የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/03 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ነሐሴ 11 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 18 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 25 የሚጀምር ሳምንት
  • መስከረም 1 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 8/03 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ነሐሴ 11 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 95 (213)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የሐምሌ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሐምሌ 2003 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው አንደኛውን መጽሔት ብቻ ያስተዋውቅና ሌላኛውን መጽሔት አያይዞ ያበረክታል። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ ውይይቱን ለማስቆም “ሥራ አለብኝ” ለሚል ሰው ምን መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳይ ይሁን።​—⁠ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 19ን ተመልከት።

15 ደቂቃ:- “የይሖዋን ጥሩነት ኮርጁ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አድማጮች ደግነት ማሳየት ምስክርነት ለመስጠት የሚያስችል አጋጣሚ እንዴት እንደከፈተላቸው የሚያሳይ አጠር ያለ ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ። የጉባኤው አባላት የእምነት ባልንጀሮቻቸውን ለመርዳት ለሚያደርጉት ጥረት አመስግናቸው።

20 ደቂቃ:- “አቅኚነት የሚያስገኛቸው በረከቶች።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ለአንቀጾቹ በቀረቡት ጥያቄዎች ተጠቀም። አንድ ወይም ሁለት አቅኚዎች በዚህ አገልግሎት ያገ​ኙትን በረከት እንዲናገሩ ጋብዛቸው። አቅኚ የመሆን ፍላጎት ያለው ማንኛውም አስፋፊ ከጉባኤው ጸሐፊ ማመልከቻ መውሰድ እንደሚችል ተናገር።

መዝሙር 74 (168) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 18 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 37 (82)

12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

15 ደቂቃ:- “መንፈስን የሚያድስ ሥራ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመ​ግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ክርስቲያናዊው አገልግሎት መንፈስን የሚያድስ የሆነላቸው እንዴት እንደሆነ የሚናገሩ ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች አስቀድመህ አዘጋጅ።

18 ደቂቃ:- “የአምልኮ ቦታችንን በሚገባ እንያዝ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። (አንቀጽ 1-5) ለአንቀጾቹ በቀረቡት ጥያቄዎች ተጠቀም። አንቀጽ 3 እና 4ን ስትወያዩ ጉባኤው አዳራሹን ለማጽዳት ያደረገውን ዝግጅት ተናገር። ትኩረት የሚያሻቸውን ጉዳዮች ግለጽ። አዳራሹን ለንጹሕ አምልኮ መሰብሰቢያነት እንደሚገባ አድርገው ለመያዝ ለሚያደርጉት ጥረት አመስግናቸው።

መዝሙር 49 (114) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 25 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 78 (175)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም የሐምሌ 15 መጠበቂያ ግንብ እና የሐምሌ 22 ንቁ! (እንግሊዝኛ) መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው አንደኛውን መጽሔት ብቻ ያስተዋውቅና ሌላኛውን መጽሔት አያይዞ ያበ​ረክታል። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አንድ ወላጅ በአሥራዎቹ ዕድሜ ከሚገኝ/ከምትገኝ ወንድ ወይም ሴት ልጁ ጋር መጽሔት ለማበርከት ሲለማመዱ አሳይ። ሠርቶ ማሳያውን ከማቅረባቸው በፊት የቀረቡትን የመግቢያ ሐሳቦች በአጭሩ ሲከልሱ ይታያል።

15 ደቂቃ:- “ይሖዋን ለማወደስ በአንድነት መሰብሰብ።” በአካባቢያችሁ የአውራጃ ስብሰባ የሚደረግበትን ቀን ከተናገርክ በኋላ በስብሰባው ላይ ለመገኘት አስቀድመው እቅድ እንዲያወጡ አበረታታ።

20 ደቂቃ:- ምስራቹን ለመስበክ ደፋሮች ሁኑ። (1 ተ⁠ሰ. 2:2) በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ብዙዎች የመንግሥቱን ምሥራች ለሌሎች መስበክ የሚያስፈራቸው ለምን እንደሆነ ግለጽ። ለብዙ ዓመታት በስብከቱ ሥራ ሲካፈሉ የቆዩ አንዳንድ አስፋፊዎች እንኳን መስበክ ያስፈራቸዋል። በታኅሣሥ 1, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 25፣ በታኅሣሥ 15, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 25 እና በሚያዝያ 1, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 31 ላይ ከሚገኙት ተሞክሮዎች አንዳንዶቹን ተናገር። አድማጮች ፍርሃት በተሰማቸው ጊዜ ደፍረው ምሥራቹን መስበክ የቻሉት እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ። በታኅሣሥ 15, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 23-4 ላይ ባለው ተሞክሮ መሠረት ከይሖዋ ድፍረት እንዲያገኙ በማበረታታት ደምድም።

መዝሙር 34 (77) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መስከረም 1 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 35 (79)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስ​ፋፊዎች የነሐሴ የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በመስከረም የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር።

15 ደቂቃ:- ተመልሳችሁ እንደምትጠይቋቸው የገባችሁትን ቃል ትጠብቃላችሁ? በመስከረም 15, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 10-⁠11 ላይ “ቃላችንን የምንጠብቅባቸው ሌሎች መንገዶች” በሚለው ርዕስ የተመሠረተ ንግግርና ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። በአገልግሎታችን ላይ ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ሲያጋጥሙን አብዛኛውን ጊዜ ውይይታችንን በሌላ ጊዜ ለመቀጠል ቀጠሮ እንይዛለን። ቃል በገባነው መሠረት በታማኝነት ተመልሰን እንጠይቃቸዋለን? ቃላችንን እንድንጠብቅ የሚያነሳሱ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን ከልስ። አድማጮች ጊዜ ሳያባክኑ ተመልሰው በመሄዳቸው እንዴት እንደተባረኩ የሚያሳዩ ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ።

20 ደቂቃ:- “የአምልኮ ቦታችንን በሚገባ እንያዝ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። (አንቀጽ 6-​12) ለአንቀጾቹ በቀረቡት ጥያቄዎች ተጠቀም። በገጽ 4 ላይ የሚገኘውን ሣጥን በማጉላት አዳራሹን በአግባቡ የመያዝን አስፈላጊነት ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። አዳራሻችሁ ስለሚገኝበት ሁኔታ አጠር ያለ ሪፖርት ካቀረብህ በኋላ እድሳት ወይም ማሻሻያ ለማድረግ እቅድ ወጥቶ ከሆነ ተናገር።

መዝሙር 22 (47) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ