመደ ነው። አንዳንዶች ይህ ጥቅም እንዳለው ይናገራሉ። ጋብቻ መለኮታዊ ዝግጅት መሆኑን ጎላ አድርገህ በመጥቀስ መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ጉዳይ ላይ ያለውን አመለካከት ተናገር። (ማመራመር ገጽ 248-9) ሳይጋቡ አብሮ መኖር ዝሙት መፈጸም ነው። (ለቤተሰብ ደስታ ገጽ 17) ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከጋብቻ በፊት አብሮ መኖር ትዳሩ ስኬታማ ለመሆን ያለውን አጋጣሚ ይቀንሰዋል እንጂ ብዙዎች እንደሚሉት ለዘላቂ ትዳር ዋስትና አይሆንም። (ንቁ! መጋቢት 2002 ገጽ 31፤ ንቁ! 92 9/8 ገጽ 28 (እንግሊዝኛ)፤ ንቁ! 91 5/8 ገጽ 28 (እንግሊዝኛ)) ክርስቲያኖች ከሥነ ምግባር መሥፈርቶቹ ጋር ተስማምተው በመኖር ይሖዋን ያከብራሉ። እንዲህ በማድረጋቸው ራሳቸውንም ይጠቅማሉ።​—⁠ኢሳ. 48:17, 18

15 ደቂቃ:- ጥቅም እያገኘህበት ነው? የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የበላይ ተመልካች ከአድማጮች ጋር በውይይት ያቀርበዋል። ከጥር ወር ጀምሮ የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት አዲስ አቀራረብ እንዲኖረው ተደርጓል። ከትምህርት ቤቱ አዳዲስ ገጽታዎች መካከል አንዳንዶቹን በአጭሩ ተናገር። እስካሁን የታዩትን መልካም ውጤቶች ጥቀስ። ተጨማሪ ተማሪዎች በትምህርት ቤቱ ተመዝግበዋል? ተሳትፎ የማድረግ ጉጉታቸው ጨምሯል? በምክር አሰጣጥ ረገድ በተደረገው ለውጥ ተማሪዎች እየተጠቀሙ ያሉት እንዴት ነው? አድማጮች እስካሁን ምን ጥቅም እንዳገኙና ወደፊትስ ከአዲሱ ፕሮግራም እንዴት ሊጠቀሙ እንደሚችሉ እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 97 (217) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ